Get Mystery Box with random crypto!

🇪🇹 ኢትዮ Students

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiostudents — 🇪🇹 ኢትዮ Students
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiostudents — 🇪🇹 ኢትዮ Students
የሰርጥ አድራሻ: @ethiostudents
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 56.46K
የሰርጥ መግለጫ

Our Bot :
@EthioExamBot
Contact : @ethioexamsupport
Or
@Etssupport

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2023-04-19 21:36:38
ትላንት የቱርኳ ኢስታንቡል ቀን ላይ በድንገት እስከ አስር ኪሎ ሜትር በሚሸፍን ግዙፍ ጥቁር ደመና ተሸፍና ነበር ። ፀሐይ ለ5 ደቂቃ ያህል አልታየችም ። ከተማዋ እንደ ሌሊት ጨለማ ሆና ነበር።

ቪዲዮው ከማህበራዊ ሚዲያ የተገኘ ነው።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
6.0K viewsedited  18:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 19:37:12
40 ሺ ብር የወጣበት ሰንጋ 53ሺ ብር የሚያወጣ ወርቅ ሆዱ ውስጥ ተገኘ።

በአርሲ ዞን ጢዮ ወረዳ ዶንሾ ቀበሌ  ለበዓል  ከታረደ ሰንጋ ሆዱ ውስጥ   18.5  ግራም ወርቅ ተገኝቷል። ቀድመው ከብቱን ለመግዛት 40 ሺህ ብር ያወጡት ሸማቾቹ በምትኩ የተገኘውን ወርቅ ደግሞ 53 ሺህ ብር በመሸጥ  ባገኙት ገንዘብ ሌላ ስንጋ ለመግዛት ቀጠሮ ይዘዋል ሲል የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ (obn) ዘግቧል። 

ይህ ነገር በሳይንስ እንዴት ይታያል ለሚለው ጥያቄ በኦሮሚያ ግብርና ቢሮ አሰላ የሚገኘው የእንስሳት ጤና ጥበቃ ማዕከላዊ የእንስሳት ጤና ጥበቃ የእንስሳት ሐኪም በሰጡት አስተያየት "በረሃማ አካባቢ የሚኖሩ ከብቶች ትንንሽ ማዕድናት ያላቸውን ተክሎች ስለሚመገቡ ከቆይታ ብዛት ወደ  ወርቅ ይለወጣል ብለዋል።"

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
3.8K views16:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 14:59:50 በሱዳን ኦምዱርማን ከተማ የአንድ ቤተሰብ አባል የሆኑ አራት ኢትዮጵያዊያን ተገደሉ

በጦርነቱ በካርቱም የኢትዮጵያ ኤምባሲ ላይ ጥቃት ደርሷል


አራተኛ ቀኑን በያዘዉ የሱዳን የከተማ ዉስጥ ጦርነት የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሀይል እና የሀገሪቱ ጦር ዉግያ ዉስጥ ይገኛሉ። በርካታ ኢትዮጵያዊያን መኖሪያ በሆነችዉ ሱዳን ኢትዮጵያዊንም ህይወታቸዉ እንዳለፈ ተሰምቷል።

በሱዳን 12 አመታትን የቆየዉና አስተያየቱን የብስራት ራዲዮ ምንጭና የጤና ባለሙያዉ አቶ ወንድወሰን ጌትነት ፤ ከትናንት በስቲያ 11 ሰዓት ከ 30 አካባቢ ኦምዱርማን በተሰኘዉ አካባቢ በጦርነቱ የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ አራት ኢትዮጵያዊያን በጦር ጄት ጥቃት ህይወታቸው ማለፉን ተናግሯል። እስካሁን ከ 10 በላይ ኢትዮጵያዊያን በጦርነቱ ሞተዋል ያለን አስተያየት ሰጪያችን ፤ በትናትናዉ እለት በካርቱም ( ጅሬፍ ) በደረሰ ሌላ ጥቃት ፤ ባለትዳሮች ህይወታቸውን ሲያጡ የሶስት አመት ህጻን ልጃቸዉ ከጥቃቱ ተርፏል ብሏል።

በተጨማሪም በካርቱም የኢትዮጵያ ኤምባሲ ላይም ጥቃት መድረሱን ገልጿል። የትኞቹ ታጣቂዎች እንደፈጸሙት ባያረጋግጥልንም የኤምባሲዉን ቅጥርግቢ ጥሰዉ በመግባት በግቢዉ በሱዳን የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ባለቤት በሆነበት የመጠለያ ማዕከል ዉስጥ በነበሩ ኢትዮጵያዊያን ላይ አጸያፊ ተግባራት ጭምር መፈጸማቸዉን ተናግሯል።

የኤምባሲዉ ጥበቃዎች በጦርነቱ ወቅት ከግዳጅ ቦታቸዉ በመነሳታቸዉ የተባለዉ ጥቃት ደርሷል። ታጣቂዎቹም ገንዘብን ጨምሮ ዘረፋ መፈጸማቸዉን ነዉ የተናገረዉ።

በሱዳን ያለዉ ሁኔታ አስከፊ መሆኑን የገለጸልን የመረጃ ምንጭ በዋና ከተማዋ ካርቱም ከፍተኛ ዝርፊ መስፈኑንም ጨምሮ ለብስራት ራዲዮ ተናግሯል። ብስራት ራዲዮ በካርቱም የኢትዮጵያ ኤምባሲን ለማግኘት ሙከራ እያደረገ ነዉ።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
4.7K views11:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 12:44:13 ልዩ አዲስ ነገርይሄን ሳይሰሙ እንዳያልፉ

በዚህ ሰዓት ሁላችንም ቤት ውስጥ የምንፈልገው አንድ ነገር አለ፡፡ እሱም ቋሚ ስራና  ገንዘብ ማግኘት ፡፡

እየተማርኩ መስራት እፈልጋለሁ ግን ምን ልስራ

ተመርቄያለሁ ግን ስራ የለኝም

ነጋዴ ነኝ ግን ስራ ስለቀዘቀዘ ብዙ ውጣ ውረድ ውስጥ እገኛለሁ

ኦንላይን ስራ መስራት እፈልጋለሁ ግን አሰራሩን አልቻልኩም

እቃዎችን ገዝቶ መሸጥ በጣም ጎበዝ ነኝ ግን መነሻ ካፒታል የለኝም

እነዚህን እና መሰል ጥያቄዎችዎን በሚፈልጉት ሁኔታ በታላቅ ጥራት ይዘን መጥናል ፡፡ ከእርስዎ የሚጠበቀው ይሄን ቻናል በመቀላቀል ከእኛ ጋር መስራት ብቻ ነው ፡፡

https://t.me/ezonlinebusiness1
https://t.me/ezonlinebusiness1
989 views09:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 10:00:02    Nova-ChatGPT AI-ChatBot | ማንኛውንም ጥያቄ ያለምንም ክፍያ የሚመልስ አፕ

Mod Features :

UNLOCK PREMIUM
  - Math ጥያቄ ያለምንም ስህተት ይሰራል
- አለም ላይ ያሉ ሁሉንም ጥያቄዎች ይመልሳል ።
- App Code ያደርጋል ።
REMOVED ADS 

UNLOCK FEATURE VIP 
- ሁሉም Features ክፍት ናቸው።
UNLIMITED CREDITS % 
ነፃ አገልግሎት

ይጠቅማችኋል

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
2.0K viewsedited  07:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 09:04:18 ለፋሲካ በዓል ልብስ አልተገዛልኝም በሚል ያኮረፈዉ ወጣት ራሱን አጠፋ


በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን ደቡብ አሪ ወረዳ ለበዓል ልብስ አልተገዛልኝም በሚል ከቤተሰቦቹ ተጨቃጭቆ መግባባት ያልቻለዉ  ወጣት በገመድ እራሱን ሰቅሎ ህይወቱን ማጥፋቱ በደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የሚዲያ ክፍል ኃላፊ ምክትል ኮማንደር ታጁ ነጋሽ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።


በደቡብ አሪ ወረዳ ባላመር ቀበሌ ነዋሪ የሆነዉ   ይህ ወጣት ለ2015  ዓ.ም የትንሳኤ  በዓል ልብስ እንዲገዛለት ለወላጆቹ ጥያቄ ያቀርብላቸዋል።

ወላጆቹምኃ ቀደም ሲል የሚለብሳቸዉ ልቦሶች አፅድቶ በመልበስ የዘንድሮዉን በዓል አክብሮ እንዲዉልና በሱ ጥያቄ ሳይሆን አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ አዳዲስ ልብሶችን ቤተሰብ ይገዛልሀል የሚል ተስፋ አስቆራጭ ምላሽ ይሰጠዋል።  ይህ  ወጣት በወላጆቹ እምቢታ ተናዶ እራሱን እንደሚያጠፋ ዝቶ ከቤተሰቦቹ ጋር ከስምምነት ሳይደርስ ይለያያል።

ወጣቱ እራሱን ለማጥፋት ቢዝትም ቤተሰብ እንዲህ አይነቱ ተግባር ሊፈፅም ይችላል የሚል ጥርጣሬ ባይኖራቸውም ሚያዝያ 08 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 12:00 ሰዓት ላይ  ወጣቱ እራሱን በገመድ ሰቅሎ  ህይወቱ ማለፉን ኮማንደር ታጁ ነጋሽ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
2.5K views06:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 00:18:42
#Update

በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስዳችሁ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገባችሁና በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ መንግስት የተሰጠውን ነፃ የትምህርት ዕድል (ስኮላርሺፕ) እየተጠባበቃችሁ ያላችሁ ተማሪዎች በተከታዩ ሊንክ አማካይነት የማመልከቻ ፎርሙን መሙላት ትችላላችሁ፦

http://survey.ethernet.edu.et/index.php/518562?lang=en

የማመልከቻ ፎርሙን መሙላት የሚቻለው ከዛሬ ሚያዝያ 09 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ተከታታይ አምስት ቀናት ብቻ መሆኑ ተገልጿል።

በማመልከቻ ፎርሙ ልትሞሏቸው የሚገቡ፦

➧ የ12ኛ ክፍል ውጤት ኮፒ፣
➧ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ኮፒ፣
➧ ግለ ታሪክ (CV) ኮፒ፣
➧ የልደት የምስክር ወረቀት ኮፒ እና
➧ ሌሎች በፎርሙ የተጠቀሱ መረጃዎች።

መረጃዎቹ ተጣርተው ለፈተና የሚቀረቡ ተማሪዎችን ዝርዝር በቀጣይ እንደሚያሳውቅ የትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
4.1K views21:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-17 20:23:23 ልዩ አዲስ ነገርይሄን ሳይሰሙ እንዳያልፉ

በዚህ ሰዓት ሁላችንም ቤት ውስጥ የምንፈልገው አንድ ነገር አለ፡፡ እሱም ቋሚ ስራና  የተረጋጋ ህይዎት መኖር ነው ፡፡

እየተማርኩ መስራት እፈልጋለሁ ግን ምን ልስራ

ተመርቄያለሁ ግን ስራ የለኝም

ነጋዴ ነኝ ግን ስራ ስለቀዘቀዘ ብዙ ውጣ ውረድ ውስጥ እገኛለሁ

ኦንላይን ስራ መስራት እፈልጋለሁ ግን አሰራሩን አልቻልኩም

እቃዎችን ገዝቶ መሸጥ በጣም ጎበዝ ነኝ ግን መነሻ ካፒታል የለኝም

እነዚህን እና መሰል ጥያቄዎችዎን በሚፈልጉት ሁኔታ በታላቅ ጥራት ይዘን መጥናል ፡፡ ከእርስዎ የሚጠበቀው ይሄን ቻናል በመቀላቀል ከእኛ ጋር መስራት ብቻ ነው ፡፡

https://t.me/ezonlinebusiness1
https://t.me/ezonlinebusiness1
587 views17:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-17 13:37:39
ስጋ ከድመት ለማስጣል የሞከረችው የ18 ዓመት ወጣት ለሞት ተዳረገች፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ በአቃቂ ቃሊት ክፍለ ከተማ አለም ባንክ አካባቢ ስጋ ይዛ ጣራ ላይ የወጣችን ድመት ለማውረድ የሞከረችው የ18 አመት እድሜ የሆናት ሴት በደረሰባት የኤልክትሪክ አደጋ ህይወቷ ማለፉ ታውቋል፡፡
ወጣቷ በድመት የተወሰደባትን ስጋ ለማስጣል በሞከረችበት ጊዜ ነው በኤልክትሪክ ምክንያት ህይወቷ ያለፈው ተብሏል፡፡

በአጠቃላይ በበአሉ ቀን እና በዋዜማው እለት የሶስት ሰዎች ህይወት ማለፉ የነገረ ሲሆን ከትራፊክ አደጋ ጋር በተያያዘም በዋዜማው ሁለት የሞት አደጋ መድረሳቸው ተነግሯል፡፡
ከበአሉ ጋር በተያያዘ የከፋ የጸጥታ ችግር ባያጋጥምም በጸም ምክንያት ግን የአንድ ሰው ህይወት ማለፉን በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ የሆኑት ምክትል ኮማንደር  ማርቆስ ታደሰ ተናግረዋል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግኑኝነት ሃላፊ ም/ኮምማንደር ማርቆስ ታደሰ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ባልደራስ አካባቢ በተከሰተ አለመግባባት የአንድ ሰው ህይወት አልፋል ብለዋል፡፡
ከዚህ ግድያ ጋር በተያያዘም የተጠረጠሩ እስካሁን ድረስ 8 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ነው የተገለጸው፡፡
ፖሊስ አሁንም ከግድያው ጋር በተያያዘ ምርምራ እያካሄደ እንደሚገኝም ጨምረው ገልጸዋል፡፡

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
3.2K views10:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-16 09:03:27
የይለፍ ቁጥሩ ስንት ነው?

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
3.0K viewsedited  06:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ