Get Mystery Box with random crypto!

🇪🇹 ኢትዮ Students

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiostudents — 🇪🇹 ኢትዮ Students
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiostudents — 🇪🇹 ኢትዮ Students
የሰርጥ አድራሻ: @ethiostudents
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 56.17K
የሰርጥ መግለጫ

Our Bot :
@EthioExamBot
Contact : @ethioexamsupport
Or
@Etssupport

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 16

2022-12-18 21:55:37
2.7K views18:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-18 21:55:36
አርጀንቲና የ 22 ኛው አለም ዋንጫ አሸናፊ ሆናለች
2.7K views18:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-15 20:59:38 #NationalExam

2ኛው ዙር የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከታህሳስ 18 እስከ 21/2015 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ይሰጣል።

በሁለተኛው ዙር ለፈተና የሚቀመጡ የሁሉም ክልል ተማሪዎች መለየታቸውን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

በሁለተኛው ዙር የ12ኛ ክፍል ፈተና የሚወስዱ ፦

• የመጀመሪያውን ዙር ፈተና በወሊድ ወይም በእርግዝና ምክንያት መፈተን ያልቻሉ፣

• በሕግ ጥላ ስር ወይም በማረሚያ ቤት ሆነው ለመፈተን ያልቻሉ፣

• የሀገር መከላከያ ሠራዊት ወይም የፌዴራል ፖሊስ ወይም የክልል ልዩ ኃይል አባል ሆነው በወቅቱ በግዳጅ ላይ በመሆናቸው ያልተፈተኑ፣

• በህመም ወይም ተቀባይነት ባገኘ ችግር ምክንያት ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ፈተና ያልወሰዱ፣

• ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በደረሰው የድልድይ መደርመስ አደጋ ምክንያት ያልተፈተኑ፣

• በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ በተፈጠረው ችግር ምክንያት አንድ ፈተና እንዲፈተኑ የተወሰነላቸው፣

• ተቀባይነት ባገኙ ችግሮች ምክንያት ፈተና እንዲወስዱ የተወሰነላቸው።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
2.7K views17:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-15 15:56:18
" የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና (የ2ኛ ዙር) ከታህሳስ 18 - ታህሳስ 21 ይሰጣል " - የሲዳማ ክልል ትምህርት ቢሮ

ከዚህ ቀደም በነበረው የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ወቅት ፈተናቸውን መውሰድ ላልቻሉ ተማሪዎች ፈተና ለመስጠት እየተሰራ ይገኛል።

ዛሬ ከሲደማ ክልል የትምህርት ቢሮ ባገኘነው መረጃ በተለያዩ ምክንያቶች ፈተና ሳይፈተኑ የቀሩ ተማሪዎችን በ2ኛ ዙር ፈተና ከታህሳስ 18 እስከ ታህሳስ 21 ድረስ ለማስፈተን ዝግጅት ተደርጓል

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
5.4K views12:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-14 10:26:25
በኢፊዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ማረጋገጫ የማይሰጣቸው የትምህርት ማስረጃዎች

1. የመጀመሪያ ዲግሪ ለመማር በመግቢያነት የተያዘው ዲፕሎማ ( ዲግሪ ከተመረቁበት የትምህርት መስክ ጋር ተያያዥነት የሌለው ከሆነ፤

2. የደረጃ 4 ብቃት ማረጋገጫ(COC) ሳያሟሉ እየተማሩ የነበሩና ትምህርት ከጀመሩ በኋላ ያሟሉ ከሆኑ፤

3. እውቅና ፈቃድ : በሌለው የከፍተኛ ትምህርት ተቋም የተማሩ ከሆነ፤

4. የፕሮግራም እውቅና ፈቃድ : በሌለው የትምህርት መስክ የተማሩ ከሆነ፤

5. የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ የመቁረጫ ነጥብ ሳያሟሉ የተማሩ ከሆነ፤

6. የመጀመሪያ ዲግሪ ተምሮ ለመመረቅ የሚያስፈልገውን ዓመትና Credit hours ሳያሟሉ የተመረቁ ከሆነ፤ እና

7.ከውጭ ሀገር ተምረው በኢፊዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን የአቻ ግምት ሳያስሩ ተምረው የተመረቁ ከሆነ ናቸው፡፡

ጥያቄ ና አስተያየት ለመስጠት
  @ethiouniversity1bot

            Share share
ለተጨማሪ መረጃ
╔═══════════╗
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
╚═══════════╝
3.1K views07:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-13 15:28:16 በአዲስ አበባ የትምህርት ቤቶች ጉዳይ የከተማው አስተዳደር፣ ትምህርት ቢሮ ፣ ፖሊስ ፣ ወላጆች ምን ይላሉ ?

የአዲስ አበባ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ፦

" ሲጀመር አዲስ አበባ አፋን ኦሮሞ የምታስተምርበት ስርዓተ ትምህርት አልነበራትም መምህራኖች ታውቃላችሁ ይሄንን እውነት።

ያኔ ቀርቶ እስካሁንም አፋን ኦሮሞ ወይም ቋንቋዎች የምናስተምርበት ስርዓተ ትምህርት አልጨረስንም አላፀደቅንም።

ስርዓተ ትምህርት ከኦሮሚያ ተዋስን አፋን ኦሮሞ የሚሰጠው ኦሮሚያ ነው ይህ በዘመነ ኢህአዴግ ነው።

እዛ ላይ ስርዓተ ትምህርቱ ላይ ምን አለ ትምህርት ክፍል ከመጀመሩ በፊት የክልሉ መዝሙር ይዘመራል፤ የክልሉ ባንዲራ ይሰቀላል የሚል አለ።

ይህን ሙሉ ስርዓተ ትምህርቱን በመተግበር ነው 4 ትምህርት ቤቶች (አ/አ ያሉ) የጀመሩት። በውቅቱ አጀንዳ ያደረገውም የለም። በዚህ ምክንያት በተለየ ሁኔታ ኦሮሞ ይጠቀማል ተብሎ የታሰበ ነገር አልነበረም።

ከዛ ተማሪዎች እያደር እየሰፉ መጡ ፣ ከየአካባቢው ፍላጎት ያላቸው ፣ በየአካባቢው ተመዝጋቢ እየበዛ መጣ ኦሮሞም የሆነ ያልሆነ መማር የሚፈልግ እየተመዘገበ መጣ።

እና እንዴት አድርገን ነው የካ ላይ የተመዘገበን ሄደህ ኮልፌ ላይ ነው የምትማረው የምንለው ? ለምን በአካባቢው ላይ ባለ ት/ቤት ክፍል የማንከፍትለት ?

በአካባቢው ትም/ቤት ላይ ፤ በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው መማር እንዲችሉ ትምህርት ቤት እየተከፈተ (በ403 ትምህርት ቤት ውስጥ) በአፋን ኦሮሞ መማር ተጀመረ ሲጀመር ይኸው ካሪኩለም / ስርዓተ ትምህርት ነው አብሮ እየሄደ ያለው።

መማህራኖች፣ ትምህርት ቤቶች እጃቸው ላይ ያለው ስርዓተ ትምህርት እሱ ነው ስርዓተ ትምህርቱን ተግብሩ ተብሎ ስለተሰጣቸው ስርዓተ ትምህርቱ ላይ ያለውን ሙሉ ነገር እየተገበሩ መጡ ይኸው ነው። "

የአ/አ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ፦

" የሆኑ ት/ቤቶች ላይ ይሄንን ቋንቋ አንሰማም የሚል ይህ መዝሙር መዘመር የለበትም የሚል ጥያቄ ያነሳ አለ። ሌላ ትምህርት ቤቶች ላይ በተለይ አፋን ኦሮሞ ተማሪዎች የሚበዙበት ላይ ሌላ ጥያቄ።

በአማርኛ የሚማሩ/ የአፋን ኦሮሞ ተማሪዎች ቁጥር ባነሰበት በባንዲራ መዝሙር አላማው አንድ ያደረገ ግን በተለያየ ስትራቴጂ መጥቶ የከተማውን ሰላማዊ መማር ማስተማር ማደፍረስ ነው። "

ወላጆች እና ተማሪዎች የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት ምን ይላሉ ?

ደስ ታቲሌስ ፦

" ... ትምህርት በ ' #አፍ_መፍቻ_ቋንቋ ' መማር እና የአንድ ክልልን ባንዲራን መስቀልና መዝሙር ማዘመር በጣም የተለያዩ ነገሮች ናቸው። 

ለምሳሌ ያህል ፦ አብዛኛዎችን የትምህርት አይነቶች የምንማረው በእንግሊዘኛ ነው። ነገር ግን የእንግሊዝን መዝሙር አልዘመርንም ፣ ባንዲራቸውም በትምህርት ቤቶቻችን ላይ አልተሰቀለም።

ይህንን ያልኩት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወይንም በመንግስት የተገነቡት ትምህርት ቤቶች ላይ ነው።

የግል ትም/ቤትን አይጨምርም። አሁን ግን የኦሮሚያ ክልል መዝሙር እየተዘመረ እና ባንዲራው እየተሰቀለ ያለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በራሱ ወጪ በሰራቸው ትምህርት ቤቶች ላይ ነው።

ሲቀጥል ቋንቋውን ማስተማርም ካስፈለገ የሌላውን ክልል መዝሙር እንዲዘምሩ በማስደረግ መሆን የለበትም።

በከተማው የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪ የሆኑ ተማሪዎች በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ሲማሩ እኮ የአማራ ክልል ባንዲራ አልተሰቀለም ፤ የአማራ ክልልን መዝሙር አልተዘመረም።

አሁን ላይ እየታየ ያለው ነገር እና ለድርጊቱ የከተማ አስተዳደር እየሰጠ ያለው መልስ ፍፁም የተለያየ ነው። "

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
4.0K viewsedited  12:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-11 14:35:30
የአርቲስቱ ቃል ተፈፃሚ ሆኗል ሲል የኢትዮጵያ የዓይን ባንክ ባወጣው የሃዘን መግለጫ ላይ ገለፀ።

በታዋቂው እና ተወዳጁ አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ) ህልፈተ ህይወት ጥልቅ ሀዘን ተሰምቶናል። ለቤተሰቦቹ፣ ለቅርብ ጓደኞቹ እና ለስራ ባልደረቦቹ የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለፅን ለወዳጅ ዘመዶቹ መፅናናትን እንመኛለን። ታሪኩ በህይወት በነበረበት ወቅት የዓይን ባንካችን አምባሳደር ከመሆኑ በተጨማሪ ህልፈት በሚያጋጥምበት ጊዜ የዓይን ብሌኑን ለመለገስ ቃል በገባው መሰረት በቤተሰቦቹ እና በጓደኞቹ ቀና ትብብር ቃሉ ተፈፃሚ ሁኗል።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
6.8K views11:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-11 14:34:33
ታሪኩ ብርሀኑ (ባባ) አይኑንም ሰጥቶ ነው የሄደው

አርቲስት ታሪኩ ብርሐኑ 2000 ዓ/ም "የዓይን ብሌኖቼን በነፃ እንዲወስዱ ፈቅጃለሁ" ሲል የገባው ውል

"ስሜ ከላይ የተጠቀሰው ስጦታ አድራጊ ለስጦታ ተቀባይ የዓይን ባንክ ሕይወት ሲያልፍ ከአስከሬኔ ላይ የዓይን ብሌኖቼ በነጻ እንዲወስዱ ፈቅጃለሁ፡፡ ስሜ ከላይ የተጠቀሰው ስጦታ አድራጊ ለስጦታ ተቀባይ የኢትዮጵያ የዓይን ብሌኖቼን በነፃ እንዲወስዱ ፈቅጃለሁ።"

- አርቲስት ታሪኩ ብርሐኑ -ባባ፤
የዓይን ብሌን የመለገሻ ቃል መግቢያ ቅጽ ላይ በ 23 ዓመቱ፣ 2000 ዓ/ም ላይ የገባው ቃል ላይ ያሰፈረው - 09/08/00


@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
6.4K viewsedited  11:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-11 09:12:00
አርቲስት ታሪኩ ብርሀኑ ከዚህ አለም በሞት ተለየ

ከአርባ በላይ የአማረኛ ፊልሞች ላይ የተወነው ተዋናይ ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ) በድንገተኛ ህመም ዛሬ ጠዋት አርፏል ።

ተዋናዩ ካባለቤቱ የፊልም ተዋናይት
ቃልኪዳን ጥበቡ ጋር ከተለያየ በኋላ ድብርት ተደጋግሞ ያጠቃው እንደነበር ፊደል ፖስት ከቅርብ ወዳጆቹ ሰምቷል።

ዕድሜው በሰላሳዎቹ አጋማሽ የሚገኘው ተዋናይ ታሪኩ ተውልዶ ያደገው ተክለ ሐይማኖት አካባቢ ሲሆን የአንድ ልጅም አባት ነው።

በአጭር ጊዜ ውስጥ ዝናን አና በብዙዎች ተወዳጅነትን ያተረፈ ተዋናይ ነው። በጉዳዬ ፊልም ላይ ደግሞ በድርሰት ፣ በዳይሬክተርነት እንዲሁም በትወና ተሳትፎበታል ፤ እጅግ በጣም ብዙ ፊልሞች ላይ ተውነዋል ።

ከተወነባቸው ፊልሞች መካከል :- 300ሺ፣ የፍቅር ABCD ፣ ብላቴና፣ ቦሌ ማነቂያ ፣ እንደ ባል እና ሚስት ፣ ኢንጂነሮቹ ፣ እርቅ ይሁን ፣ ኢዮሪካ ፣ ጉዳዬ ፣ ሀገርሽ ሀገሬ ፣ ሕይወቴ ፣ ህይወት እና ሳቅ ፣ ከባድ ሚዛን ፣ ፍቅር እና ፌስቡክ ፣ ከቃል በላይ፣ላውንድሪ ቦይ ፣ ኮከባችን ፣ ማርትሬዛ ፣ ይመችሽ-የአራዳ ልጅ 2 ፣ ሞኙ የአራዳ ልጅ ፣ ትዳርን ፍለጋ ፣ አንድ ሁለት ፣ ብር ርርር ፣ ወደው አይሰርቁ፣ ወፌ ቆመች፣ ወንድሜ ያዕቆብ ፣ እንደ ቀልድ ፣ ወቶ አደር፣ አባት ሀገር፣ የሞግዚቷ ልጆች፣ ይዋጣልን ፣ ዋሻው፣ ወሬ ነጋሪ ፣ ወጣት በ97 ተጠቃሽ ናቸዉ።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
8.0K viewsedited  06:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-09 21:06:00
በኳታሩ የዓለም ዋንጫ ክሮሺያ ብራዚልን ጥላ ወደ ግማሽ ፍጻሜው አለፈች!

በ22ኛው የኳታሩ የዓለም ዋንጫ ዛሬ ምሽት የተገናኙት ብራዚልና ክሮሺያ 90ውን ደቂቃ ያለምንም ግብ በማጠናቀቃቸው ተጨማሪ 30 ደቂቃ ለመጫወት ተገደዋል።

በጭማሪው የመጀመሪያ 15 ደቂቃ ኔይማር ባስቆጠራት ጎል ብራዚል ክሮሺያን 1 ለ 0 መምራት ብትችልም በሁለተኛው 15 ደቂቃ ክሮሺያ አቻ መሆን ችላለች።

ጨዋታው በአቻ ውጤት በመጠናቀቁ በተሰጠው የመለያ ምት ክሮሺያ 4 ለ2 አሸንፋ ወደ ግማሽ ፍጻሜው አልፋለች።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
3.5K views18:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ