Get Mystery Box with random crypto!

'የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ መልቀቂያ ፈተና ሃምሌ ወር ላይ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ይሰጣል' - ፕሮፌሰር | 🇪🇹 ኢትዮ Students

"የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ መልቀቂያ ፈተና ሃምሌ ወር ላይ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ይሰጣል" - ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ከዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶችና  ከክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች ጋር በ2015 ዓም. የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በሚመለከት  ውይይት አካሄዷል፡፡

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ  ፈተና ሃምሌ ወር ላይ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንደሚሰጥ ገልጸዋል፡፡ፈተናው ልክ እንደባለፈው አመት በሁለት ዙር የሚሰጥ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በመጀመሪያው ዙር የነበሩ የፈተና ችግሮችን ዘርዝረው ለቀጣዩ የመፍትሄ አቅጣጫ ማስቀመጥና ቅድመ ዝግጅት ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን በአጽንኦት አሳስበዋል፡፡

ሚኒስትሩ የህብረተሰቡን ችግር ለመቅረፍና አመለካከቱን ለመቀየር፣ ብቁና አገር ተረካቢ ትዉልድ ለመፍጠር አሁን ያለው ባለድርሻ አካል ሚናውን ሊወጣ ይገባል ሲሉም ተናግረዋል፡፡በ2016 ዓ.ም የሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ  ፈተና እንደአካባቢው ሁኔታ ኦን ላይን እንደሚሆን ገልጸዋል ።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) በበኩላቸው የ2015 ዓ.ም ፈተናን ለማስፈፀም ልዩ ልዩ መመሪያዎች እየተዘጋጁ መሆኑንና የተፈታኞች መረጃ በአግባቡ እየተደራጀ መሆኑን  ገልጸዋል።

[የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት]

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS