Get Mystery Box with random crypto!

#ፍትሕ_ሚኒስቴር የሁለት ህፃናትን ህይወት በአሰቃቂ ሁኔታ ያጠፋችው ህይወት መኮንን በዛሬው ችሎት | 🇪🇹 ኢትዮ Students

#ፍትሕ_ሚኒስቴር

የሁለት ህፃናትን ህይወት በአሰቃቂ ሁኔታ ያጠፋችው ህይወት መኮንን በዛሬው ችሎት ዐቃቤ ህግ በሞት እንድትቀጣ ካለ በኃላ ፦

- ከዚህ ቀደም ወንጀል ፈፅሜ የማላውቅ፣
- ወንጀሉን የፈጸምኩት ከእውቀት ማነስና ያልተማርኩ በመሆኔ መሆኑ፣
- እጄን ለፖሊስ አምኜ የሰጠው በመሆኔ ከግምት ገብቶ ቅጣቱ ይቅለልልኝ በማለት የቅጣት ማቅለያዎችን ከመንግስት በተመደበላት የተከላካይ ጠበቃ አማካኝነት  የጠየቀች ቢሆንም የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ሰው ግድያና ከባድ ውንብድና ወንጀል ችሎት ተከሳሿ ያቀረበችውን ማቅለያዋን #አልተቀበለውም፡፡

ፍርድ ቤቱ ሌሎች አጥፊዎችን ያስጠነቅቃል በማለት ተከሳሿ #በሞት እንድትቀጣ ሲል ወስኖባታል፡፡

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS