Get Mystery Box with random crypto!

🇪🇹 ኢትዮ Students

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiostudents — 🇪🇹 ኢትዮ Students
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiostudents — 🇪🇹 ኢትዮ Students
የሰርጥ አድራሻ: @ethiostudents
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 56.46K
የሰርጥ መግለጫ

Our Bot :
@EthioExamBot
Contact : @ethioexamsupport
Or
@Etssupport

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2023-05-04 16:29:51
ኢትዮ ቴሌኮም አዳዲስ የዲጂታል መዝናኛ አገልግሎቶችን ይፋ አደረገ

ኢትዮ ቴሌኮም የመዝናኛው ዘርፍ ዲጂታላይዝድ በማድረግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያላቸውን መተግበሪያዎች ከአጋሮቹ  ጋር በመሆን ለደንበኞች በዛሬው እለት ይፋ ማድረጉን ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል፡፡ በዛሬው ዕለት ይፋ ከተደረጉት አገልግሎቶች መካከል በሀበሻ ቪው የሚቀርበው አይፒቲቪ  ወይም ቪዲዮ ስትሪሚንግ አንዱ ነው፡፡

ይህም ደንበኞች የቀጥታ ቴሌቪዥን ፕሮግራሞች ድራማዎች ፊልሞች እንዲሁም በርካታ ሞባይል ስልካቸውን በቴሌቪዥን እንዲሁም በኮምፒውተር ለመጠቀም የሚያስችል አገልግሎት መሆኑን ተጠቁሟል፡፡

አገልግሎቱን ለማግኘት ደንበኞች የሀበሻ ቪው መተግበሪያ ወይም ድረገጽ አጭር የጽሁፍ መልዕክት ወደ 9433 A ወይም  B በመላክ የሚፈልጉትን ፓኬጅ  መመዝገብ እንዲኖርባቸውም ተገልጾል፡፡በተጨማሪም  ሰዋሰው የሙዚቃ ስትሪሚንግ ፣ ቴሌ ጌም እና ቴሌዊን የተሰኙ የሞባይል ጌሞች  በቴክኖላቭ እና አይኮኔክት ዲጂታል ሰርቪስ  ቀርበዋል፡፡

ደንበኞች በአይይኮኔክት የቀረቡትን የቴሌዊን ጨዋታዎች በቴሌዊን ድረገጽ ወይም አጭር የጽሁፍ  መልዕክት  ወደ *985# በመደወል የሚፈልጉትን  ዕለታዊ  ወይም ሳምንታዊ  ጥቅሎች በመመዝገብ ጌሞችን ሲያሸንፉ ሽልማቶችን የሚያስገኝ አገልግሎት መሆኑን ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል፡፡

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
10.5K views13:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-03 15:32:22
የ2024 ዲቪ ሎተሪ እድለኞች ከመጪው ቅዳሜ ጀምሮ ይፋ እንደሚደረጉ አሜሪካ አስታወቀች

የዲቪ 2024 ማመልከቻ የሞሉ ዜጎች መመረጣቸውን እና አለመመረጣቸውን ከፊታችን ቅዳሜ ሚያዚያ 28/2015 ጀምሮ ማወቅ እንደሚችሉ አሜሪካ አስታውቃለች።

በዚህም መሰረት፤ አመልካቾች በዲቪ ሎተሪ ድረገጽ ላይ በመግባት ያመለከቱበትን ልዩ ቁጥር ወይም ኮድ በማስገባት አሸናፊ መሆናቸውንና አለመሆናቸውን ማረጋገጥ ይችላሉ ተብሏል።

ኤምባሲው አክሎም፤ የዲቪ ሎተሪ አሸንፋችኋል፣ ከአሜሪካ ኢምባሲ ነው የምንደውለው በሚል የሚያጭበረብሩ አካላት ስለሚኖሩ አመልካቾች እንዲጠነቀቁ ያሳሰበ ሲሆን፤ የዕድሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ስለመመረጣቸውና አለመረጣቸው አመልካቾች በድቪ ሎተሪ ድረገጽ ow.ly/9E7A50O7plm ላይ በመግባት፤ በራሳቸው እጃቸው ላይ ባለው ሚስጢራዊ ቁጥር ማረጋገጥ ብቸኛው መንገድ እንደሆነም አመላክቷል።

በተጨማሪም የ2023 ድቪ ሎተሪ አሸናፊዎች፤ እስከ ቀጣዩ መስከረም 2016 ድረስ ብቻ እንደሚስተናገዱ ኢምባሲው አስታውቋል።

አሜሪካ በዓለም ላይ በየዓመቱ 50 ሺሕ ሰዎችን በ”ዳይቨርሲቲ ቪዛ“ ወይም ድቪ ሎተሪ አማካኝነት ወደ አገሯ የምታስገባ ሲሆን፤ ከእነዚህም ውስጥ የአፍሪካ፣ እስያ፣ አውሮፓ፣ ሰሜን አሜሪካ፣ ደቡብ አሜሪካ እና አውስትራሊያ ዜጎች ይገኙበታል።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
11.5K views12:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 10:34:28
#ይህንን_ያውቆ_ኖሯል

ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ ከ1997 እስከ 2018 ባሉት ዓመታት ከፍተኛ የአህያ ቁጥር እድገት ካሳዩት አስር ሀገራት አንዷ ነበረች።

በጠቅላላ የአህያ ቁጥር ደግሞ በዓለም ቀዳሚውን ስፍራ እንደምትይዝ ተመላክቷል።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
12.3K viewsedited  07:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-27 20:07:13 "የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ መልቀቂያ ፈተና ሃምሌ ወር ላይ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ይሰጣል" - ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ከዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶችና  ከክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች ጋር በ2015 ዓም. የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በሚመለከት  ውይይት አካሄዷል፡፡

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ  ፈተና ሃምሌ ወር ላይ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንደሚሰጥ ገልጸዋል፡፡ፈተናው ልክ እንደባለፈው አመት በሁለት ዙር የሚሰጥ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በመጀመሪያው ዙር የነበሩ የፈተና ችግሮችን ዘርዝረው ለቀጣዩ የመፍትሄ አቅጣጫ ማስቀመጥና ቅድመ ዝግጅት ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን በአጽንኦት አሳስበዋል፡፡

ሚኒስትሩ የህብረተሰቡን ችግር ለመቅረፍና አመለካከቱን ለመቀየር፣ ብቁና አገር ተረካቢ ትዉልድ ለመፍጠር አሁን ያለው ባለድርሻ አካል ሚናውን ሊወጣ ይገባል ሲሉም ተናግረዋል፡፡በ2016 ዓ.ም የሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ  ፈተና እንደአካባቢው ሁኔታ ኦን ላይን እንደሚሆን ገልጸዋል ።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) በበኩላቸው የ2015 ዓ.ም ፈተናን ለማስፈፀም ልዩ ልዩ መመሪያዎች እየተዘጋጁ መሆኑንና የተፈታኞች መረጃ በአግባቡ እየተደራጀ መሆኑን  ገልጸዋል።

[የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት]

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
14.5K views17:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-27 09:44:12
#Reminder

የ2015 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የተማሪዎች ምዝገባ ነገ ሚያዝያ 20/2015 ዓ.ም ይጠናቀቃል።

ምዝገባው ከመጋቢት 20/2015 ዓ.ም ጀምሮ በኦንላይን ሲከናወን መቆየቱ ይታወቃል።

ከሚያዚያ 20/2015 ዓ.ም በኋላ በግለሰብም ሆነ በተቋም የሚመጡ ተመዝጋቢዎችን እንደማያስተናግድ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ማሳወቁ አይዘነጋም።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
317 views06:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-24 17:22:45
በአሜሪካ ቴክሳስ ሞተ ተብሎ ቤተሰቦቹ አስክሬኑን የተሰናበቱት የ 16 አመቱ ልጅ መነሳቱ ግርምት ፈጥሯል።

የ16 ዓመቱ አሜሪካዊ ሳሚ በጂም ውስጥ እየዘለለ ሳለ እያለ በድንገት ልቡ ቆመ።

ሐኪሞች ልቡን በማሽን ለማስነሳት ለሁለት ሰዓታት ቢሞክሩም አልተሳካም።

በሐዘን የተጨነቁ ወላጆች መሰናበት ጀመሩ። የወጣቱ እናት ምን ያህል እንደምትወደው እያለቀሰች ሞተ ላለችው ልጇ አስከሬኑ አጠገብ ተናግራ ተለየች ።

ከአምስት ደቂቃ በኋላ ሳሚ በተአምራዊ ሁኔታ ተንቀሳቀሰ ። ቤተሰቦቹም ሐኪሞቹም ዓይናቸውን ማመን አልቻሉም ሲል ኢንዲያን ታይምስ ከሰሞኑ አስነብቧል።

ታዳጊው ወንድሙ ቀደም ብሎ እንዲሞት ባደረገው ብርቅዬ የዘረመል የልብ ህመም ታሞ እንደነበር ታውቋል።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
848 viewsedited  14:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-23 02:39:38
ኦንላይን የኮምፕዩተር ኮርሶችን በመከታተል የቴክኖሎጂ እውቀትዎን ያሳድጉ።

የቴክኖሎጂ ምክሮች
ስልጠናዎች
ጥያቄዎች
የቴክኖሎጂ ዜና

አሁኑኑ ይመዝገቡ
1.8K views23:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-22 21:16:18
በቻይና አንድ ኩባንያ ለሰራተኞቹ ባወጣው ዕጣ አንድ ሰራተኛ አመቱ ሙሉ ደሞዝ እየተከፈለው የአንድ አመት ዕረፍት የሚያሰጥ እጣ አሸናፊ ሆኗል።

እንዲህ ያለ ዕጣ ቁጭ ብሎ መብላትን የሚያበረታታ ነው የሚል ከፍተኛ ትችት በማህበራዊ ሚዲያ ቀርቦበታል።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
3.3K viewsedited  18:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 14:19:07
ትዊተር በክፍያ ምክንያት የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይን ጨምሮ የታዋቂ ግለሰቦችን ሰማያዊ ምልክት ማንሳት ጀመረ

ትዊተር ከትላንት ጀምሮ በሺዎች የሚቆጠሩ ታዋቂ ሰዎችን ሰማያዊ ማረጋገጫ ምልክት ማንሳት ጀምሯል።

ላብነትም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህምድ ፣ የአሜሪካዉ ፕሬዝዳንት ጆ ባንደን ፣ ክርስቲያኖ ሮናልዶ፤ ኪሊያን ምባፔ፤ ሰሊና ጎሜዝ ፤ቢዮንሴ፤ አቡነ ፍራንሲስን ጨምሮ በርካታ የተዋቂ ሰዎች አጠገብ ያለውን 'ሰማያዊ ምልክት' አንስቷል።

ግለሰቦቹ ትክክለኛ ገጻቸው እንደሆነ ለማወቅ የሚረዳው ሰማያዊ ምልክት ለማግኘት በዓመት 84 ዶላር እንደሚያስከፍል ትዊተር መግለጹ አይዘነጋም። ክፍያው ካልተፈጸመ ሰማያዊ ምልክት እንደሚነሳ በቅርቡ አሳውቆ ነበር።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
3.5K views11:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 18:34:53
የሸዋል ወር ጨረቃ በሳኡዲ አረበያ ዛሬ ሀሙስ በመታየቷ የዒድ አልፈጥር በዓል ነገ ጁምዓ / አርብ ይውላል።

እንኳን 1 ሺህ 444ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

ምንጭ፦ Haramain Sharifain

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
3.2K viewsedited  15:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ