Get Mystery Box with random crypto!

ከኢየሱስ ጋር ካልሆነ ከሰይጣን ጋር ቻት ማድረጊያ አፕ ተሰራ አዲስ AI chatbot መተግበሪያ | 🇪🇹 ኢትዮ Students

ከኢየሱስ ጋር ካልሆነ ከሰይጣን ጋር ቻት ማድረጊያ አፕ ተሰራ

አዲስ AI chatbot መተግበሪያ "ቴክስት ከኢየሱስ ጋር" በሚል ተጠቃሚዎች እንደ ኢየሱስ በተጨማሪም ሌሎች መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ካሉ ነብያትና ታሪካቸው ከተጠቀሱ ሰዎች ጋር ስማቸውን እየተጠራሩ ውይይት እንዲያደርጉ ያስችላቸዋል። ሆኖም ተጠቃሚዎች በሌላ በኩል የ AI chatbot መተግበሪያን ሲጠቀሙ ከሰይጣን ጋር መወያየት የሚያስችል መሆኑ ውዝግብ አስነስቷል።

አፕሊኬሽኑ የተዘጋጀው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶችን በመጠቀም ነው። የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ብቅ ማለት የሁሉንም ሰው ህይወት እያሻሻለ ሲሆን በቴክኖሎጂ ኢንደስትሪው ውስጥ ብቻ ሳይሆን AI የመምህር፣ አጋር እና አልፎ ተርፎም የስነ ከዋክብትን ሚና በመጫወት የሰዎች ህይወት አካል እየሆነ እንደሚገኝ ሎስ አንጀለስ ውስጥ መሰረቱን ያደረገው ካት ሉፍ የሶፍትዌር ኩባንያ አስታውቋል።


አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ሰዎችን ከመለኮታዊው ዓለም ጋር እንዲያገናኝ አስችሏል ሲል ኩባንያው ገልጿል።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS