Get Mystery Box with random crypto!

በደብረታቦር እና ደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ያሉ ተማሪዎች የዛሬውን ፈተና አንፈተንም አሉ የዛሬውን | 🇪🇹 ኢትዮ Students

በደብረታቦር እና ደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ያሉ ተማሪዎች የዛሬውን ፈተና አንፈተንም አሉ

የዛሬውን የ12ኛ ክፍል ፈተና አንፈተንም ሲሉ በደብረታቦር እና በደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲዎች የተመደቡ ተማሪዎች ገለፁ።

በዛሬው እለት የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና መሰጠት ከጀመረ ሁለተኛ ቀኑን የያዘ ቢሆንም ደብረታቦር እና ደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የሚፈተኑ ተማሪዎች ፈተናውን እንዳልወሰዱ ተሰማ።

በሁለቱም ዩኒቨርሲቲዎች የተመደቡ ተፈታኝ ተማሪዎች በትላንትነው እለት ፈተናቸውን የተፈተኑ እና የትላንቱን ውሎ በሰላም ያጠናቀቁ ቢሆንም በዛሬው እለት የሚሰጠውን ፈተና ግን አንወስድም ብለዋል።

አዲስ ዘይቤ ከአካባቢዎቹ የኮምኒኬሽን ቢሮዎች ለማጣራት እንደሞከረችው ተማሪዎቹ ምናልባትም የትላንትናው ፈተና ከባድ ሆኖባቸው ሊሆን እንደሚችል የተገመተ ቢሆንም በአካባቢው ሽማግሌዎች እና የኃይማኖት አባቶች ፈተናውን እንዲወስዱ ለማረጋጋት እየተሞከረ ነው።


ምንም እንኳን አዲስ ዘይቤ ይህንን ቢዘግብም የምስራቅ ጎጃም ዞን የትምህርት መመሪያ ሀላፊ አቶ ጌታሁን ፈንቴ ለ #ብስራትራዲዮ ተፈታኝ ተማሪዎች የጠዋቱን ፈተና በተያዘዉ ሰሌዳ አጠናቅቀዉ የከሰዓቱን መርሐ ግብር በመጠባበቅ ላይ ናቸዉ ብለዋል።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS