Get Mystery Box with random crypto!

የፋይናንስ ማጭበርበርን ለመከላከል ቴሌብር በዋይፋይ ኢንተርኔት እንዳይሰራ ተደረገ። የዲጂታል ክፍ | 🇪🇹 ኢትዮ Students

የፋይናንስ ማጭበርበርን ለመከላከል ቴሌብር በዋይፋይ ኢንተርኔት እንዳይሰራ ተደረገ።

የዲጂታል ክፍያና ሥርዓት እየተስፋፋ ባለበት በዚህ ወቅት የማጭበርበሪያ ስልቱም ሆነ መጠኑ እየጨመረ መጥቷል። ይህን ተከትሎ የፋይናንስ ተቋማት በተለይ በዲጂታል መተግበሪያዎቻቸውን ያዘምናሉ።

በኢትዮጵያ 36 ሚሊዮን ደንበኞች እንዳሉት ያስታወቀው ቴሌብር በደንበኞቹ ላይ የሚደርሰውን መጭበርበር ይቀርፋል ያለውን ማዘመኛ ይፋ አድርጓል። 

ማዘመኛው፥ ስልክ በመደወል፤ የፒን ቁጥርን በማታለል በመቀበልና በሌላ ስልክ በመጠቀም አካውንቱ ላይ የሚገኝ ገንዘብን በማዘዋወር የሚፈጸምን ማጭበርበር ለመግታት እንደሆነ ኢትዮ ቴሌኮም አስታውቋል።

በዚህም መሰረት፦

- ደንበኛው የራሱ ስልክ ቁጥር ባለበት የሞባይል ቀፎ ካልሆነ በስተቀር በሌላ አገልግሎት ቁጥር (ሲም ካርድ) እንዳይሰራ፣

- የራሱን ስልክ የሞባይል ዳታን በመጠቀም ካልሆነ በስተቀር በዋይፋይ ኢንተርኔት እንዳይሰራ የተደረገ መሆኑን ተቋሙ አስታውቋል፡፡

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS