Get Mystery Box with random crypto!

የ2024 ዲቪ ሎተሪ እድለኞች ከመጪው ቅዳሜ ጀምሮ ይፋ እንደሚደረጉ አሜሪካ አስታወቀች የዲቪ 20 | 🇪🇹 ኢትዮ Students

የ2024 ዲቪ ሎተሪ እድለኞች ከመጪው ቅዳሜ ጀምሮ ይፋ እንደሚደረጉ አሜሪካ አስታወቀች

የዲቪ 2024 ማመልከቻ የሞሉ ዜጎች መመረጣቸውን እና አለመመረጣቸውን ከፊታችን ቅዳሜ ሚያዚያ 28/2015 ጀምሮ ማወቅ እንደሚችሉ አሜሪካ አስታውቃለች።

በዚህም መሰረት፤ አመልካቾች በዲቪ ሎተሪ ድረገጽ ላይ በመግባት ያመለከቱበትን ልዩ ቁጥር ወይም ኮድ በማስገባት አሸናፊ መሆናቸውንና አለመሆናቸውን ማረጋገጥ ይችላሉ ተብሏል።

ኤምባሲው አክሎም፤ የዲቪ ሎተሪ አሸንፋችኋል፣ ከአሜሪካ ኢምባሲ ነው የምንደውለው በሚል የሚያጭበረብሩ አካላት ስለሚኖሩ አመልካቾች እንዲጠነቀቁ ያሳሰበ ሲሆን፤ የዕድሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ስለመመረጣቸውና አለመረጣቸው አመልካቾች በድቪ ሎተሪ ድረገጽ ow.ly/9E7A50O7plm ላይ በመግባት፤ በራሳቸው እጃቸው ላይ ባለው ሚስጢራዊ ቁጥር ማረጋገጥ ብቸኛው መንገድ እንደሆነም አመላክቷል።

በተጨማሪም የ2023 ድቪ ሎተሪ አሸናፊዎች፤ እስከ ቀጣዩ መስከረም 2016 ድረስ ብቻ እንደሚስተናገዱ ኢምባሲው አስታውቋል።

አሜሪካ በዓለም ላይ በየዓመቱ 50 ሺሕ ሰዎችን በ”ዳይቨርሲቲ ቪዛ“ ወይም ድቪ ሎተሪ አማካኝነት ወደ አገሯ የምታስገባ ሲሆን፤ ከእነዚህም ውስጥ የአፍሪካ፣ እስያ፣ አውሮፓ፣ ሰሜን አሜሪካ፣ ደቡብ አሜሪካ እና አውስትራሊያ ዜጎች ይገኙበታል።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS