Get Mystery Box with random crypto!

በዘጠነኛ ክፍል የመጀመሪያ ዲግሪ ያገኝው እስራኤል ቤሌማ 'የራሱን የስልክ መስመር ዘርግቶ ሰዎች | 🇪🇹 ኢትዮ Students

በዘጠነኛ ክፍል የመጀመሪያ ዲግሪ ያገኝው እስራኤል ቤሌማ

"የራሱን የስልክ መስመር ዘርግቶ ሰዎችን በነፃ ስልክ ሲያስጠቅም ነበር"

የተወለደው በምዕራብ ሸዋ ዞን ጊንጪ ከተማ ነው፡፡ ልጅነቱን ከእድሜ እኩዮቹ ጋር በጨዋታ ከማሳለፍ ይልቅ ከእድሜው በላይ በፈጠራ ስራዎች እና በምርምር አሳልፏል፡፡

ያኔ ገና የ7 አመት ልጅ ሳለ ከቴሌ መስመር ጋር ማይገናኝ ቤት ውስጥ መግባት የሚችል ስልክ ሰራ፡፡ የአካባቢው ህብተረሰብም በነፃ በእስራኤል ስልክ ተንበሸበሸ፡፡

ይህ ከቴሌ እውቅና ውጭ የሆነ ስልክ እንዲጣራለት ያዘዘው ቴሌ እስራኤል በፖሊስ እንዲያዝ አደረገ፡፡  ይሁን እንጂ ያገኙት ወንጀለኛ ሳይሆን ባለ ምጡቅ አዕምሮ ባለቤት የሆነውን ታዳጊ ነበር፡፡

በእስር ፈንታ ስራው ተመርምሮ እውቅና እንዲሰጠው ተደረገ፡፡ በኋላም ቴሌ በሰጠው የትምህርት እድል የዘጠነኛ ክፍሉ እስራኤል በጅማ ዩኒቨርሲቲ ከዲግሪ ተማዎች ጋር ተቀላቅሎ በመማር የመጀመሪያ ዲግሪውን ያዘ፡፡

እስራኤል ሙሉ ግዜውን በፈጠራ እና በምርምር ስራዎች ላይ የሚያሳልፍ ሲሆን ሁለት የፓተንት ፈቃድ ያስገኙለት ፈጠራዎች አሉት፡፡ ሌሎች በሂደት ላይ ያሉ ፈጠራዎች እና ምርምሮችም እንዳሉት ይናገራል፡፡

ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ለመጀመሪያ ጊዜ ባዘጋጀው የስራ ፈጠራ ውድድር ላይ ተሳትፎ የ150ሺህ ብር ተሸላሚ ሆኗል፡፡ በአሁኑ ሰዓት ኢትዮ ኢኖቬሽን ሴንተር መስራች እና ባለቤት በመሆን ለአስር ሰዎች የስራ እድል ፈጥሯል፡፡

ዘገባው የኤፍኤም አዲስ 97.1 ነው።


@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS