Get Mystery Box with random crypto!

በአዲስ አበባ የትምህርት ቤቶች ጉዳይ የከተማው አስተዳደር፣ ትምህርት ቢሮ ፣ ፖሊስ ፣ ወላጆች ም | 🇪🇹 ኢትዮ Students

በአዲስ አበባ የትምህርት ቤቶች ጉዳይ የከተማው አስተዳደር፣ ትምህርት ቢሮ ፣ ፖሊስ ፣ ወላጆች ምን ይላሉ ?

የአዲስ አበባ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ፦

" ሲጀመር አዲስ አበባ አፋን ኦሮሞ የምታስተምርበት ስርዓተ ትምህርት አልነበራትም መምህራኖች ታውቃላችሁ ይሄንን እውነት።

ያኔ ቀርቶ እስካሁንም አፋን ኦሮሞ ወይም ቋንቋዎች የምናስተምርበት ስርዓተ ትምህርት አልጨረስንም አላፀደቅንም።

ስርዓተ ትምህርት ከኦሮሚያ ተዋስን አፋን ኦሮሞ የሚሰጠው ኦሮሚያ ነው ይህ በዘመነ ኢህአዴግ ነው።

እዛ ላይ ስርዓተ ትምህርቱ ላይ ምን አለ ትምህርት ክፍል ከመጀመሩ በፊት የክልሉ መዝሙር ይዘመራል፤ የክልሉ ባንዲራ ይሰቀላል የሚል አለ።

ይህን ሙሉ ስርዓተ ትምህርቱን በመተግበር ነው 4 ትምህርት ቤቶች (አ/አ ያሉ) የጀመሩት። በውቅቱ አጀንዳ ያደረገውም የለም። በዚህ ምክንያት በተለየ ሁኔታ ኦሮሞ ይጠቀማል ተብሎ የታሰበ ነገር አልነበረም።

ከዛ ተማሪዎች እያደር እየሰፉ መጡ ፣ ከየአካባቢው ፍላጎት ያላቸው ፣ በየአካባቢው ተመዝጋቢ እየበዛ መጣ ኦሮሞም የሆነ ያልሆነ መማር የሚፈልግ እየተመዘገበ መጣ።

እና እንዴት አድርገን ነው የካ ላይ የተመዘገበን ሄደህ ኮልፌ ላይ ነው የምትማረው የምንለው ? ለምን በአካባቢው ላይ ባለ ት/ቤት ክፍል የማንከፍትለት ?

በአካባቢው ትም/ቤት ላይ ፤ በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው መማር እንዲችሉ ትምህርት ቤት እየተከፈተ (በ403 ትምህርት ቤት ውስጥ) በአፋን ኦሮሞ መማር ተጀመረ ሲጀመር ይኸው ካሪኩለም / ስርዓተ ትምህርት ነው አብሮ እየሄደ ያለው።

መማህራኖች፣ ትምህርት ቤቶች እጃቸው ላይ ያለው ስርዓተ ትምህርት እሱ ነው ስርዓተ ትምህርቱን ተግብሩ ተብሎ ስለተሰጣቸው ስርዓተ ትምህርቱ ላይ ያለውን ሙሉ ነገር እየተገበሩ መጡ ይኸው ነው። "

የአ/አ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ፦

" የሆኑ ት/ቤቶች ላይ ይሄንን ቋንቋ አንሰማም የሚል ይህ መዝሙር መዘመር የለበትም የሚል ጥያቄ ያነሳ አለ። ሌላ ትምህርት ቤቶች ላይ በተለይ አፋን ኦሮሞ ተማሪዎች የሚበዙበት ላይ ሌላ ጥያቄ።

በአማርኛ የሚማሩ/ የአፋን ኦሮሞ ተማሪዎች ቁጥር ባነሰበት በባንዲራ መዝሙር አላማው አንድ ያደረገ ግን በተለያየ ስትራቴጂ መጥቶ የከተማውን ሰላማዊ መማር ማስተማር ማደፍረስ ነው። "

ወላጆች እና ተማሪዎች የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት ምን ይላሉ ?

ደስ ታቲሌስ ፦

" ... ትምህርት በ ' #አፍ_መፍቻ_ቋንቋ ' መማር እና የአንድ ክልልን ባንዲራን መስቀልና መዝሙር ማዘመር በጣም የተለያዩ ነገሮች ናቸው። 

ለምሳሌ ያህል ፦ አብዛኛዎችን የትምህርት አይነቶች የምንማረው በእንግሊዘኛ ነው። ነገር ግን የእንግሊዝን መዝሙር አልዘመርንም ፣ ባንዲራቸውም በትምህርት ቤቶቻችን ላይ አልተሰቀለም።

ይህንን ያልኩት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወይንም በመንግስት የተገነቡት ትምህርት ቤቶች ላይ ነው።

የግል ትም/ቤትን አይጨምርም። አሁን ግን የኦሮሚያ ክልል መዝሙር እየተዘመረ እና ባንዲራው እየተሰቀለ ያለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በራሱ ወጪ በሰራቸው ትምህርት ቤቶች ላይ ነው።

ሲቀጥል ቋንቋውን ማስተማርም ካስፈለገ የሌላውን ክልል መዝሙር እንዲዘምሩ በማስደረግ መሆን የለበትም።

በከተማው የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪ የሆኑ ተማሪዎች በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ሲማሩ እኮ የአማራ ክልል ባንዲራ አልተሰቀለም ፤ የአማራ ክልልን መዝሙር አልተዘመረም።

አሁን ላይ እየታየ ያለው ነገር እና ለድርጊቱ የከተማ አስተዳደር እየሰጠ ያለው መልስ ፍፁም የተለያየ ነው። "

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS