Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮ ቴሌኮም አዳዲስ የዲጂታል መዝናኛ አገልግሎቶችን ይፋ አደረገ ኢትዮ ቴሌኮም የመዝናኛው ዘርፍ | 🇪🇹 ኢትዮ Students

ኢትዮ ቴሌኮም አዳዲስ የዲጂታል መዝናኛ አገልግሎቶችን ይፋ አደረገ

ኢትዮ ቴሌኮም የመዝናኛው ዘርፍ ዲጂታላይዝድ በማድረግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያላቸውን መተግበሪያዎች ከአጋሮቹ  ጋር በመሆን ለደንበኞች በዛሬው እለት ይፋ ማድረጉን ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል፡፡ በዛሬው ዕለት ይፋ ከተደረጉት አገልግሎቶች መካከል በሀበሻ ቪው የሚቀርበው አይፒቲቪ  ወይም ቪዲዮ ስትሪሚንግ አንዱ ነው፡፡

ይህም ደንበኞች የቀጥታ ቴሌቪዥን ፕሮግራሞች ድራማዎች ፊልሞች እንዲሁም በርካታ ሞባይል ስልካቸውን በቴሌቪዥን እንዲሁም በኮምፒውተር ለመጠቀም የሚያስችል አገልግሎት መሆኑን ተጠቁሟል፡፡

አገልግሎቱን ለማግኘት ደንበኞች የሀበሻ ቪው መተግበሪያ ወይም ድረገጽ አጭር የጽሁፍ መልዕክት ወደ 9433 A ወይም  B በመላክ የሚፈልጉትን ፓኬጅ  መመዝገብ እንዲኖርባቸውም ተገልጾል፡፡በተጨማሪም  ሰዋሰው የሙዚቃ ስትሪሚንግ ፣ ቴሌ ጌም እና ቴሌዊን የተሰኙ የሞባይል ጌሞች  በቴክኖላቭ እና አይኮኔክት ዲጂታል ሰርቪስ  ቀርበዋል፡፡

ደንበኞች በአይይኮኔክት የቀረቡትን የቴሌዊን ጨዋታዎች በቴሌዊን ድረገጽ ወይም አጭር የጽሁፍ  መልዕክት  ወደ *985# በመደወል የሚፈልጉትን  ዕለታዊ  ወይም ሳምንታዊ  ጥቅሎች በመመዝገብ ጌሞችን ሲያሸንፉ ሽልማቶችን የሚያስገኝ አገልግሎት መሆኑን ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል፡፡

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS