Get Mystery Box with random crypto!

#Update በአማራ ክልል ደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ከሚወስዱ ተማሪዎ | 🇪🇹 ኢትዮ Students

#Update

በአማራ ክልል ደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ከሚወስዱ ተማሪዎች መካከል ብዙዎቹ በራሳቸው ፈቃድ ፈተናውን ጥለው መውጣታቸውን የከተማ አስተዳደሩ አስታወቀ። በደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ ደግሞ በተማሪዎችና በፈታኞች መካከል በተፈጠረ አለመግባባትና በተፈጠረ ረብሻ ከሰዓት በኋላ የፈተና ሂደቱ መስተጓጎሉን የዓይን እማኝ ገልጠዋል። የደብረማርቆስ ከተማ ተቀዳሚ ከንቲባ ይትባረክ አወቀ ዛሬ ለዶይቼ ቬሌ እንደተናገሩት ከምሥራቅ ጎጃም አንዳንድ ወረዳዎች የመጡ ተማሪዎች «ለተፈታኝ ተማሪ የማይመጥን መፈክር በማሰማት በጠዋት የመፈተኛ ግቢያቸውን ጥለው ወጥተዋል።» ተማሪዎቹ ተረጋግተው ፈተናቸውን እንዲወስዱ የተለያዩ አካላት ጥረት ቢያደርጉም አልተሳካም ብለዋል።
«ተማሪዎቹ ባልተጨበጠ ወሬና በመንደር ፖለቲካ ተጠልፈዋል» ያሉት አቶ ይትባረክ ግቢውን ጥለው ከወጡት ተማሪዎች ውጪ ሌሎች ተረጋግተው፣ እየተፈተኑ መሆኑን ገልጠዋል። ተማሪዎቹ እንደተደበደቡና እንደተዋከቡ የሚናፈሰው ወሬ ከእውነት የራቀ እንደሆነም ተናግረዋል።

ምንጭ፡ዶይቼ ቬሌ

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS