Get Mystery Box with random crypto!

🇪🇹 ኢትዮ Students

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiostudents — 🇪🇹 ኢትዮ Students
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiostudents — 🇪🇹 ኢትዮ Students
የሰርጥ አድራሻ: @ethiostudents
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 56.17K
የሰርጥ መግለጫ

Our Bot :
@EthioExamBot
Contact : @ethioexamsupport
Or
@Etssupport

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 20

2022-10-10 14:38:10
ማሳሰቢያ
=======
በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ የተመደባችሁ የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ዛሬ ጠዋት በተፈጠረው የድልድይ መውደቅ አደጋ ምክንያት ለዛሬ የታቀዱትን ፈተናዎች መፈተን እንዳልቻላችሁ ይታወቃል:: በተከሰተው ያልተጠበቀ አደጋ በጣም አዝነናል:: ሆኖም ሌሎቻችሁ በሁኔታው ተደናግጣችሁ ከግቢ የወጣችሁም ሆነ እዚሁ የምትገኙ ተማሪዎች ተረጋግታችሁ ወደየነበራችሁበት እንድትመለሱና ለነገ ፈተና እንድትዘጋጁ እናሳስባለን::

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
5.2K views11:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-09 13:27:54
የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች የተቀመጠላቸውን መመሪያ በማክበር ፈተናውን እንዲወስዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ጥሪ አድርገዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለዘንድሮ ተፈታኞቾ ባስተላለፉት መልዕክት፤ "የምትፈተኑት የ12ኛ ክፍል ፈተና ለኢትዮጵያ እውነተኛ ተስፋዎች መሆናችሁን የምታረጋግጡበት እንደሚሆን አምናለሁ" ብለዋል።

"እናንተን እዚህ ለማድረስ ወላጆች፣ መምህራን እና መላው ማኅበረሰብ ለዓመታት ለፍቷል" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ "ኢትዮጵያ እናንተን ስታይ ተስፋ ነው የሚታያት" ሲሉ ገልጸዋል።

"ውጤቱን የምታሳዩት ከኩረጃና ከስርቆት ነጻ ሆናችሁ፣ በራሳችሁ ተማምናችሁ፣ ፈተናውን ስትፈተኑ ነው" ብለዋል።

"የተሰጣችሁን መመሪያ አክብሩ፤ ተረጋግታችሁ ፈተናችሁን ሥሩ፤ በምንም አትሸበሩ፤ የኢትዮጵያ አምላክ ዕውቀቱን ይግለጥላችሁ" ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላፈዋል።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
3.2K views10:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-09 08:44:23
ተማሪዋን እንርዳት...አድሚሽን ካርዷን ባስ ውስጥ ጥላ ወረደች..

የ ጀነራል ዋቆ ጉቱ 2ተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ የሆነቺው እና የፊታችን ሰኞ ሀገር አቀፍ ፈተና የምትወስድ RADIA EDIRIS BUNKA የተሰኘች ተማሪ አድሚሽን ካርዷን ባስ ውስጥ ጥላ ወርዳለች... ያለ አድሚሽን ካርዱ ሀገር አቀፍ ፈተና ላይ መቀመጥ አትችልም ለዚህም ሲባል የ ጀነራል ዋቆ ጉቱ 2ተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የምታውቁ ሰዎች ለትምህርት ቤቷ እንድታሳውቁላት በትህትና እንጥይቃቹዋለን

አድሚሽን ካርዱን 0910222366  ጋር ይገኛል

#Share ያድርጉ

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
4.7K viewsedited  05:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-08 10:41:48
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከ11ዱም ክፍለ ከተማዎች ለተማሪዎች ሽኝት ተካሄደ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ለሚወስዱ ተማሪዎች ወደ ሚፈተኑባቸዉ ዩኒቨርስቲዎች ከ11ዱም ክፍለ ከተማዎች ሽኘት ተደርጎላቸዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፎ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ በአራዳ ክፍለ ከተማ በሚኒሊክ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመገኘት ለተማሪዎች ሽኝት በማድረግ ተማሪዎችን አበረታተዋል፡፡

በሽኝቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ መምህራን ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ ድንቃለም ቶሎሳ እና የክፍለ ከተማዉ ትምህርት ጽፈት ቤት ሀላፊ አቶ ወንድሙ ኡመር በተጨማሪ ተገኝተዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች በዛሬዉ እለት በተዘጋጀላቸው ተሽከርካሪ ወደፈተና ጣቢያዎች ገብተው በዩኒቨርሲቲዎቹ ኦረንቴሽን ተሰቷቸው የፊታችን ሰኞ ፈተናውን መፈተን እንደሚጀምሩ ቀደም ብሎ መገለጹ ይታወቃል።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
4.3K views07:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-07 17:22:25
የ85 ዓመቱ የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ

አቶ ባፋ ባጋጃ ይባላሉ። የ85 ዓመት አዛውንት ናቸው። በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን ከሚወስዱ ተፈታኞች መካከል አንዱ ናቸው።

የስምንት ልጆች አባት የሆኑት አቶ ባፋ፤ በ1949 ዓ.ም የሰባተኛ ክፍል ተማሪ ሆነው ትምህርታቸውን እንዳቋረጡ ይገልጻሉ።

የ85 ዓመቱ አዛውንት በ2009 ዓ.ም ከ66 ዓመት በኋላ ያቋረጡትን ትምህርት በድጋሚ በመጀመር በባይራ ኮይሻ ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ቆይተዋል።

"እውቀት መቅሰም በእድሜ አይገደብም" የሚሉት አቶ ባፋ፤ ዓላማቸው ተምረው ለአገር ውለታ መስራት መሆኑን ለኢዜአ ገልጸዋል።

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ከሀድያ እና ከወላይታ ዞኖች የተውጣጡ ከ30 ሺህ በላይ የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች በመቀበል ላይ ነው።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
5.0K views14:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-06 09:56:33
#For_All_Students
 
@ethioexambot ምን ምን ይዘዋል?

የብሄራዊ ፈተና ውጤቶች

    ቦቶቻችንን የ(2010,2011,2012,2013) የፈተና ውጤቶችን ይዘዋል።
  
የፈተና መዘጋጃ ጥያቄዎች ከ8ኛ - 12ኛ

      ለዘንድሮ ( 2014 ) ተፈታኞች የፈተና መዘጋጃ አዘጋጅተንላችኋል።
      የሁሉም ትምህርት አይነቶች ጥያቄዎችን የምታገኙ ሲሆን
     በሰአት የተገደበ ጥያቄና መልስ (quiz) መልኩ መፈተን ይችላሉ።


የመኪና አሽከርካሪነት ፈቃድ ፈተና

    የDriving license የሁሉም ደረጃ ፈተና እና መልሶች በquiz መልኩ ቀርበዋል።

Resources / አስፈላጊ ነገሮች

     ለሁሉም የትምህርት ደረጃዎች የሚጠቅሙ ዲጂታል መጽሀፍትን የምታገኙበት ክፍል ነው።

| |
| @ethiostudents
| |
4.9K views06:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-05 23:05:14
#ሼር

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት መስከረም 30 ቀን 2015 ዓ/ም ከሚጀምረው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ጋር በተያያዘ የዩኒቨርሲቲ እና ዩኒቨርሲቲ ካምፓሶች አድራሻ አሰራጭቷል ፤ ከላይ ይመልከቱ።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
1.5K views20:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-03 13:34:51 የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን በተሳካ ሁኔታ ለመስጠት ዝግጅት መደረጉ ተገለጸ

የትምህርት ሚኒስቴር የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በዩኒቨርሲቲዎች ለመስጠት ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን ገልጿል፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ  ፈተናውን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።

በመግለጫውም ፈተናው በዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ የሚሰጠው፥ ባለፉት አመታት የፈተና አሰጣጡን ሲያውክ የነበረውን የፈተና ስርቆትና የሃሰተኛ መልስ ስርጭትን ለመከላከል በማሰብ  መሆኑን አስታውቋል።

ለዚህም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሙሉ ዝግጅት  ማድረጉን ነው የገለጸው።

ተፈታኞች በአካባቢያቸው በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ፈተናውን የሚወስዱ ሲሆን በተቀመጡ መመሪያዎች መሰረት የፈተናውን ደህንነት ለማስጠበቅ የተወሰነውን ውሳኔ አክብረው እንዲፈተኑ፤ ወላጆችም ለዚህ አላማ መሳካት አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ተጠይቋል።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
3.5K views10:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-02 10:12:39
#ኢንዶኔዢያ በእግር ኳስ ክለብ ደጋፊዎች በተነሳ ጠብ
127 ደጋፊዎች ሲሞቱ 180 ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፦

በኢንዶኔዥያ ሁለት ክለቦች አረማ እና ፔርሴባያ ባደረጉት ጨዋታ የባለ ሜዳው አረማ 3ለ2 መሸነፉን ተከትሎ ደጋፊዎች ባስነሱት ብጥብጥ /ረብሻ ፖሊስ ረብሻውን ለማርገብ በተጠቀመዉ የአስለቃሽ ጋዝ ምከንያት ደጋፊዎች ለሞት ተዳርገዋል፡፡

እየወጡ ባሉ መረጃዎች መሰረት የስታዲየሙ የመያዝ አቅም 30,000 ሆኖ ሳለ እስከ 42,000 የሚጠጉ ደጋፊዎች ሜዳው ከአቅሙ በላይ መያዙ ፖሊስ አደጋውን ለመቆጣጠር ከባድ አድርጎበታል ተብሏል፡፡

በአጠቃላይ በአደጋው 127 ሰዎች የሞቱ ሲሆን 2 የፖሊስ መኮንኖች መሆናቸው ተረጋግጧል፡፡

34 ደጋፊዎች እዛው በስታዲየሙ ውስጥ የሞቱ ሲሆን ሌሎች ደግሞ በሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ህይወታቸው ማለፉን ታውቋል፡፡

ከወደ ምስራቅ ኢንዶኔዥያ እየወጡ ባሉ መረጃዎች መሰረት ስታዲየሙ ከአቅም በላይ ደጋፊ ማስተናገዱ የአስተዳደሩ እንዝላልነት ነው ሲሉ ለአደጋው መከሰት የስታዲየም አስተዳዳሪዎችን ተጠያቂ አድርገዋል፡፡

የሟቾቹ ቁጥር ከዚህ በላይ ሊያሻቅብ እንደሚችል እየወጡ ያሉ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

መረጃው፦ AFPን ጠቅሶ ፓተርን ስፖርት ነው።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
4.3K viewsedited  07:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-27 16:07:13
ዶ/ር አብይ አህመድ በአርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅ ሞት የተሰማቸውን ሀዘን ገለፁ

አርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅ በማረፉ የተሰማኝ ኀዘን ከባድ ነው። ለሀገሩ በአጭር እድሜው ብዙ የሠራ ከያኒ ነው።  ሀገር በተደፈረች ጊዜ ሕመሙን እየቻለ ግንባር ተገኝቶ ሠራዊቱን አጀግኗል። ሠልጣኞችን አበርትቷል። ነፍሱ በሰላም ትረፍ። 

Via Dr Abiy ahmed

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
391 views13:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ