Get Mystery Box with random crypto!

🇪🇹 ኢትዮ Students

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiostudents — 🇪🇹 ኢትዮ Students
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiostudents — 🇪🇹 ኢትዮ Students
የሰርጥ አድራሻ: @ethiostudents
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 56.46K
የሰርጥ መግለጫ

Our Bot :
@EthioExamBot
Contact : @ethioexamsupport
Or
@Etssupport

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 23

2022-04-27 18:33:27
Campus Twin ምንድነው ???

Campus Twin
ከናንተ ጋር ተመሳሳይ ዩኒቨርስቲ የደረሳቸው ስንት ተማሪዎች እንደሆኑ እና እነማን እንደሆኑ የምታውቁበት #Feature ነው ።


ማን ማን ከኔ ጋር ተመድቧል

መልሱን ለማወቅ


@Exampreparationbot
@ethioexambotbot
@EthioExamResultBot
@CampusGeeksBot
@neagovetbot
@Neagovet_bot
@Ethioresultbot
@examplus_bot


በመጀመሪያ "Admission Number" ያስገቡ
በመቀጠል "Placement Result" ወይም "የምደባ ውጤት" የሚለውን ይምረጡ፣
ቀጥሎ "Campus Twin" የሚለውን ይምረጡ፣።


@EthioStudents @Ethiostudents
52.7K views15:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-25 16:59:07
የዩኒቨርሲቲ የምደባ ውጤት ተለቋል።

ቦቶቻችንን የምደባ ውጤታችሁን በማሳየት ላይ ይገኛሉ።

የ2013 አ.ም የዩኒቨርሲቲ ምደባ ውጤት በሁሉም ቦቶቻችንን ማግኘት ትችላላችሁ።

ከአለን የተጠቃሚ ቁጥር ብዛት አንጻር busy ሊሆኑ ስለሚችል በትእግስት ተጠቀሟቸው።

በመጀመሪያ "Admission Number" ያስገቡ
በመቀጠል "Placement Result" ወይም "የምደባ ውጤት" የሚለውን ይምረጡ፣

#2013_Placement_Result

@neagovetbot
@Neagovet_bot
@Ethioresultbot
@examplusbot
47.0K views13:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-25 08:03:49
ሰበር ዜና

የ ዩኒቨርስቲ ምደባ ይፋ ተደርግዋል

የ 2013 12ኛ ክፍል ማለፊያ ነጥብ ላመጡ ተማሪዎች ዩኒቨርስቲ ምደባ ይፋ ተደርግዋል
ውጤታችሁን ለማየት ከታች ባለው ግሩፕ አድሚሽን ቁጥራችሁን በማስገባት ማየት ትችላላችሁ።
https://t.me/studentsethiopia

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
46.4K viewsedited  05:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-19 15:24:54
#Update

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ፤ ከክልሉ ተጨማሪ ወደ መንግስት ዩኒቨርሲቲ እንዲገቡ የተወሰነላቸው 4339 ተማሪዎች በምን አግባብና ሂደት እንደሚመረጡ አሳውቋል።

4,339 ተማሪዎች 50 ፐርሰንት እና ከዛ በላይ ካመጡ ከክልሉ ሁሉም ዞኖች መካከል በውጤታቸው ቅደም ተከተል ይመረጣሉ ብሏል።

ይህ በዚህ እንዳለ ሌሎች 50 ፐርሰንት እና በላይ ውጤት አምጥተው ወደ ዩኒቨርስቲዎች መግባት ያልቻሉት ደግሞ በክልሉ መምህራን ኮሌጆቾ በመደበኛው የዲግሪ ኘሮግራም የመምህርነት ስልጠና እንዲጀምሩ ሰፋ ያለ ቁጥር ለመቀበል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ቢሮው አሳውቋል።

ሌላው መግቢያ ነጥብ ያላመጡ ተማሪዎች በመደበኛ ተማሪነት በድጋሜ ፈተና ይወስዳሉ የተባለው ሁሉንም የክልሉን ተማሪዎችን የሚያካትት ሲሆን ይህም በልዩ ሁኔታ ለአማራ ክልል ብቻ መሆኑ ተገልጿል።

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ወደ ዩኒቨርስቲዎች ሆነ ወደ መምህራን ኮሌጆቾ መግባት ያልቻሉት ተማሪዎች በቂ ዝግጅት አድርገው መፈተን እንዲችሉ የ2014 ዓም የ12ኛ ክፍል የፈተና ጊዜ እንዲራዘም ትምህርት ሚኒስቴርን ጠይቋል።

ትምህርት ሚኒስቴርም ቢሮው ባቀረበው ጥያቄ መሠረት ከመስከረም 2015 ዓ/ም በፊት ፈተናው እንደማይሰጥ ትላንት መወሰኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ገልጿል።

የክልሉ ተማሪዎች የ2014 የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከመስከረም 20 ቀን 2015 ዓ/ም ጀምሮ ባሉት ጊዚያት ሊሰጥ እንደሚችል አውቀው ተገቢውን ዝግጅት እንዲያደርጉ ቢሮው አሳስቧል።

መረጃውን ይፋ ያደረጉት ዶክተር ማተብ ታፈረ (የክልሉ ት/ቢሮ) ሀላፊ ናቸው።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
54.1K views12:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-18 12:54:14
የዩኒቨርሲቲ ምደባ በዚህ ሳምንት መጨረሻ ይፋ ይሆናል ሲል ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቆናል።

መቼ ? በየትኛው ቀን ? ስለሚለው ጉዳይ አንድ የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ኃላፊ ቁርጥ ያለውን ቀን ለማሳወቅ እየተሰራ ነው ፤ ቀኑንን እናሳውቃለን ሲሉ ለቲክቫህ መልዕክት ልከዋል።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
45.5K views09:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-18 11:41:05
#አሁናዊ_መረጃ
ትምህርት ሚኒስቴር ፥ በጦርነት እና በግጭት ውስጥ ሆነው ተፈትነዋል ተብለው የተለዩ እና የ12ኛ ክፍል የማለፊያ ውጤት ያላመጡ ተማሪዎች በዚህ ዓመት በሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና እንደ መደበኛ ተማሪ ሆነው መፈተን እንደሚችሉ አስታወቀ፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር፣ ሁሉም ክልሎች እና የከተማ መስተዳድሮች ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች በጋራ መግለጫ እየሰጡ እየተሰጠ ነው ዝርዝር መረጃ ይዘን እንቀርባለን።


@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
40.0K views08:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-14 15:55:35 "የትምህርት ሚኒስቴር በአጭር ጊዜ ውጤቱን ይገልጻል።" የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ

በአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የተላከው አጣሪ ኮሚቴ በፈተና አስተራረም ዙሪያ የደረሰበትን ሂደት ይፋ አድርጓል።

የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ይፋ ከተደረገ በኋላ በተማሪዎች፣ በመምህራን፣ በወላጆች እና በተቋማት ቅሬታ መፈጠሩ ይታወቃል።

የፈተና ውጤቱ የአስተራረም ስህተት አለበት እንዲሁም በጦርነቱ ውስጥ የነበሩ አካባቢዎችን ግምት ውስጥ ያስገባ አይደለም የሚሉ ቅሬታዎች ተነስተውበታል።

በአማራ ክልል በ12ኛ ክፍል የፈተና አስተራረም ዙሪያ የተነሳውን ቅሬታ ለማጣራት የክልሉ ትምህርት ቢሮ አጣሪ ኮሚቴ መላኩ ይታወሳል። አጣሪ ኮሚቴው የደረሰበትን ሂደት በተመለከተ ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል።

መግለጫውን የሰጡት የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊና የኮሚቴው ሰብሳቢ ሙላው አበበ ፈተናው በአማራ ክልል ያለምንም ችግር ተጠናቅቆ እንደነበር አስታውሰዋል።

ፈተናው ታርሞ ውጤት ሲታይ ችግር ስለነበር ሳይስተካከል መለቀቅ የለበትም የሚል ቅሬታ ትምህርት ቢሮው ማቅረቡንም አንስተዋል። የተነሱ ችግሮች ሳይጣሩ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ መቆረጥ እንደሌለበት መግለጻቸውንም ተናግረዋል።

የውጤት መቀያቀር እና የፈተና አስተራረም ስህተት ስለነበር አጣሪ ኮሚቴ ወደ አዲስ አበባ መላኩንም አስታውቀዋል።

"በትምህርት ቤታቸው ጎበዝ የነበሩ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ የመግቢያ ውጤት ያላመጡበት ምክንያት፣ አንዳንድ ተማሪዎች በአንድ ትምህርት ከፍ ያለ ውጤት በአንደኛው ደግሞ የወረደ ያመጡበት ምክንያት፣ ምንም አይነት ተማሪዎች ያላስገቡ ትምህርት ቤቶችንና የውጤት መቀያየር ለምን ኖረ? የሚለውን ይዘው መሄዳቸውንም" ገልጸዋል።

የዩኒቨርሲቲ መግቢያ በጦርነት ለተጎዱ አካባቢዎች ታሳቢ ያደረገ አይደለም የሚለው ጥያቄም ሌላው ጉዳይ እንደሆነ ተናግረዋል።

ማሽኑን አናምንም ብለን በእጃችን ሁሉ አርመን አረጋግጠናል፣ የውጤት አገላለፁ ምን ያክል ትክክል ነው የሚለውንም አይተናል ብለዋው። የፈተና ቡክሌት መቀያየር ችግር እንደተመለከቱም ገልጸዋል።

ምንም ያላሳለፉ ትምህርት ቤቶችን ርእሰ መምህሩን በመውሰድ ጎበዝ ተማሪዎችን በእጃችን ሁሉ የማረም ሥራ ሠርተናል ነው ያሉት።

በአማራ ክልል ተማሪዎች ውጤት መቀነሱ በጦርነት ምክንያት የሥነ ልቦና ችግር ስለነበረባቸው ነውም ብለዋል። እነዚህን ተማሪዎች ከሌሎች ተማሪዎች ጋር እኩል መመዘን ፍትሐዊ አለመሆኑን ቢሮው መጠየቁንም ጠቁመዋል። ከሲቪክስ ውጤት በተጨማሪ በሌሎች ላይም ጥርጣሬ አለን መታየት አለበት የሚል ጉዳይ ማቅረባቸውንም ገልጸዋል።

ፈተናዎች ወጥተዋል የሚል ወሬ በመናፈሱ ተማሪዎች ሳይረጋጉ መፈተናቸው በውጤታቸው ተፅዕኖ መፍጠሩንም ተናግረዋል።

የትምህርት ቢሮው ኃላፊ ማተብ ታፈረ (ዶ/ር) እየተነሱ ያሉ ጉዳዮችን ያለ እረፍት እየተከታተሉ መሆናቸውን አስታውቀዋል። የክልሉ ተማሪዎች ያላቸው አቅም ይታወቃል ያሉት ኃላፊው ነገር ግን በተማሪዎች ውጤት ላይ የታየው የውጤት ማሽቆልቆል የተጠበቀ እንዳልነበር ተናግረዋል። ለውጤት ማሽቆልቆል ምክንያት የፈተና አስተራረም ችግር፣ በሌሎች አካባቢዎች አብላጫ እድል ተወስዶባቸው ይሆናል የሚልና ጦርነቱ ያመጣው ችገር ይሆናል የሚል ጉዳዮችን ይዘው መሥራታቸውንም ተናግረዋል።

የተቋቋመው ኮሚቴ ያገባኛል ከሚሉ አካላት የተውጣጣ መሆኑንም ገልፀዋል። በቴክኖሎጂ ችግር እንዳይፈጠር የሶፍት ዌር ባላሙያ ጭምር በኮሚቴው መካተቱን ተናግረዋል። ቢሮው በትኩረት እየሠራበት መሆኑን የተናገሩት ዶክተር ማተብ ዝም ብሎ የራስን ሃሳብ ብቻ ማቅረብ የሕዝብ ጥያቄም አልመለሰም፣ ሕዝብም አላዳነም ነው ያሉት።

ትምህርት ሚኒስቴርም ኮሚቴው ማጣራት የሚገባውን ጉዳይ እንዲያጠራ ትብብር ማድረጉንም አስታውቀዋል። እንደሲቪክስ በጣም የወጣ ባይሆንም በሌሎች የትምህርት አይነቶችም ጥርጣሬ መነሳቱንም ተናግረዋል።

በተነሱ ችግሮች በተደረገ ውይይት በትምህርት ስርዓቱ ላይ ያለው የእምነት መላላት እንዲስተካከል መስማማታቸውን ገልፀዋል።

የፈተናዎች ስርቆት መኖሩንም በተደረገው ውይይት መገለፁን እና ከዚህ አዙሪት ለመውጣት የሚያስችል ሥርዓት መዘርጋት እንደሚያስፈልግ መግባባታቸውንም ተናግረዋል።

የአማራ ክልልን ከማንም ክልል ጋር ሳናወዳድር በራሱ ክብረ ወሰን ነው ያወዳደርነው ያሉት ዶክተር ማተብ በአንድ ዓመት እንደዚህ አይነት የውጤት ማሽቆልቆል ሊፈጠር እንደማይችል ዝርዝር ጉዳይ ማቅረባቸውን ገልፀዋል። በተደረገው ውይይት ጦርነቱ በተማሪዎች ውጤት ላይ ተፅዕኖ ማሳረፉን መስማማታቸውንም አስታውቀዋል። ውሳኔው ደግሞ ከፍ ባሉ አካለት እንዲሰጥ መግባታቸውንም አንስተዋል። እኛ ጥያቄ ያቀረብነው ተማሪዎች አማራ ስለሆኑ ሳይሆን ችግር ውስጥ ስለነበሩና ችግሩን በግልጽ ስለምናውቀውና ስለነበርንበት መታየት ስላለበት ነው ብለዋል።

ለሚነሱ ችግሮች እንደሚታገሉም አረጋግጠዋል። በሕልውና አደጋ ውስጥ የነበሩ ተማሪዎች ለፈተና ሲዘጋጁ ነበር ብሎ መከራከር እንዳማይቻልም ገልፀዋል። የአማራ ክልል ወጣቶች በጦርነቱ ምክንያት ከሌሎች አካባቢዎች በተለየ መልኩ በሕልውና ዘመቻው ተሳትፈዋል። በርካታ መምህራን በጦርነቱ ተሳትፈው ተሰውተዋል። በዚህ ሁኔታ ውስጥ የነበረ ተማሪ ተረጋግቶ ተፈትኗል ማለት አይቻልም፤ ይህን ሰው የሆነ ሁሉ እንዲረዳው እንፈልጋለን፣ ኢትዮጵያውያን በዚህ ልክ እንዲረዱን እንፈልጋለንም ብለዋል።

ጦርነቱ ከፍተኛ የሆነ ችግር አድርሷል ይህ ሊታመን ይገባልም ነው ያሉት። በአስከፊ ጦርነት ውስጥ ቆይተው ያለ በቂ ዝግጅት የተፈተኑ ተማሪዎች የተለየ ፍትሐዊ ውሳኔ ይፈልጋሉ ብለዋል። በሀገር በተቃጣ ጦርነት የአማራ ክልል ተማሪዎች ተለይው ሰላባ መሆን የለባቸውምም ብለዋል። እንዲህ አይነት ችግር በየትኛውም አካባቢ ይፈጠር ለፍትሐዊነት እንታገላለን ነው ያሉት። ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ ዓይናችን ከጉዳዩ ላይ አናነሳም፣ የተወከልነው የሕዝብ ጥያቄ ለመመለስ ነው፣ ሌላ ጉዳይ የለንም፣ መተማመን ሊኖረን ይገባል፣ እኛ የሕዝባችን ልጆች ነንም ብለዋል። በትምህርት ሚኒስቴር በኩልም በአጭር ጊዜ ውጤቱን ይገልጻል ብለዋል።

አሁን የተፈጠረው እንዲፈታ ጥሩ ሂደቶች መኖራቸውን ያነሱት ኃላፊው፤ ቀጣይ ተፈታኞች ተገቢ ዝግጅት እንዲያደርጉ የሞራልም የሙያም ድጋፍ እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል። #አሚኮ


@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
47.6K views12:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-14 14:24:13
የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ምዝገባን አስመልክቶ ማብራሪያ ተሰጠ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት 12ኛ ክፍል ለሚያስፈትኑ የመንግስትና የግል 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሀገር አቀፍ ፈተና የምዝገባ ስርዓትን አስመልክቶ ኦረንቴሽን ሰጥቷል::

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳኘው ገብሩ በገለፃው ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት በምዝገባው ወቅት የሚፈጠሩ የመረጃ ክፍተቶችን ለመከላከል በየደረጃው የሚገኝ አካል ለምዝገባው ትኩረት ሰጥቶ እንዲሰራ አሳስበዋል::

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዲናኦል ጫላ በበኩላቸው ክፍለ ከተሞችና የትምህርት ቤት ርዕሳነ መምህራን በምዝገባው ዝግጅት ሂደት የራሳቸው ሚና እንዳላቸው ገልፀዋል:: በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳም መረጃዎችን በአግባቡ በመሙላት ተመዝጋቢዎችን ዝግጁ እንዲያደርጉ አሳስበው በምዝገባ ሂደት መደረግ ስላለበት ጥንቃቄ አብራርተዋል ::

በመድረኩ የፈተና እና አይ ሲ ቲ ባለሞያዎች ፣ የአማርኛና አፋን ኦሮሞ ትምህርት ቡድን መሪዎች እንዲሁም የትምህርት ቤት ርዕሳነ መምህራን ተገኝተዋል፡፡

በዘንድሮው ዓመት የ12ኛክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በ201 ትምህርት ቤቶች 50ሺ 504 ተማሪዎች በቀን ፣ በማታና በግል ይመዘገባሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ከሚያዝያ 7 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ምዝገባ እንደሚጀመር ከዳይሬክቶሬቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል::

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
35.3K views11:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-09 21:08:40
#NE2014

ከትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በተገኘው መረጃ የ2014 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ነው።

ፈተናው የሚያጠቃልለው ከ9ኛ ክፍል እስከ 12ኛ ክፍል ሲሆን የ " ኢኮኖሚክስ " ትምህርትን እንደማያካትት ከአገልግሎቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የፈተናው ቅድመ ዝግጅት እየተጠናቀቀ መሆኑን የሚገልፀው አገልግሎቱ፤ ከአሁን በኃላ ከINSA፣ ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት እና ከፌዴራል ፖሊስ ጋር በመቀናጀት የፈተናውን ዝግጅት የሚጀምርበት ነው ብሏል።

በ2013 ዓ/ም ብሄራዊ ፈተና ከገጠሙ ችግሮች አንፃር የ2014 ዓ/ም ፈተና በምን መልኩ ነው የሚሰጠው ? እንዴትስ ከዚህ በፊት የገጠሙ ችግሮችን በሚፈታ መንገድ ፈተናው ይሰጣል በሚለው ላይ ውይይት እየተደረገ ነው ተብሏል።

እስካሁን የ2014 ዓ/ም ብሄራዊ ፈተና የሚሰጥበት ቀን ያልተገለፀ ሲሆን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚሰራጩ መረጃዎች ትክክለኛ አይደሉም።

በሌላ በኩል፥ በ2013 ዓ/ም ፈተናቸውን የወሰዱና የመንግስት ዩኒቨርሲቱ መግቢያ ነጥብ ያስመዘገቡ ተማሪዎች እስካሁን (የዓመቱ 8ኛ ወር ገብቷል) ምደባቸው ይፋ ያልሆነ ሲሆን መቼ ይፋ እንደሚሆን የታወቀ ነገር የለም።

ከፈተናው ጋር በተያያዘ ለትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የቀረቡ ቅሬታዎች እየታዩ ሲሆን ከመነሻው ጅምሮ አጠቃላይ ቅሬታቸውን ያመለከቱ ወደ 30 ሺ የሚደርሱ ተማሪዎች እንደሆኑና እስከትላንት በስቲያ ድረስም ቅሬታዎች እየታዩ እንደነበር ተገልጿል።

ምደባን በተመለከተ ከቀናት በፊት የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላኩት መልዕክት ተማሪዎችና ወላጆች ለትንሽ ጊዜ እንዲታገሱ እና በማህበራዊ ሚዲያ ከሚሰራጩ ሀሰተኛ መረጃዎች እራሳቸውን እንዲጠብቁ መልዕክት ማስተላለፋቸው ይታወሳል።

@ETHIOSTUDENTS
51.6K views18:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-08 12:07:19 ሀገርና ትውልድ እየገደለ ያለው የፈተና ስርቆት !

የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፦

" ... ፈተናዎች ይሰረቃሉ። ቢያብስ እኔ እስከማውቀው ከ2008 ዓ/ም ጀምሮ የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና ያልተሰረቀበት ጊዜ ያለ አይመስለኝም፤ ደረጃው ይለያይ እንጂ።

አንዱ መሰረታዊ ጥያቄ መጠየቅ ያለብን እንዴት ነው የሚሰረቀው ? ማነው የሚሰርቀው ? ለምድነው የሚሰርቀው ? የሚለው ነው።

አንደኛው በአጠቃላይ ፈተናውን አውጥቶ ሶሻል ሚዲያ ላይ ለቆ ሁሉም እንዲያገኘው ማድረግ ነው። ይሄ የተወሰነ ግሩፕን ለመጥቀም የታለመ እንቅስቃሴ አይደለም። በአጠቃላይ የትምህርትሩትን Integrity ለማናጋት የሚደረግ እንቅስቃሴ ነው። ምክንያቱም አንድ ፈተና አውጥቶ ለሁሉም በሶሻል ሚዲያ ሲለቀቀ አንድ የተወሰነ ግሩፕ የሚጠቀምበት ሁኔታ የለም ሁሉም ነው የሚያገኘውና፤ እሱ በአጠቃላይ እንደማህበረሰብ ሁሉን ነገር ፖለቲካ እና የፖለቲካ ትርፍ ማግኛ እየተደረገ የሚኬድበት አካሄድ ያመጣው ጣጣ ነው። በስፋት እና በስነስርዓት መታለፍ ያለበት ሂደት ነው።

ፈተና ሚሰረቀው ግን በዛ መልክ ብቻ አይደለም፤ በተለያየ መልክ ፈተና ይሰረቃል። ከየት በኩል ነው ስርቆቱ ሊመጣ የሚችለው ብለን ለማየት ሞክረን ነበር።

ፈተና አውጭዎቹ ፣ ፈተና የሚያዘጋጁ ሰዎች አካባቢ ስርቆት ሊፈፀም ይችላል። ፈተና አውጭዎችን የምንከታተልበት መንገድ በጥንቃቄ ለመመለከት ሞክረናል እዛ አካባቢ ትልቅ አደጋ አላየንም።

ፈተና ሲታተም ፤ አታሚ መስሪያ ቤት ውስጥ የሚደረገው ጥንቃቄ እና ጥበቃ አለ። ፈተና የሚያትመው 4 ኪሎ ያለው ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ነው። ፈተና ማተመ ከተጀመረ ጀምሮ በፌዴራል ፖሊስ ዕዝ ስር ነው። በሙሉ ካሜራ እየታየ ነው የሚታተመው ያ ፈተና እዛ ይሰረቃል የሚለው እድል አነስተኛ ነው።

በአብዛኛው ፈተና ከስርጭት ጋር በተያያዘ ፈተናው ተይዞ በየክልሎች በሚሰራጭበት ጊዜ ካለው ጀምሮ ነው ችግሩ ያለው።

አንዳንዱ ሆን ተብሎ ነው፤ አንዳንዱ በየክልሉ ያሉ የመንግስት በዞን ይሁን በወረዳ በተለያየ ደረጃ ያሉ የመንግስት ባለሟሎች የሚሳተፉበት ነው። ይሄ መነሻው ይሄን ፈተና ሰርቆ ለአካባቢው ተወላጆች / ተፈታኞች በመስጠት አካባቢዬን እጠቅማለሁ ተብሎ የሚታሰብ የትምህርት ስርዓቱን ከፖለቲካ እና ከክልላዊነት ጋር ያጣበቀው አካሄዳችን ያመጣው በጣም ትልቅ ችግር ነው።

... ፈተና ሰርቀን የአካባቢያችንን ሰው እንጠቅማለን ፤ የአካባቢያችንን ተማሪ እንጠቅማለን ብሎ የሚያስብ ሰው የሚያስበው ምንድነው ? ያ በስርቆት አልፎ የመጣ ተማሪ ኮሌጅ ገብቶ በስርቆት እና በማጭበርበር ድግሪ ያገኛል ፤ በስርቆት እና በማጭበርበር የያዘውን ድግሪ ይዞ እዛው ክልል መንግስት ውስጥ ነው ስራ የሚቀጠረው እና በትክክል እንዲሰራ ነው የሚጠበቀው ? ክልል መንግስት ውስጥ ገብቶ መስረቅ ነው የሚጀምረው / የትም ቦታ ቢገባ።

የስርቆት ስርዓቱ አንዴ ከታች ማበላሸት ከጀምርን በፍፁም መቆሚያ የሌለው ማንንም በተለየ የማይጠቅም ህብረተሰብን ግን በጋራ ይዞ ገደል የሚገባ ስራ ነው።

ፈተናዎች የሚሰረቁት ፤ ፈተናው ከመሰረቁ ባሻገር ተማሪዎች ሊፈተኑ ከገቡ በኃላ ያለአግባብ በኩረጃ ወይም በፈታኞች እርዳታ ያለ አግባብ ውጤት እንዲያመጡ በተቀናበረ እና በተደራጀ መንገድ እንቅስቃሴ ይካሄዳል።

... የምናውቃቸው ነገሮች አሉ። አንዳንድ ክልል ፈታኞች ሲሄዱ ገንዘብ ተዋጥቶ፣ በሬ ታርዶ ፣ ድግስ ተደርጎ ፣ እንደውም ከገንዘቡ ተጨማሪ ለፈታኞቹ ጉቦ ተሰጥቶ ወይ ፈተናውን አይቶ እዛው እራሳቸው አርመው ለተማሪዎቹ እንዲሰጡ ወይም እርስ በእርስ ሲኮራረጁ ዝም ብሎ እንዲያዩ የሚደረግበት ጉደኛ ሀገር እኮ ነው ያለነው።

የግል ትምህርት ቤቶች ባለቤቶች የነሱ ትምህርት ቤቶች የሚፈተኑባቸውን ትምህርት ቤቶች / ቦታዎች እየፈለጉ ፈታኞቹን ለማማለል ጉቦ ለመስጠት የሚወጣው ወጪ በሚሊዮን ነው የሚቆጠረው።

እንዴት አድርገን ነው እንደሀገር በዚህ ሁኔታ ይሄ 12ኛ ክፍል ፈተና ላይ የጀመረ ነገር አይደለም የምናወራው ፤ ከስር ጀምሮ የመጣ ነው ኮሌጅ ሲደርስ ደግሞ የሚያቆም አይደለም። ኮሌጅ ውስጥ ያለውን የፈተና ስርቆት እና ማጭበርበር እና ኩረጃ ሁላችንም የምናውቀው ነው።

ወረቀት ለአንድ ትምህርት ስርዓት ለአንድ ሰው ዲፕሎማ / ዲግሪ ሲሰጥ ለህብረተሰቡ እየነገር ያለው ይህ ሰው በተማረበት ትምህርት መስክ ይሄን ያህል ውጤት አለው ተቀበል ነው ህብረተሰብን የሚለው። ያ ወረቀት በስርቆት ከመጣ፣ ያ ወረቀት በኩረጃ ከመጣ ያ ወረቀት ትርጉም የለውም።

... ብዙ የግል ኮሌጆች የዲግሪ ወፍጮ ቤቶች ናቸው ። ዲግሪ ነው እየሸጡ ያሉት ልጆችን አስተምረው ፣ አብቅተው አይደለም። ያ ማለት ጥሩ ጥሩ ትምህርት ቤቶች ፣ ጥሩ የሚያስተምሩ የሉም ማለት አይደለም።

ነገር ግን አንዴ የትምህርት ስርዓቱ ከታች እስከ ላይ መሰረታዊ Integrity ከተበላሸ ፤ ለምን ይገርመናል አሁን ያለንበት መከራ ውስጥ መሆናችን እንደ ሀገር ። የሚያበላሸው ሁሉን ነገር ነው። ሲቪል ሰርቪሳችን ፣ ፖለቲካችንን ያበላሸዋል።

በትንሽ በትልቁ የምንባለው እና የምንጋደለው እኮ ከትምህርት ስርዓትም ጋር የተያያዘ ነው። ለዚህ ነው ይሄን ነገር እንደቀላል ነገር አይደለም ማለት ያለብን ፤ ... በመሰረታዊ መንገድ ይሄን ካልቀየርነው የትም አንሄድም። "

ፕ/ር ብርሀኑ ነጋ

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
41.2K viewsedited  09:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ