Get Mystery Box with random crypto!

🇪🇹 ኢትዮ Students

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiostudents — 🇪🇹 ኢትዮ Students
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiostudents — 🇪🇹 ኢትዮ Students
የሰርጥ አድራሻ: @ethiostudents
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 56.17K
የሰርጥ መግለጫ

Our Bot :
@EthioExamBot
Contact : @ethioexamsupport
Or
@Etssupport

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 17

2022-12-09 10:37:25 ከኦሮሚያ ሰንደቅ አላማ ጋር በተያያዘ በተነሳ ግጭት የአንድ ተማሪ ህይወት አለፈ! አዲስ ማለዳ አገኘውት ባለው መረጃ በአዲስ አበባ ፈረንሳይ አካባቢ ልዩ ስሙ ጉራራ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ በሚገኘው፣ ከፍተኛ 12 ትምህርት ቤት ከኦሮሚያ ሰንደቅ አላማ ጋር በተያያዘ በተማሪዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት የአንድ ተማሪ ህይወት ማለፉን ተሰምቷል። ከትናንት በስተያ ኀዳር 27/2015 በኦሮሚያ ክልል ሰንደቅ…
6.7K viewsedited  07:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-08 23:37:26 ከኦሮሚያ ሰንደቅ አላማ ጋር በተያያዘ በተነሳ ግጭት የአንድ ተማሪ ህይወት አለፈ!

አዲስ ማለዳ አገኘውት ባለው መረጃ

በአዲስ አበባ ፈረንሳይ አካባቢ ልዩ ስሙ ጉራራ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ በሚገኘው፣ ከፍተኛ 12 ትምህርት ቤት ከኦሮሚያ ሰንደቅ አላማ ጋር በተያያዘ በተማሪዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት የአንድ ተማሪ ህይወት ማለፉን ተሰምቷል።

ከትናንት በስተያ ኀዳር 27/2015 በኦሮሚያ ክልል ሰንደቅ አላማ ምክንያት በተማሪዎች መካከል በተከሰተው ግጭት፣ ከ10 በላይ የትምህርት ቤቱ ተማሪ የመቁሰል አደጋ ጋጥሟቸዋል ተብሏል፡፡ ከተማሪዎች በተጨማሪ አንድ የትምህርት ቤቱ መምህር መጎዳቱን  ምንጮች ጠቁመዋል፡፡

የግጭቱ መነሻ የኦሮሚያ ክልል ሰንደቅ አላማ በትምህርት ቤቱ በመሰቀሉ ቅሬታ ባደረባቸው ተማሪዎች፣ የሰንደቅ አላማውን መሰቀል በሚደግፉ ተማሪዎች መካከል በተፈጠረ ልዩነት ነው ተብሏል፡፡

በዚህም የሰንደቅ አላማውን መሰቀል የማይደግፉ ተማሪዎች እንዲወርድ ፍላጎት ሲያሳዩ፣ በአንጻሩ መሰቀሉን የሚደግፉት ደግሞ ሰንደቅ አላማው አይወርድም የሚል ውዝግብ ውስጥ ገብተው እንደነበር ታውቋል፡፡

በግጭቱ ተሳታፊ ያልሆኑ ተማሪች ጭምር ከሁለቱም ወገን በሚወረወር ድንጋይ ቆስለዋል፡፡

የኦሮሚ ክልል ሰንደቅ አላማውን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ት/ት ቤቶች እንዲሰቀል መንግሥት ከወሰነ በኋላ፣ የተለያዩ አካላት ውሳኔውን  ከመቃወምም አልፈው ወደፊት ችግር ሊፈጥር ይችላል በማለት ስጋታቸውን ሲገልጹ ነበር፡፡

ምንጭ፦ አዲስ ማለዳ

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
8.3K viewsedited  20:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-05 13:25:16 የሞት ፍርድን በተመለከተ  ከህግ ባለሙያዎች  መልስ;

*በመደበኛ ፍርድ ቤት በኢትዮጵያ   የሞት ፍርድ የተወሰነበት ሰው  ለጠቅላይ ፍርድ ቤት እና  ለሰበር ችሎት አቤቱታ የማቅረብ መብት አለው።

*የሞት ፍርድ ከተወሰነ በኋላ አቃቢ ህግ የሞት ፍርዱ እንዲወሰን  የሚጠይቅ ሲሆን ውሳኔ እንዲፈፀም   በሀገሪቱ ፕሬዝዳንት መፈረም አለበት።

*የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሆኖ የሞት ፍርድ እንዲፈፀም የፈረመ  ሰው የለም።

*የሞት ፍርድ ባይፈፀም   ጥፋተኛው ሰው እድሜ ልክ የሚታሰር ሲሆን የእድሜ ልክ  እስር ጣሪያው ደግሞ 25 አመት ነው።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
1.4K viewsedited  10:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-05 13:04:22
#ፍትሕ_ሚኒስቴር

የሁለት ህፃናትን ህይወት በአሰቃቂ ሁኔታ ያጠፋችው ህይወት መኮንን በዛሬው ችሎት ዐቃቤ ህግ በሞት እንድትቀጣ ካለ በኃላ ፦

- ከዚህ ቀደም ወንጀል ፈፅሜ የማላውቅ፣
- ወንጀሉን የፈጸምኩት ከእውቀት ማነስና ያልተማርኩ በመሆኔ መሆኑ፣
- እጄን ለፖሊስ አምኜ የሰጠው በመሆኔ ከግምት ገብቶ ቅጣቱ ይቅለልልኝ በማለት የቅጣት ማቅለያዎችን ከመንግስት በተመደበላት የተከላካይ ጠበቃ አማካኝነት  የጠየቀች ቢሆንም የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ሰው ግድያና ከባድ ውንብድና ወንጀል ችሎት ተከሳሿ ያቀረበችውን ማቅለያዋን #አልተቀበለውም፡፡

ፍርድ ቤቱ ሌሎች አጥፊዎችን ያስጠነቅቃል በማለት ተከሳሿ #በሞት እንድትቀጣ ሲል ወስኖባታል፡፡

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
1.9K views10:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-05 11:24:16
በሞት እንድትቀጣ ተወሰነ

ሁለት ህፃናትን በአሰቃቂ ሁኔታ በመግደል የተከሰሰችው የህይወት መኮንን የሞት ፍርድ ተፈረደባት ።
የአሰሪዎቿን  ሁለት ህጻናት በአሰቃቂ ሁኔታ  ገድላለች  ተብላ የተከሰሰችው  ህይወት መኮንን የተባለችው የቤት ሰራተኛ  ላይ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የከባድ ግድያና የውንብድና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት  በሞት ቅጣት እንድትቀጣ ወሰነ።

ተከሳሽ ህይወት መኮንን ሀይሉ በነሃሴ 26 ቀን 2014 ዓ/ም ከጠኋቱ 3:30 ላይ በለሚኩራ ክ/ከ አራብሳ ኮንዶሚኒዬም  በቤት ሰራተኛነት ተቀጥራ በምትሰራበት መኖሪያ ቤት ውስጥ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ የህጻን ግዮናዊት መላኩ አፏን በማፈን  በቢላ በማረድ ህይወቷ እንዲያልፍ ማድረጓን እና ህጻን ክርስቲና መላኩን ደግሞ አፍፏን በማፈን በማነቅ  በአጠቃላይ ህፃናቶቹን በአሰቃቂ ሁኔታ ህይወታቸው እንዲያልፍ  አድርጋለች ሲል በግድያ ወንጀል እና በወቅቱ የሟች ቤተሰቦችን የሰነድ ማስረጃዎች ቀዳዳ በማጥፋት በአጠቃላይ በተደራራቢ ክስ  በጥቅምት 15 ቀንፐ 2015 ዓ/ም የወንጀል  ክስ ተመስርቶባት እንደነበር ይታወሳል።
(ፎቶ:- በችሎት የተገኙ የሟች ህፃናት ቤተሰቦች)

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
3.3K viewsedited  08:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-02 21:47:25
የሁለኛው ዙር መፈተኛ ቀን ታወቀ!!!

በምዕራብ ሸዋ ዞን ባሉ 7 ወረዳዎች የመጀመሪያ ዙር ፈተና ያልተፈተኑ ሲሆን የሁለተኛው ዙር ፈተና ቀን ታህሳስ 11 2015 እንደሆነ ዛሬ የሸዋ ዞን ትምህርት መመሪያ አረጋግጧል።

ተማሪዎች ወደ መፈተኛ ዩንቨርስቲዎች ከ ታህሳስ 7-9 ይጓጓዛሉ

የተማሪዎች ዉጤት ከታህሳስ 20 እስከ 25 ውስጥ ባሉት ቀናት ያሳውቃል ተቦሏል።

ሌላ የሰላም እና ፀጥታ ችግር ካላጋጠመን በስተቀር ተማሪዎች ከ ጥር መጀመሪያ ጀምሮ ወደ ዩኒቨርስቲ እንዲገቡ ይደረጋል።


@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
6.8K views18:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-02 08:56:59
#ExitExam

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ  ፦

" የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና በሁሉም ዩኒቨርስቲዎች ለሚማሩ የቀን ፣ የማታ እና የርቀት መርሀ ግብር ተመራቂዎች ይሰጣል።

ከዚህ ዓመት ጀምሮ  በመንግስትና ግል ዩኒቨርስቲዎች ተግባራዊ የሚደረገውን የመውጫ ፈተና #በኦንላይን ለመስጠት ታቅዷል ።

በመሆኑም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመሠረተ ልማት አቅሞቻቸውን ከወዲሁ በማረጋገጥ ለፈተናው ተገቢውን ዝግጅት ሊያደርጉ ይገባል ።  "

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
3.6K views05:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-24 19:46:09
#ሰበር

የ12ኛ ክፍል ፈተና ላመለጣችሁ የሀዋሳ እና አካባቢዋ ተማሪዎች በሙሉ

"ተማሪዎች ፈተናውን ለመፈተን ዝግጅት አድርጉ"
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ በተለያየ ምክንያት የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል ላልተፈተኑ ተማሪዎች ፈተናውን በታህሳስ ወር መጀመሪያ ሳምንት ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ትምህርይ መምሪያ አሳውቋል።
- በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ በመሸጋገሪያ ድልድይ ተሰብሮ በደረሰው አደጋ ምክንያት የመጀመሪያውን ቀን ፈተና ያልተፈተኑ፤

- በወሊድ ምክንያት ፈተናውን ያልወሰዱ፤

- የተለያየ ማህበራዊ ችግር አጋጥሟቸው ጉዳዩ ለሚመለከተው አካል አሳውቀው ለፈተና ያልተቀመመጡ ፤

- በሀዋሳ ከተማ ማዕከላዊ ማረሚያ ትምህርት ቤት የሚገኙ ተማሪዎች ፈተናውን ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ነው ብሏል።

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ ፤ " ትምህርት ሚኒስቴር ፈተናውን ላልወሰዱ ተማሪዎች በታህሳስ ወር  2015 ዓ.ም  በመጀሪያ ሳምንት አከባቢ ፈተናው ለመስጠት ቅድመ ዝግጅቱን እያጠናቀቀ ነው " ያለ ሲሆን ተማሪዎች ይህንን አውቀው ፈተናውን ለመፈተን ዝግጅት እንዲያደርጉ አሳስቧል።
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ


@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
1.6K views16:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-23 21:53:57 ነገ ከ 4ቱ university ስለየትኛው እናዘጋጅላችሁ ?

Gonder university
jimma university
bahir dar university
Dembi Dolo university

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
2.8K views18:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-23 21:41:44
#Last_part
ውሃ፤መብራት፤WIFI

መብራት እና ውሃ አይጠፋም ኀለአንዳንድግቢዎች ለልሎች
ይጠፋል።

አሪፍ የሆነ WIFI በግቢ የተለያየ ቦታ ላይ ይገኛል።

ስለዮኒቨርሲቲው


ሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ

ሀገራችን ላይ አሉ ከሚባሉ ዩኒቨርሲቲዎች በትምህርት ጥራቱም ሆነ በግቢ ውበቱ አንደኛ ደረጃ ከሚባሉት
ተርታ የሚመደብ ግቢ ነው።

ትምሮ በተወሰነ መልኩ ሊያጨናንቅ ይችላል ግን በግቢው ውበትና በከተማው ማብለጭለጭ ካልተሸነፋቹህ የትምህርቱ ነገር ሙድ አለው።

የ ካፌ ምግብ

በጣም ጥሩ የሚባል ምግብ ያቀርባሉ..!፤ከብዙ ዮኒቨርሲቲዎች ጥሩ ምግብ የሚሰጥ ካንፓስ ነው።

ከካፌውጪያሉየምግብቤቶችዋጋ የምግብ ዋጋ በaverage ከ40-55 ብር ይደርሳል፥የሁሉም ግቢዎች ዋጋ ይለያያል።

ቡና ምናምን 10ብር
ለተማሪዎች fair በሆነ ዋጋ የሸጣሉ ትንሽ ቢወደድም።

ሽንትቤት

ጥሩ የሚባል ሽንት ቤት አለው ፤ ከብዙ ግቢዎች የሚሻል አይነት ባኞ አለው።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
3.0K viewsedited  18:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ