Get Mystery Box with random crypto!

በሞት እንድትቀጣ ተወሰነ ሁለት ህፃናትን በአሰቃቂ ሁኔታ በመግደል የተከሰሰችው የህይወት መኮን | 🇪🇹 ኢትዮ Students

በሞት እንድትቀጣ ተወሰነ

ሁለት ህፃናትን በአሰቃቂ ሁኔታ በመግደል የተከሰሰችው የህይወት መኮንን የሞት ፍርድ ተፈረደባት ።
የአሰሪዎቿን  ሁለት ህጻናት በአሰቃቂ ሁኔታ  ገድላለች  ተብላ የተከሰሰችው  ህይወት መኮንን የተባለችው የቤት ሰራተኛ  ላይ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የከባድ ግድያና የውንብድና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት  በሞት ቅጣት እንድትቀጣ ወሰነ።

ተከሳሽ ህይወት መኮንን ሀይሉ በነሃሴ 26 ቀን 2014 ዓ/ም ከጠኋቱ 3:30 ላይ በለሚኩራ ክ/ከ አራብሳ ኮንዶሚኒዬም  በቤት ሰራተኛነት ተቀጥራ በምትሰራበት መኖሪያ ቤት ውስጥ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ የህጻን ግዮናዊት መላኩ አፏን በማፈን  በቢላ በማረድ ህይወቷ እንዲያልፍ ማድረጓን እና ህጻን ክርስቲና መላኩን ደግሞ አፍፏን በማፈን በማነቅ  በአጠቃላይ ህፃናቶቹን በአሰቃቂ ሁኔታ ህይወታቸው እንዲያልፍ  አድርጋለች ሲል በግድያ ወንጀል እና በወቅቱ የሟች ቤተሰቦችን የሰነድ ማስረጃዎች ቀዳዳ በማጥፋት በአጠቃላይ በተደራራቢ ክስ  በጥቅምት 15 ቀንፐ 2015 ዓ/ም የወንጀል  ክስ ተመስርቶባት እንደነበር ይታወሳል።
(ፎቶ:- በችሎት የተገኙ የሟች ህፃናት ቤተሰቦች)

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS