Get Mystery Box with random crypto!

#ኢንዶኔዢያ በእግር ኳስ ክለብ ደጋፊዎች በተነሳ ጠብ 127 ደጋፊዎች ሲሞቱ 180 ከባድ የአካል | 🇪🇹 ኢትዮ Students

#ኢንዶኔዢያ በእግር ኳስ ክለብ ደጋፊዎች በተነሳ ጠብ
127 ደጋፊዎች ሲሞቱ 180 ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፦

በኢንዶኔዥያ ሁለት ክለቦች አረማ እና ፔርሴባያ ባደረጉት ጨዋታ የባለ ሜዳው አረማ 3ለ2 መሸነፉን ተከትሎ ደጋፊዎች ባስነሱት ብጥብጥ /ረብሻ ፖሊስ ረብሻውን ለማርገብ በተጠቀመዉ የአስለቃሽ ጋዝ ምከንያት ደጋፊዎች ለሞት ተዳርገዋል፡፡

እየወጡ ባሉ መረጃዎች መሰረት የስታዲየሙ የመያዝ አቅም 30,000 ሆኖ ሳለ እስከ 42,000 የሚጠጉ ደጋፊዎች ሜዳው ከአቅሙ በላይ መያዙ ፖሊስ አደጋውን ለመቆጣጠር ከባድ አድርጎበታል ተብሏል፡፡

በአጠቃላይ በአደጋው 127 ሰዎች የሞቱ ሲሆን 2 የፖሊስ መኮንኖች መሆናቸው ተረጋግጧል፡፡

34 ደጋፊዎች እዛው በስታዲየሙ ውስጥ የሞቱ ሲሆን ሌሎች ደግሞ በሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ህይወታቸው ማለፉን ታውቋል፡፡

ከወደ ምስራቅ ኢንዶኔዥያ እየወጡ ባሉ መረጃዎች መሰረት ስታዲየሙ ከአቅም በላይ ደጋፊ ማስተናገዱ የአስተዳደሩ እንዝላልነት ነው ሲሉ ለአደጋው መከሰት የስታዲየም አስተዳዳሪዎችን ተጠያቂ አድርገዋል፡፡

የሟቾቹ ቁጥር ከዚህ በላይ ሊያሻቅብ እንደሚችል እየወጡ ያሉ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

መረጃው፦ AFPን ጠቅሶ ፓተርን ስፖርት ነው።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS