Get Mystery Box with random crypto!

🇪🇹 ኢትዮ Students

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiostudents — 🇪🇹 ኢትዮ Students
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiostudents — 🇪🇹 ኢትዮ Students
የሰርጥ አድራሻ: @ethiostudents
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 56.17K
የሰርጥ መግለጫ

Our Bot :
@EthioExamBot
Contact : @ethioexamsupport
Or
@Etssupport

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 11

2023-04-17 13:37:39
ስጋ ከድመት ለማስጣል የሞከረችው የ18 ዓመት ወጣት ለሞት ተዳረገች፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ በአቃቂ ቃሊት ክፍለ ከተማ አለም ባንክ አካባቢ ስጋ ይዛ ጣራ ላይ የወጣችን ድመት ለማውረድ የሞከረችው የ18 አመት እድሜ የሆናት ሴት በደረሰባት የኤልክትሪክ አደጋ ህይወቷ ማለፉ ታውቋል፡፡
ወጣቷ በድመት የተወሰደባትን ስጋ ለማስጣል በሞከረችበት ጊዜ ነው በኤልክትሪክ ምክንያት ህይወቷ ያለፈው ተብሏል፡፡

በአጠቃላይ በበአሉ ቀን እና በዋዜማው እለት የሶስት ሰዎች ህይወት ማለፉ የነገረ ሲሆን ከትራፊክ አደጋ ጋር በተያያዘም በዋዜማው ሁለት የሞት አደጋ መድረሳቸው ተነግሯል፡፡
ከበአሉ ጋር በተያያዘ የከፋ የጸጥታ ችግር ባያጋጥምም በጸም ምክንያት ግን የአንድ ሰው ህይወት ማለፉን በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ የሆኑት ምክትል ኮማንደር  ማርቆስ ታደሰ ተናግረዋል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግኑኝነት ሃላፊ ም/ኮምማንደር ማርቆስ ታደሰ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ባልደራስ አካባቢ በተከሰተ አለመግባባት የአንድ ሰው ህይወት አልፋል ብለዋል፡፡
ከዚህ ግድያ ጋር በተያያዘም የተጠረጠሩ እስካሁን ድረስ 8 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ነው የተገለጸው፡፡
ፖሊስ አሁንም ከግድያው ጋር በተያያዘ ምርምራ እያካሄደ እንደሚገኝም ጨምረው ገልጸዋል፡፡

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
3.2K views10:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-16 09:03:27
የይለፍ ቁጥሩ ስንት ነው?

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
3.0K viewsedited  06:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 20:54:33
የማሌዢያ ነዋሪ የሆነች በህልሟ ያየችውን ሎተሪ ቁጥር በመቁረጥ አራት ሚልየን ዶላር አሸንፋለች ።


የ54 ዓመቷ ሴት ሁለት ባለአራት አሃዝ ቁጥሮችን 3887 እና 5785 በህልሟም አይታ በእውነታው ስታያቸው ገዝታቸዋለች ሲል ማሌይ ሜይል ዘግቧል።

ከ 15 ቀን በፊት በወጣው የ ማግነም 4D ጃክፖት ጨዋታ የእጣ ድልድል ቁጥሯ ከሶስቱ አሸናፊ ቁጥሮች ሁለቱ ነበሩ።

ገንዘቡን ከቤተሰቦቿ ጋር ለረጅም ጊዜ በጉጉት ለሚጠበቀው ጉዞ፣ ቤት እና በጎ አድራጎት ስራ አውለዋለው ብላለች።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
4.4K viewsedited  17:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 13:27:16
የ1 GB የኢንተርኔት ዳታ ስጦታ ከኢትዮ ቴሌኮም

ኢትዮ ቴሌኮም የስቅለት በአልን ምክንያት በማድረግ የ1 GB የኢንተርኔት ዳታ አገልግሎት ስጦታ ለደንበኞቹ አበርክቷል።

የትንሳኤን ጥቅል ገዝታችሁ ስትጠቀሙ 1GB ነፃ ታገኛላችሁ

ይሁንና እንደ ፌስቡክ፣ ቴሌግራምና ዩትዩብ የመሳሰሉ የማኅበራዊ መገናኛዎች ላይ የተጣለው ክልከላ ዛሬም ባለመነሳቱ ደንበኞች ስጦታውን መጠቀም የሚችሉት "በቪፒኤን" በመግባት ብቻ ነው።
6.6K viewsedited  10:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-09 20:22:11 የሬሚዳል ፕሮግራምን ለመከታተል የመመዝገቢያ ነጥብ በመንግስት እና በግል ዩኒቨርሲቲዎች ይለያያል?


ትምህርት ሚኒስቴር ከ50 በመቶ በታች ያመጡ የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች የሬሚዳል ፕሮግራምን በተለያዩ አማራጮች እንዲከታተሉ የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ማድረጉ አይዘነጋም።

የመቁረጫ ነጥቡ ለታዳጊ እና አርብቶ አደር ባልሆኑ ክልሎች የተፈጥሮ ሳይንስ  ተማሪዎች ለወንድ 263 ከ700 ለሴት ደግሞ 227 ሲሆን ለማህበራዊ ሳይንስ ለወንድ 220 ከ600 እንዲሁም ለሴት 190 ከ600 መሆኑን ማሳወቁም የሚታወስ ነው።

በዚህ የሬሚዳል መቁረጫ ነጥብ መሰረት ባደረግነው ምልከታ ከተቀመጠው ነጥብ #በታች ያመጡ ተማሪዎችን የሚመዘግቡ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መሆራቸውን አይተናል።
ምዝገባውን እያከናወነ ላለው ዩኒቨርሲቲ እና ኮሎጁ ትምህርት ሚኒስቴር ካስቀመጠው ነጥብ በታች ያመጡ ተማሪዎችን ለምን መዘገባችሁ? በሚል ላቀረብንላቸው ጥያቄ መንግሥት ይፋ ያደረገው ለመንግሥት ዩኒቨርስቲዎች እንጂ ለግል ተቋማት አይደለም ሲሉ ምላሽ ሰጥተውናል።

አል ዓይን ይህን ጥያቄ ይዞ ትምህርት ሚኒስቴርን የጠየቀ ሲሆን የሚኒስቴሩ የህዝብ ግንኙነት እና ኮሙንኬሽን ሀላፊ ወይዘሮ አመለወርቅ እዝቅኤል፥ "ለሬሚዳል ፕሮግራምም ይሁን ከ50 በመቶ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች መመዝገቢያ ነጥብ ለመንግሥትም ይሁን ለግል ዩኒቨርሲቲ ተመሳሳይ ነው" ሲሉ ተናግረዋል ።

ከዚህ በፊት የነበረው ለግል እና ለመንግሥት ዩኒቨርስቲዎች የተማሪዎች መመዝገቢያ ነጥብ ይለያይ ነበር ያሉት ሀላፊዋ፥ ከ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና በኋላ ተመሳሳይ እንዲሆን መወሰኑን አክለዋል።
በዚህም መሰረት ትምህርት ሚኒስቴር ካስቀመጠው የሬሚዳል ፕሮግራም መመዝገቢያ ነጥብ ውጪ የሚመዘግቡ ዩኒቨርስቲዎች እና ኮሌጆች ህግ እየጣሱ መሆኑንና እርምጃም እንደሚወሰድባቸው ነው ያብራሩት።


ምንጭ፡አልዓይን

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
4.8K views17:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-03 06:59:04
በአዲስ አበባ ትላንት ምሽት በደረሰ የእሳት አደጋ ሁለት መኖሪያ ቤቶችና 10 የንግድ ሱቆች  ወደሙ

በአዲስ አበባ ትላንት ምሽት በደረሰ የእሳት አደጋ አንድ የእሳት አደጋ ሰራተኛን ጨምሮ በሶስት ሰዎች ላይ ቀላል ጉዳት መድረሱን የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።

ትላንት ካቲት 23 ቀን 2015 ከምሽቱ 12:36 ሰዓት በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ጉርድ ሾላ ንግድ ባንክ ጀርባ በደረሰ የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ውድመት ደርሷል።

በእሳት አደጋዉ ሁለት መኖሪያ ቤቶችና 10 የንግድ ሱቆች  የተቃጠሉ ሲሆን አንድ የእሳት አደጋ ሰራተኛን ጨምሮ በሶስት ሰዎች ላይ ቀላል ጉዳት መድረሱን የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል።

የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠር 13 የእሳት አደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪዎች አንድ የዉሀ ቦቴ ሶስት አንፑላንስና 103 የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ተሰማርተዋል።

አስቀድም የተስፋፋዉ የእሳት አደጋ ወደ አካባቢዉ ተዛምቶ ተጨማሪ ጉዳት ሳያደርስ ባለበት ለመቆጣጠር የተቻለ ሲሆን የእሳት አደጋዉን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር 2:35 ሰዓት ፈጅቷል።

@ETHIOSTUDENTS @ETHIOSTUDENTS
4.3K views03:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-01 14:52:52
#Update

የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስደው ወደ ቴክኒክና ሞያ ተቋማት የሚገቡ ሰልጣኞች የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ተደረገ፡፡


በዚህም መሰረት በደረጃ 5 የመግቢያ መቁረጫ ነጥቡ በተፈጥሮ ሳይንስ ወንዶች 246 እና ከዚያ በላይ ፣ ለሴቶች 218 እና ከዚያ በላይ ሆኗል፡፡

ለታዳጊ ክልሎችና አርብቶ አደር አካባቢዎች ለወንዶች 203 እና ከዚያ በላይ ለሴቶች 202 እና ከዚያ በላይ ሆኖ ተቆርጧል፡፡

ለሁሉም ክልል አካል ጉዳተኞች የመቁረጫ ነጥብ 149 እኛ ከዚያ በላይ ሆኗል፡፡

ለማህበራዊ ሳይንስ በደረጃ 5 ለወንዶች 203 እና ከዚያ በላይ ለሴቶች 179 እና ከዚያ በላይ ሆኗል፡፡

ለታዳጊ ክልልና አርብቶ አደር አካባቢዎች ለወንዶች 173 እና ከዚያ በላይ ፣ ለሴቶች 171 እና ከዚያ በላይ ሲሆን ለሁሉም ክልል አካል ጉዳተኞች የመግቢያ ነጥቡ 149 እና ከዚያ በላይ ሆኗል፡፡

ለደረጃ 3 እና 4 እንዲሁም የደረጃ 1 እና 2 የመግቢያ ነጥብ ተቆርጦ ይፋ ተደርጓል፡፡

የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ስልጠና እስካሁን ከደረጃ 1 እስከ 5 ተከፋፍሎ ይሰጥ የነበረ ሲሆን በአዲሱ ፖሊሲ መሰረት እስከ ደረጃ 8 ድረስ ከፍ ተደርጎ መሰናዳቱ ተሰምቷል፡፡

ይህም ደረጃ 6 ከመጀመሪያ ዲግሪ ፣ ደረጃ 7 ከሁለተኛ ዲግሪ እንዲሁም ደረጃ 8 ከሶስተኛ ደረጃ አቻ ነው ተብሏል፡፡

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
2.6K views11:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-26 22:32:34 የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ምደባ ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ምደባ ይፋ ሆነ።

በ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋም ምደባቸውን ከዛሬ ጀምሮ ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ማየት የሚችሉ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቋል።

በዚህም መሠረት ተማሪዎቹ በተመደቡበት የትምህርት ተቋሞች በሚያስተላልፉት ጥሪ መሰረት የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራሙን እንዲከታተሉ አሳስቧል።

የተቋም ይቀየርልኝ ጥያቄንም የማያስተናግድ መሆኑን አስታውቋል።

የተመደቡበትን ተቋም ለማየት የቀረቡ አማራጮች

Website:

https://placement.ethernet.edu.et
SMS: 9444

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
2.7K viewsedited  19:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-13 16:36:26
#Update የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች እና በተለያዩ አማራጮች ለመከታተል የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ተደረገ። የትምህርት ሚኒስቴር በ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና  ወስደው 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያመጡትን ከግምት ውስጥ በማስገባት እና በተመሳሳይ ሁኔታ ፈተናው የተሰጠበትን አግባብ እና ሌሎች ጉዳዮችን ከግምት በመውሰድ ለአንድ…
3.8K views13:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-13 16:34:49 #Update

የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች እና በተለያዩ አማራጮች ለመከታተል የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ተደረገ።

የትምህርት ሚኒስቴር በ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና  ወስደው 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያመጡትን ከግምት ውስጥ በማስገባት እና በተመሳሳይ ሁኔታ ፈተናው የተሰጠበትን አግባብ እና ሌሎች ጉዳዮችን ከግምት በመውሰድ ለአንድ ጊዜ ብቻ  የሚያገለግል የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) እንዲተገበር መወሰኑ ይታወቃል።

በዚሁ መሰረት በ2015 የትምህርት ዘመን ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ገብተው በ Remedial ፕሮግራም የሚከታተሉ ተማሪዎችን አነስተኛ የመግቢያ ውጤት መወሰን አስፈላጊ በመሆኑ 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያላስመዘገቡ ነገር ግን ከላይ የተዘረዘሩትን የሚያሟሉ ተማሪዎች የ Remedial ፕሮግራም ተጠቃሚዎች ይሆናሉ ።

1. በሁሉም አማራጮች (በግል እና በመንግስት ተቋማት) የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል ተማሪዎች እንደተፈተኑት የትምህርት አይነት ብዛት 30% ከመቶ እና ከዚያ በላይ ማለትም (210 ከ 700፣  180 ከ 600 እና 150 ከ 500) የተቆረጠ መሆኑን።

2. ከላይ በተራ ቁጥር 1 የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ  በመንግስት ተቋማት(ወጪያቸው በመንግስት ተሸፍኖ) የ Remedial ፕሮግራም የሚከታተሉት የሚከተሉትን መቁረጫ ነጥብ ያሟሉ ብቻ ይሆናል ተብሏል።

(የአቅም ማሻሻያ የመቁረጫ ነጥቡን ከላይ ይመልከቱ)

ምንጭ፦ ትምህርት ሚኒስቴር

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
3.7K views13:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ