Get Mystery Box with random crypto!

🇪🇹 ኢትዮ Students

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiostudents — 🇪🇹 ኢትዮ Students
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiostudents — 🇪🇹 ኢትዮ Students
የሰርጥ አድራሻ: @ethiostudents
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 56.17K
የሰርጥ መግለጫ

Our Bot :
@EthioExamBot
Contact : @ethioexamsupport
Or
@Etssupport

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 19

2022-10-14 20:55:16 የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች ጥቅምት 05 እና 06/2015 ዓ.ም ወደየተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ ይገባሉ።

የተፈታኞች መብቶች፦

➭ ከፈተና ጥያቄ ውጪ ማንኛውንም ያልተረዳውን ነገር ጠይቆ የመረዳት መብት አላቸው።

➭ በዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ የምግብ፣ የህክምና አገልግሎት፣ የማደሪያ ክፍል፣ ፍራሽ እና ትራስ የማግኘት መብት አላቸው።

➭ ማንኛውም ተፈታኝ በዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ያለውን የቤተ መፅሐፍት፣ የመጸዳጃ ቤቶች፣ የሻወር፣ የካፍቴሪያዎች፣ የሚኒ ሱፐር ማርኬቶች፣ የተለያዩ ሱቆች እንዲሁም የመናፈሻና መዝናኛ አገልግሎቶችን የመጠቀም መብት አላቸው።

➭ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ የጋራ የደህንነት ጥበቃ የማግኘት መብት አላቸው።

➭ በፈተና ሰዓት መፈተኛ ክፍል ገብቶ ብርሃናማ የመፈተኛ ቦታ፣ ወንበርና መፃፊያ ጠረጴዛ የማግኘት መብት አላቸው።

➭ ፈተና ከመጀመሩ አንድ ቀን ቀድሞ ስለፈተናው ገለጻ (ኦሬንቴሽን) የማግኘት መብት አላቸው።

የተፈታኞች ግዴታዎች፡-

➤ ማንኛውም ተፈታኝ በፈተና ማዕከልና መፈተኛ ክፍል አድሚሽን ካርድ ይዞ የመገኘት ግዴታ አለበት።

➤ ማንኛውም ተፈታኝ ወደ ዩኒቨርሲቲ ሲመጣ የትምህርት ቤት ወይም የነዋሪነት መታወቂያ ይዞ መገኘት አለበት።

➤ ማንኛውም ተፈታኝ ወደ ግቢ ከመግባቱ በፊትና ወደ መፈተኛ ክፍል ከመግባቱ በፊት ሙሉ አካላዊ ፍተሻ የመፈተሽ ግዴታ አለበት።

➤ ማንኛውም ተፈታኝ በዩኒቨርሲቲ ግቢና በመፈተኛ ክፍል የተከለከሉ ዕቃዎችን መያዝ የለበትም።

➤ ማንኛውም ተፈታኝ እርሳስ፣ ላጲስ እና የእርሳስ መቅረጫ ይዞ መገኘት አለበት።

➤ ማንኛውም ተፈታኝ የፈተና ደንብን ማክበር አለበት።

➤ ማንኛውም ተፈታኝ በፈተና ማዕከል/በመፈተኛ ክፍል ውስጥ የፈተና አስፈጻሚዎች የፈተና አስተዳደር ሥራን ውጤታማ ለማድረግና ሁኔታዎችን ለማመቻቸት የሚያደርጉትን ጥረት የመተባበር ግዴታ አለበት።

➤ ማንኛውም ተፈታኝ ፈተና ከመጀመሩ በፊት መፈተኛ ክፍል የመገኘት ግዴታ አለበት።

➤ ተፈታኙ ፈተናው ሳይጠናቀቅ ከፈተና ክፍል የሚወጣ ከሆነ የፈተና ጥያቄ የያዘውን ቡኩሌት ለፈታኙ የማሰረከብ ግዴታ አለበት።

➤ ማንኛውም ተፈታኝ ወደተመደበበት ዩኒቨርሲቲ ሲመጣ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና የትራስ ጨርቅ ይዞ የመምጣት ግዴታ አለበት።

ለተፈታኞች የተፈቀዱ ነገሮች፦

➣ አዲስ ወይም ቀድሞ ለመማር እና ለማጥናት ሲጠቀሙበት የነበሩ ማስተወሻ ደብተር፣ የትምህርት መፅሐፍ፣ መንፈሳዊ/ኃይማኖታዊ መፅሐፍት፣ ባዶ ወረቀት

➣ ደረቅ ምግቦች (ጭኮ፣ በሶ፣ ዳቦ ቆሎ፣ ቆሎ….)

➣ ገንዘብ (ብር)

➣ ቦርሳ፣ የግል ልብስ፣ ጫማ፣ ...

➣ የግል ንጽህና መጠበቂያዎች (ሳሙና፣ ሞዴስ፣ የጥርስ ብሩሽ፣ የጥርስ ሳሙና፣ ፎጣ፣ ሶፍት፣ ሻምፖ፣ ኮንዲሽነር፣ ሎሽን፣ ቻፕስቲክ፣ የጸጉር ቅባት፣ የፊት ቅባት)

ለተፈታኞች የተከለከሉ ነገሮች፦

➣ ማንኛውንም ዓይነት የጦር መሣሪያ ይዞ መገኘት የተከለከለ ነው፡፡

➣ ማንኛውንም ዓይነት ስለት እና ሹልነት ያላቸውን ብረታ ብረቶችና ጠንካራ ፕላስትኮች ይዞ መገኘት የተከለከለ ነው።

➣ ማንኛውም ድምጽ የሚቀዳ፣ ፎቶ የሚያነሳ፣ ቪዲዮ የሚቀርጽ፣ ከቴሌ መስመርም ሆነ ከቴሌ መስመር ውጭ መልዕክት በዲጂታል መንገድ የሚሰጥ ወይም የሚቀበል የግል ዕቃ/መሳሪያ/የቴክኖሎጂ ውጤት፣ ስልክ፣ አይ-ፓድ፣ ታብሌት፣ ኮምፕዩተር፣ ላፕቶፕ፣ ስማርት ሰዓት፣ ማጂክ ብዕር/እስክሪብቶ፣ ማጂክ ኮት/ጃኬት እና ሌሎች ማንኛቸውም ፎቶ፣ ምስል እና ድምጽ የሚቀርጹ የኤሌክትሮኖክስ መሣሪያዎችን በዩኒቨርሲቲው ግቢ ውስጥም ሆነ ግቢ ዙሪያ ይዞ መገኘት ወይም መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡

➣ በዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ማንኛውንም ዓይነት የግል ፍላሽ ዲስክ፣ ሃርድ ዲስክ፣ ሲዲ፣ ሚሞሪ፣ ሚሞሪ ሪደር፣ ኦ-ቲጂ ኮንቨርተርና መሰል ዕቃዎችን ይዞ መገኘት ወይም መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡

➣ ማንኛውም አደንዛዥ እጾች (ጫት፣ ሲጋራ፣ በሐኪም ማዘዣ የሌለው መድኃኒት)፣ ህክምና መስጫ መርፌ መያዝ ወይም መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡

➣ ማንኛውም ዓይነት የአልኮል መጠጥ ይዞ መገኘት ወይም መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡

➣ ማንኛውም ዓይነት የአንገት ሐብል፣ የጸጉር ጌጥ፣ የጆሮ ጌጥ፣ የጣት ቀለበት፣ የእጅ አንባር፣ አድርጎ ወይም ይዞ መገኘት የተከለከለ ነው፡፡ (ከልሙጥ የጋብቻ ቀለበት በስተቀር)

➣ ፈተና ከተጀመረ ከ30 ደቂቃ በኋላ ወደ ፈተና ክፍል መግባት እና ፈተናው ተጀምሮ 45 ደቂቃ ሳይሞላ ከፈተና ክፍል መውጣት የተከለከለ ነው፡፡

➣ ተፈታኙ ፈተናው ሳይጠናቀቅ ከፈተና ክፍል የሚወጣ ከሆነ የፈተና ጥያቄ የያዘውን ቡኩሌት ይዞ መውጣት ተከለከለ ነው፡፡

➣ በፈተና ሰዓት በመፈተኛ ክፍል ውስጥ ማስቲካ መያዝም ሆነ መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡

➣ በዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ በግልም ሆነ በቡድን መጮህ ወይም በጣም ከፍተኛ ድምጽ ማሰማት የተከለከለ ነው፡፡

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
15.0K views17:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-14 11:59:58
የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች የፈተና የጊዜ ሰሌዳ

የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ዘንድሮ ፈተናው በሀገር አቀፍ ደረጃ ከመስከረም 30/2015 ዓ.ም ጀምሮ በሁለት ዙር በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እንደሚሰጥ ቀደም ብሎ በትምህርት ሚኒስቴር በተገለጸዉ መሰረት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም ፈተናው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፤ በኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ፤ በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ፣ በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና ኢ.ፌ.ዴ.ሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት በመጀመሪያ ዙር ለማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች ተሰጥቶ ተጠናቋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሁለተኛ ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች በነዚሁ ዩኒቨርሲቲዎች ከጥቅምት 08 እስከ 11/2015 ዓ.ም ድረስ ፈተና ይወስዳሉ።

የሁለተኛ ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ፈተና ተፈታኞች የጊዜ ሰሌዳም፦

1. ጥቅምት 6 እና 7/2015 ዓ.ም ተፈታኞች ወደ ተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ ይገባሉ።

2. ጥቅምት 07/2015 ዓ.ም ገለጻ ( ኦሬንቴሽን) ለተፈታኞች ይሰጣል።

3. ከጥቅምት 08 እስከ 11/2015 ዓ.ም ድረስ ፈተናው ይሰጣል።

4.ጥቅምት 11/2015 ዓ.ም ተፈታኞች ወደ አካባቢያቸው ይመለሳሉ።


መልካም ፈተና እንዲሆንላችሁ እንመኛለን

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
13.7K viewsedited  08:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-13 08:03:42 የትምህርት ሚኒስቴር በ12ኛ ክፍል የማህበራዊ ሳይንስ ፈተና አጋጥመዋል ያላቸው 6 ቁልፍ ችግሮች

1- በቂ ኦሬንቴሽን ባለማግኘት ወይም በማወቅም ጭምር የተከለከሉ ቁሶችን ይዘው የመጡና ይዘው የተገኙ ተፈታኞች መኖራቸው፤

2- ነፍሰጡርና መጫት ተፈታኞች በሌላ ዙር እንደሚፈተኑ አስቀድሞ ቢገለፅም በዚህኛው ዙር ለፈተና መምጣታቸው፣

3- በፈተና አዳራሽ በጋራ ካልሰራን ብለው ከፈተና አስፈጻሚዎች ጋር ግብ ግብ የፈጠሩ ተፈታኞች ማጋጠማቸው፤

4- ከተሰጣቸው መመሪያና ከፈታኝ የማይጠበቅ ተግባር ላይ የተሳተፉ የፈተና አስፈፃሚዎች ማጋጠማቸው፤

5- በትራንስፖርት እጥረት ምክንያት ዘግይተውና አምሽተው በዩኒቨርስቲዎች የደረሱ መኖራቸው፤

6- ተማሪዎች ስልክ እንደሌላቸውና ፈተና ቢወጣ እንኳ እንደማያገኙ እየታወቀ ፈተና እንለጥፋለን የሚሉ " የቴሌግራም ገፆች " ማጋጠማቸውና ፈተና ካለቀ ወይም በመሰጠት ላይ እያለ አንድም ሁለትም ገፅ መለጠፋቸው እንደሆነ አመልክቷል።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
14.5K views05:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-13 05:55:34
" መፈተን የፈለገ ይፈተናል ፤ መፈተን ያልፈለገ ትቶ ይሄዳል፤ ትቶ ለሚሄደው ተማሪ ግን ምንም ተጨማሪ ዕድል የሚሰጥበት መንገድ የለም " - ትምህርት ሚኒስቴር

የትምህርት ሚኒስቴር ፤ መውሰድ የነበረባቸውን ፈተና ሙሉ በሙሉ ወይም ውስን ፈተናዎችን ብቻ ወስደው ከዩኒቨርሲቲ ጥለው ወጥተዋል ያላቸው ፦

- ከመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ (መካነ ሰላም ካምፓስ) 1,700 ተማሪዎች

- ከደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ 1,226 ተማሪዎች

- ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ 2,711 ተማሪዎች

- ከደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ 7,150 በአጠቃላይ 12,787 ተማሪዎች ናቸው።

እንዚህ ተማሪዎች ከግቢ የወጡት " ፈተና መፈተን እንደማይፈልጉ " አሳውቀው በመሆኑ በቀጠይ ፈተና እንደማይወስዱ አሳውቋል።

ጥቅምት 8 ፈተና ሚጀምሩት የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ከዚህ ሊማሩ እንደሚገባ የገለፀው ሚኒስቴሩ ፤ " ፈተናውን ተፈትነን አናልፍም ብሎ በመፍራት / በሌላ መንገድ ፈተናውን ለመረበሽ ሲሞከር ዝም ብለው ሌሎችን ተከትሎ መሄድ በራሳቸው ህይወት ላይ አስከፊ የሆነ ነገር ይዞ እንደሚመጣ ማወቅ አለባቸው " ብሏል።

ተማሪዎች በራሳቸው ብቻ ተማምነው እንዲፈቱ ሌሎች አስገድደው አደጋ ያደርሱብኛል ብለው የሚሰጉ ካሉም የተማሪዎችን ደህንነት ማስጠበቅ የትምህርት ሚኒስቴር ስራ ስለሆነ " ደህንነታችሁን እናስጠብቃለን ለዚህም ቃል እንገባለን " ብሏል።

" መፈተን የፈለገ ይፈተናል ፤ መፈተን ያልፈለገ ትቶ ይሄዳል ትቶ ለሚሄደው ግን ምንም ተጨማሪ ዕድል የሚሰጥበት መንገድ የለም " ሲል አሳስቧል።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
13.4K views02:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-12 19:49:52
#Update

ዛሬ በተጠናቀቀው የመጀመሪያው ዙር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከ12 ሺህ በላይ ተማሪዎች ፈተናውን እንዳልወሰዱ የትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

ለፈተናው ከተመዘገቡ 595 ሺህ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ውስጥ 586 ሺህ 541 ተፈታኞች ፈተናውን
እንደወሰዱ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሀኑ ነጋ (ፕ/ር)
ተናግረዋል።

በመቅደላ አምባ፣ ደብረ ማርቆስ፣ ባህር ዳር እና ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲዎች "ከትምህርት ስርዓቱ ባፈነገጠ ሁኔታ አንፈተንም በማለት" 12 ሺህ 787 ተማሪዎች ጊቢውን ለቀው መውጣታቸውን ገልጸዋል።

በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ በደረሰ "ኃይል የተቀላቀለ ግርግር" የአንድ ተማሪ ህይወት ሲያልፍ በፀጥታ አካላት ላይ ጉዳት መድረሱንም አመልክተዋል።

ፈተና አቋርጠው ለወጡ ተማሪዎች ሚኒስቴሩ ምንም አይነት እድል እንደማይሰጥ አሳውቋል።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
13.9K views16:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-12 11:05:28
የመጀመሪያው ዙር የሦሥተኛ ቀን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና እየተሰጠ ነው።

መልካም የፈተና ቀን ውሎ እንዲሆን እንመኛለን!

የማህበራዊ ሳይንስ መስክ የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ዛሬ ፈተናቸውን እንደሚያጠናቅቁ ይጠበቃል።

ፈተናው ከሰኞ መስከረም 30/2015 ዓ.ም ጀምሮ
ሲሰጥ ቆይቷል።

ጥቅምት 03 እና 04/2015 ዓ.ም የመጀመሪያ ዙር ተፈታኞች ወደየአካባቢያቸው ይመለሳሉ።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
13.5K views08:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-11 20:00:28 #Update

በአማራ ክልል ደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ከሚወስዱ ተማሪዎች መካከል ብዙዎቹ በራሳቸው ፈቃድ ፈተናውን ጥለው መውጣታቸውን የከተማ አስተዳደሩ አስታወቀ። በደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ ደግሞ በተማሪዎችና በፈታኞች መካከል በተፈጠረ አለመግባባትና በተፈጠረ ረብሻ ከሰዓት በኋላ የፈተና ሂደቱ መስተጓጎሉን የዓይን እማኝ ገልጠዋል። የደብረማርቆስ ከተማ ተቀዳሚ ከንቲባ ይትባረክ አወቀ ዛሬ ለዶይቼ ቬሌ እንደተናገሩት ከምሥራቅ ጎጃም አንዳንድ ወረዳዎች የመጡ ተማሪዎች «ለተፈታኝ ተማሪ የማይመጥን መፈክር በማሰማት በጠዋት የመፈተኛ ግቢያቸውን ጥለው ወጥተዋል።» ተማሪዎቹ ተረጋግተው ፈተናቸውን እንዲወስዱ የተለያዩ አካላት ጥረት ቢያደርጉም አልተሳካም ብለዋል።
«ተማሪዎቹ ባልተጨበጠ ወሬና በመንደር ፖለቲካ ተጠልፈዋል» ያሉት አቶ ይትባረክ ግቢውን ጥለው ከወጡት ተማሪዎች ውጪ ሌሎች ተረጋግተው፣ እየተፈተኑ መሆኑን ገልጠዋል። ተማሪዎቹ እንደተደበደቡና እንደተዋከቡ የሚናፈሰው ወሬ ከእውነት የራቀ እንደሆነም ተናግረዋል።

ምንጭ፡ዶይቼ ቬሌ

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
4.3K views17:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-11 19:58:33
በደብረታቦር እና ደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ያሉ ተማሪዎች የዛሬውን ፈተና አንፈተንም አሉ

የዛሬውን የ12ኛ ክፍል ፈተና አንፈተንም ሲሉ በደብረታቦር እና በደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲዎች የተመደቡ ተማሪዎች ገለፁ።

በዛሬው እለት የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና መሰጠት ከጀመረ ሁለተኛ ቀኑን የያዘ ቢሆንም ደብረታቦር እና ደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የሚፈተኑ ተማሪዎች ፈተናውን እንዳልወሰዱ ተሰማ።

በሁለቱም ዩኒቨርሲቲዎች የተመደቡ ተፈታኝ ተማሪዎች በትላንትነው እለት ፈተናቸውን የተፈተኑ እና የትላንቱን ውሎ በሰላም ያጠናቀቁ ቢሆንም በዛሬው እለት የሚሰጠውን ፈተና ግን አንወስድም ብለዋል።

አዲስ ዘይቤ ከአካባቢዎቹ የኮምኒኬሽን ቢሮዎች ለማጣራት እንደሞከረችው ተማሪዎቹ ምናልባትም የትላንትናው ፈተና ከባድ ሆኖባቸው ሊሆን እንደሚችል የተገመተ ቢሆንም በአካባቢው ሽማግሌዎች እና የኃይማኖት አባቶች ፈተናውን እንዲወስዱ ለማረጋጋት እየተሞከረ ነው።


ምንም እንኳን አዲስ ዘይቤ ይህንን ቢዘግብም የምስራቅ ጎጃም ዞን የትምህርት መመሪያ ሀላፊ አቶ ጌታሁን ፈንቴ ለ #ብስራትራዲዮ ተፈታኝ ተማሪዎች የጠዋቱን ፈተና በተያዘዉ ሰሌዳ አጠናቅቀዉ የከሰዓቱን መርሐ ግብር በመጠባበቅ ላይ ናቸዉ ብለዋል።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
4.3K views16:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-11 19:58:30 #Update

በአማራ ክልል ደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ከሚወስዱ ተማሪዎች መካከል ብዙዎቹ በራሳቸው ፈቃድ ፈተናውን ጥለው መውጣታቸውን የከተማ አስተዳደሩ አስታወቀ። በደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ ደግሞ በተማሪዎችና በፈታኞች መካከል በተፈጠረ አለመግባባትና በተፈጠረ ረብሻ ከሰዓት በኋላ የፈተና ሂደቱ መስተጓጎሉን የዓይን እማኝ ገልጠዋል። የደብረማርቆስ ከተማ ተቀዳሚ ከንቲባ ይትባረክ አወቀ ዛሬ ለዶይቼ ቬሌ እንደተናገሩት ከምሥራቅ ጎጃም አንዳንድ ወረዳዎች የመጡ ተማሪዎች «ለተፈታኝ ተማሪ የማይመጥን መፈክር በማሰማት በጠዋት የመፈተኛ ግቢያቸውን ጥለው ወጥተዋል።» ተማሪዎቹ ተረጋግተው ፈተናቸውን እንዲወስዱ የተለያዩ አካላት ጥረት ቢያደርጉም አልተሳካም ብለዋል።
«ተማሪዎቹ ባልተጨበጠ ወሬና በመንደር ፖለቲካ ተጠልፈዋል» ያሉት አቶ ይትባረክ ግቢውን ጥለው ከወጡት ተማሪዎች ውጪ ሌሎች ተረጋግተው፣ እየተፈተኑ መሆኑን ገልጠዋል። ተማሪዎቹ እንደተደበደቡና እንደተዋከቡ የሚናፈሰው ወሬ ከእውነት የራቀ እንደሆነም ተናግረዋል።

ምንጭ፡ዶይቼ ቬሌ

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
4.2K views16:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-11 13:22:16


@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
6.8K views10:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ