Get Mystery Box with random crypto!

🇪🇹 ኢትዮ Students

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiostudents — 🇪🇹 ኢትዮ Students
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiostudents — 🇪🇹 ኢትዮ Students
የሰርጥ አድራሻ: @ethiostudents
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 56.17K
የሰርጥ መግለጫ

Our Bot :
@EthioExamBot
Contact : @ethioexamsupport
Or
@Etssupport

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 21

2022-09-27 15:43:48
ድምጻዊ ማዲንጎ አፈወርቅ ከዚህ አለም በሞት ተለየ

ተወዳጁ ድምጻዊ ማዲንጎ አፈወርቅ አርፏል ሲል የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘግቧል።

ድምጻዊው ባደረበት ህመም ምክንያት ማረፉን የቅርብ ወዳጆቹ ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ በተፈተነችበት ወቅት እያመመው ግንባር ድረስ በመሔድና ማሰልጠኛም ምልምሎችን በማነቃቃት የራሱ የሆነ ታሪክ የሰራ አርቲስት ነበር።

Via ኢፕድ

https://t.me/ethiogeeks
https://t.me/ethiogeeks
1.6K views12:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-26 12:49:45 #ብሔራዊ_ፈተና

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ኮማንድ ፖስት በፈተናው ቅድመ ዝግጅት ዙሪያ ውይይት አካሂዷል።

በውይይቱ ፦
• የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ፣
• የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ማኔጅመንት አባላት ፣
• የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፣
• የኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ፣
• የኢትዮጵያ የሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ፣
• የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ
• የፌደራል ቴክኒክና እልጠና ኢንስቲትዩት ሀላፊዎች እና የክ/ከተማ የትምህርት ጽ/ቤት ሀላፊዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከመስከረም 30 ጀምሮ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እንደሚሰጥ ቀደም ብሎ በትምህርት ሚኒስቴር የተገለጸ ሲሆን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፈተናውን ፦

- አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፤
- ኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ፤
- ኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ፣
- አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ
- ፌደራል ቴክኒክና እልጠና ኢንስቲትዩት ለመስጠት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ መሆኑ በውይይቱ ላይ ተገልጻል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የፈተና ዝግጅት እና አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ ዲናኦል ጫላ የተፈታኞችን መብትና ግዴታዎች አቅርበዋል።

#የተፈታኞች_መብቶች_የሆኑት፡- 

➭ ከፈተና ጥያቄ ውጪ ማንኛውንም ያልተረዳውን ነገር ጠይቆ የመረዳት መብት አላቸው።

➭ በየኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ምግብ፣ የህክምና አገልግሎት፣ የማደሪያ ክፍል፣ ፍራሽና ትራስ የማግኘት መብት አላቸው።

➭ ማንኛውም ተፈታኝ በዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ያለውን የቤተ መጽሐፍት፣ የመጸዳጃ ቤቶች፣ የሻወር፣ የካፍቴሪያዎች፣ የሚኒ ሱፐር ማርኬቶች፣ የተለያዩ ሱቆች፣ የመናፈሻና መዝናኛ አገልግሎቶችን የመጠቀም መብት አላቸው።

➭ የኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ የጋራ የደህንነት ጥበቃ የማግኘት መብት አላቸው።

➭ በፈተና ሰዓት መፈተኛ ክፍል ገብቶ ብርሃናማ የመፈተኛ ቦታ፣ ወንበር፣ መጻፊያ ጠረጴዛ የማግኘት መብት አላቸው።

➭ ፈተና ከመጀመሩ አንድ ቀን ቀድሞ ስለፈተናው ገለጻ (ኦሬንቴሽን) የማግኘት መብት አላቸው።

#የተፈታኞች_ግዴታ_የሆኑት፡-

➤ ማንኛውም ተፈታኝ በፈተና ማዕከልም ይሁን መፈተኛ ክፍል አድሚሽን ካርድ ይዞ የመገኘት ግዴታ አለበት።

➤ ማንኛውም ተፈታኝ ወደ ዩኒቨርሲቲ ሲመጣ የትምህርት ቤት #ወይም የነዋሪነት መታወቂያ ይዞ መገኘት አለበት።

➤ ማንኛውም ተፈታኝ ወደ ግቢ ከመግባቱ በፊትና ወደ መፈተኛ ክፍል ከመግባቱ በፊት ሙሉ አካላዊ ፍተሻ የመፈተሽ ግዴታ አለበት።

➤ ማንኛውም ተፈታኝ በዩኒቨርሲቲ ግቢና በመፈተኛ ክፍል የተከለከሉ ቁሳቁሶችን/ዕቃዎችን መያዝ የለበትም።

➤ ማንኛውም ተፈታኝ እርሳስ፣ ላጲስና የእርሳስ መቅረጫ ይዞ መገኘት አለበት።

➤ ማንኛውም ተፈታኝ የፈተና ደንብን የማክበር ግዴታ አለበት።

➤ ማንኛውም ተፈታኝ በፈተና ማዕከል ውስጥና በመፈተኛ ክፍል ውስጥ የፈተና አስፈጻሚዎች የፈተና አስተዳደር ሥራን ውጤታማ ለማድረግና ሁኔታዎችን ለማመቻቸት የሚያደርጉትን ጥረት የመተባበር ግዴታ አለበት።

➤ ማንኛውም ተፈታኝ ፈተና ከመጀመሩ በፊት መፈተኛ ክፍል የመገኘት ግዴታ አለበት።

➤ ተፈታኙ ፈተናው ሳይጠናቀቅ ከፈተና ክፍል የሚወጣ ከሆነ የፈተና ጥያቄ የያዘውን ቡኩሌት ለፈታኙ የማሰረከብ ግዴታ አለበት።

➤ ማንኛውም ተፈታኝ ወደ ተመደበበት ዩኒቨርሲቲ  ሲመጣ  አንሶላ፣  ብርድልብስና  የትራስ  ጨርቅ ይዞ የመምጣት ግዴታ አለበት።

➤ #ዩኒፎርም ለብሶ መገኘት አለበት።

#ለተፈታኞች_የተፈቀዱ_ነገሮች ፦

➣ አዲስ ወይም ቀድሞ ለመማር እና ለማጥናት ሲጠቀሙበት የነበሩ ማስተወሻ  ደብተር ፣ የትምህርት መጽሐፍ፣ መንፈሳዊ/ኃይማኖታዊ መጽሐፍት፣ ባዶ ወረቀት

➣ ደረቅ ምግቦች ወይም ሰንዱች ምግቦች (ጩኮ፣ በሶ፣ ዳቦ ቆሎ፣ ቆሎ….)

➣ ገንዘብ (ብር)

➣ የልብስ ወይም የእጅ ቦርሳ፣ የግል ልብስ፣ ጫማ

➣ የግል ንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ (ሳሙና፣ ሞዴስ፣ የጥርስ ብሩሽ፣ የጥርስ ሳሙና፣ የገላ ማድረቂያ ፎጣ፣ ሶፍት፣ ሻምፖ፣ ኮንዲሽነር፣ ሎሽን፣ ቻፕስቲክ፣ የጸጉር ቅባት፣ የፊት ቅባት)

#ለተፈታኞች_የተከለከሉ_ነገሮች ፦

⮕ ማንኛውንም ዓይነት የጦር መሣሪያ ይዞ መገኘት የተከለከለ ነው፡፡

⮕ ማንኛውንም ዓይነት ስለት እና ሹልነት ያላቸውን ብረታ ብረቶችና ጠንካራ ፕላስትኮች ይዞ መገኘት የተከለከለ ነው።

⮕ ማንኛውም ድምጽ የሚቀዳ፣ ፎቶ የሚያነሳ፣ ቪዲዮ የሚቀርጽ፣ ከቴሌ መስመርም ሆነ ከቴሌ መስመር ውጭ መልዕክት በዲጂታል መንገድ የሚሰጥ ወይም የሚቀበል የግል ዕቃ/መሳሪያ /ቴክኖሎጂ ውጤት፣ ስልክ፣ አይ-ፓድ፣ ታብሌት፣ ኮምፕዩተር፣ ላፕቶፕ፣ ስማርት ሰዓት፣ ማጂክ ብዕር/እስክሪብቶ፣ ማጂክ ኮት/ጃኬት እና  ሌሎች  ማንኛቸውም  ፎቶ፣  ምስል  እና  ድምጽ የሚቀርጹ የኤሌክትሮኖክስ መሣሪያዎችን በዩኒቨርሲቲው ግቢ ውስጥም ሆነ ግቢ  ዙሪያ  ይዞ መገኘት ወይም መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡

⮕ በዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ማንኛውንም ዓይነት የግል ፍላሽ ዲስክ፣ ሃርድ ዲስክ፣ ሲዲ፣ ሚሞሪ፣ ሚሞሪ ሪደር፣ ኦ-ቲጂ ኮንቨርተርና መሰል ዕቃዎችን ይዞ መገኘት  ወይም  መጠቀም  የተከለከለ ነው፡፡

⮕ ማንኛውም አደንዛዥ እጾች (ጫት፣  ሲጋራ፣  በሓኪም  ማዘዣ  የሌለው  መድኃኒት  (በሽሮፕም ይሁን በታብሌት፣ ህክምና መስጫ መርፌ)) መያዝ ወይም መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡

⮕ ማንኛውም ዓይነት የአልኮል መጠጥ ይዞ መገኘት ወይም መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡

⮕ ማንኛውም ዓይነት የአንገት ሐብል፣ የጸጉር ጌጥ፣ የጆሮ ጌጥ፣ የጣት ቀለበት፣ የእጅ አንባር፣ አድርጎ ወይም ይዞ መገኘት የተከለከለ ነው፡፡ (ከልሙጥ የጋብቻ ቀለበት በስተቀረ)

⮕ ፈተና ከተጀመረ ከ30 ደቂቃ በኋላ ወደ ፈተና ክፍል መግባት እና ፈተናው ተጀምሮ  45 ደቂቃ ሳይሞላ ከፈተና ክፍል መውጣት የተከለከለ ነው፡፡

⮕ ተፈታኙ ፈተናው ሳይጠናቀቅ ከፈተና ክፍል የሚወጣ ከሆነ የፈተና ጥያቄ የያዘውን ቡኩሌት ይዞ መውጣት ተከለከለ ነው፡፡

⮕ በፈተና ሰዓት በመፈተኛ ክፍል ውስጥ ማስቲካ መያዝም ሆነ መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡

⮕ በዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ በግልም ሆነ በቡድን መጮህ ወይም በጣም ከፍተኛ ድምጽ ማሰማት የተከለከለ ነው፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 49,203 ተማሪዎች ፈተናውን ለመውሰድ የተመዘገቡ ሲሆን ፈተናው ከመስከረም 30 ጀምሮ በቅድሚያ የሶሻል ሳይንስ ተማሪዎች ተፈትነው ሲጨርሱ የናቹራል ሳይንስ ተማሪዎች ቀጥለው ይፈተናሉ ፤ ተፈታኝ ተማሪዎች በፈተና ወቅት የምግብና የመኝታ አገልግሎቶችን በየተቋማቱ ያገኛሉ።

(የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ)

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
4.7K viewsedited  09:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-23 11:32:18
#ብሔራዊ_ፈተና

ከመፈተኛ ዩኒቨርሲቲ ከ50 ኪሎ ሜትር በላይ ለሆኑ የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች የትራንስፖርት ወጪን ትምህርት ቤቶቻቸው የሚገኙባቸው ወረዳዎች እንደሚሸፍኑ የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታውቋል።

ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 17 ቀን 2015 ዓ.ም በሁለት ዙር ለሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ፈተና በቂ ቅድመ ዝግጅት መደረጉን አገልግሎቱ ገልጿል።

የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር እሸቱ ከበደ ለ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት (ኤፍ ቢ ሲ) የሰጡት ቃል ፦

- ፈተና ማተም ጨምሮ ሌሎች አስፈላጊ ዝግጅቶች ከወዲሁ ተጠናቀዋል።

- ከመፈተኛ ዩኒቨርሲቲዎች በ50 ኪሎሜትር ርቀት ውስጥ ያሉ ተፈታኝ ተማሪዎች የትራንስፖርት ወጪን በራሳቸው ይሸፍናሉ፤ ከ50 ኪሎ ሜትር ርቀት #በላይ የሚገኙ ተማሪዎች ደግሞ ትምህርት ቤቶቻቸው የሚገኙባቸው ወረዳዎች ወጪያቸውን ይሸፍናሉ።

- ተፈታኝ ተማሪዎች መያዝ የሚፈቀዱላቸው ፦

• መጽሐፍት፣
• ሲያጠኗቸው የነበሩ ማስታወሻወች፣
• የንጽህና መጠበቂያዎች
• የሌሊት ልብስ ከተፈቀዱት ቁሳቁስ መካከል ናቸው።

ተማሪዎች ማንነታቸውን የሚገልጽ የቀበሌ መታወቂያ ፣ የመፈተኛ ካርድ ወይም አድሚሽን ካርድ መያዝ ይኖርባቸዋል።

- ተፈታኝ ተማሪዎች መያዝ የሚከለከሏቸው ቁሳቁስ፦

• ማንኛውንም የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣
• ከጋብቻ ቀለበት ውጪ የተለየ ፈርጥ ያላቸው ቀለበቶች፣
• ሀብሎች ፣
• የጸጉር ጌጦች
• ድምጽ የሚያወጡ ጃኬቶች መያዝ አይቻልም።

- የመፈተኛ ዩኒቨርሲቲዎች ለተፈታኝ ተማሪዎች የመኝታና የምግብ አገልግሎት ያመቻቻሉ።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
5.9K views08:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-22 10:42:02 ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በሙሉ

የሁለተኛ ደረጃ ማጠናቀቂያና ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ተፈታኞች በሙሉ:-

2014/15 የኢትዮ ዩኒቨርሲቲ መግቢያና
የሁለተኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ ፈተና ተፈታኞች ወደ ተመደቡበት ካምፖስ ጉዞ ሲያደርጉ #መያዝ #የተፈቀደላቸው፣#መያዝ #የተከለከሉ እና #የጊዜ #ሠሌዳ እንደሚከተለው ያለው ሲሆን ተማሪዎች ከወዲሁ ራሣችሁን እንድታዘጋጁ ይሁን።

❶#መያዝ #የተፈቀደላቸው
አንሶላ፣
ትራስ ጨርቅ፣
የማታ ልብስ፣
ደረቅ ምግብ፣
ልብስ፣ቦርሳ፣
የመፈተኛ ካርድ፣እርሳስ፣ላጲስ፣የማስታወሻ ደብተር፣ባዶ ወረቀት፤መጽሐፍ

❷፣#መያዝ #የተከለከሉ
ማንኛውም ድምፅ የሚቀዳ፤ቪዲዮ የሚቀዳ ወይም ፎቶግራፍ የሚያነሳ፤
ካሜራ
ማንኛውም ከቴሌ መስመርም ይሁን ከቴሌ ውጭ መልዕክት በድጂታል ቴክኖሎጂ መቀበያ ወይም ማስተላለፊያ ውጤቶች(ታብሌት፣ኮሚፕዩተር፣ላብቶፕ፣ ስልክ፣አይፓድ፥ሃርድ ዲስክ፣ፍላሽ)

❸ #የጊዜ #ሠሌዳ
ማህበራዊ ሳይንስ $social science dep't
➤26_28/1/2015 ዩኒቨርስቲ መግቢያ
➤29/01/2015 ኦሬንተሽን
➤30/01/2015_02/02/2015 ፈተናው የሚሰጥበት ጊዜ ይሆናል።

የተፈጥሮ ሳይንስ Natural Science dep't
➤05_06/2/2015 ዩኒቨርስቲ መግቢያ
➤07/02/2015 ኦሬንተሽን
➤08/02/2015_11/02/2015 ፈተናው
የሚሰጥበት ጊዜ ይሆናል።

ትምህርት ሚኒስቴር

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
10.1K views07:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-19 13:51:10
ወደ 9677 OK ብለው ይላኩ,የቴክኖሎጂ ትምህርቶችን እየተማሩ ያልተገደበ የኢንተርኔትና የድምፅ ጥቅል ያሸንፉ!!

የዚህ ሳምንት ሽልማት ያልተገደበ የኢንተርኔት ጥቅል(package)።

ጥቅሉን ለማሸነፍ:

ወደ 9677 OK ብለው ይላኩ።

የሳምንቱ ዕጣ አሸናፊ ከሆኑ የኢንተርኔት ጥቅል ወይም የድምፅ ጥቅል ወደ ስልኮ ይላክሎታል::

መልካም እድል
13.3K views10:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-19 10:13:05
ውድ ተማሪዎች እና መምህራን!

የ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ዛሬ የተጀመረ ሲሆን ተማሪዎች እና መምህራን እንዲሁም የትምህርት ማህበረሰብ እንኳን ለ 2015ዓ.ም የትምህርት ዘመን በሰላም አደረሳችሁ እንላለን።

ሁላችንም እድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህፃናትን ወደ ትምህርት ቤት በመላክ የበኩላችንን እንወጣ!!!

መልካም የትምህርት ዘመን

ትምህርት ሚኒስቴር!
11.6K views07:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-17 20:28:47
በ4ኛ ክፍል የሂሳብ መፅሐፍ ላይ አለ ተብሎ እየተሰራጨ ያለው መረጃ የሀሰት ነዉ ተባለ

በዛሬው እለት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ያዘጋጃቸውን አዳዲስ የመማርያ መጻሕፍት ይፋ ማድረጉንና ርክክብ መፈፀሙ አስታውቋል፡፡

ይፋ በተደረገውና በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት መሰረት የ4ኛ ክፍል የሂሳብ መጻሕፍት ገፅ 18 ላይ የግእዝ ቁጥርን አስመልክቶ ወጥቷል ተብሎ የተገለፀው ሃሳብ በመፅሐፍ ውስጥ የማይገኝ ሆነ ተብሎ የሃሰት መረጃ በማሰራጨት ውዥንብር ሊፈጥሩ በሚፈልጉ አካላት የተፈበረከ መሆኑ ተገልጿል። ይህንንም በዛሬው እለት መምህራኑ ራሳቸው በምረቃው ስነ-ስርዓት ላይ ማረጋገጣቸው ቢሮው አስታውቋል፡፡

እነኚህ አዳዲስ መጻሕፍት ከትምህርት መጀመር ቀደም ብሎ ህትመቱ ተጠናቆ  በሁሉም ትምህርት ቤቶች እየተሰራጩ ያሉ   ሲሆኑ ህብረተሰቡም ከእንዲህ አይነት የተሳሳቱ ውዥንብሮች ራሳችሁን ጠብቁ ሲል ቢሮው መልዕክት አስተላልፏል።
  
@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
14.2K views17:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-17 12:40:05 አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ይዟቸው የመጡ አዳዲስ ነገሮች ምን ምን ናቸው ?

አምስት ዓመታትን በፈጀውና ከ3 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ የማህበረሰብ ክፍሎች የተሳተፉበት ስርዓተ ትምህርት ክለሳ የያዛቸው አዳዲስ ነገሮች ፦

ስርዓተ ትምህርቱ በሁሉም የአገሪቱ ክፍል ባሉ የግል እና  የመንግስት ትምህርት ቤቶች የሚተገበር ቢሆንም፤ ኢንተርናሽናልና የማህበረሰብ አቀፍ ትምህርትቤቶችን አያካትትም፤

በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ግብረ ገብ፣ አገር በቀል ዕውቀት፣ ሙያና የቀለም ትምህርት፣ ቴክኖሎጂ፣ ምርትና ተግባር፣ ጥናትና ምርምር ትኩረት ተደርጎባቸው እንዲሰጡ ይሆናሉ፤

ከአንደኛ እስከ ስድስተኛ ክፍል ላሉ የክፍል ደረጃዎች ትምህርት በአፍ መፍቻ ቋንቋ  ይሰጣል፤

ከሰባተኛ ክፍል እስከ12ኛ ክፍል ያሉት ደግሞ ሁሉም ተማሪ በእንግሊዘኛ ቋንቋ ይማራል፤

ከአንደኛ ክፍል ጀምሮ እስከ12ኛ ክፍል ድረስ ያሉት ተማሪዎች የእንግሊዘኛ ቋንቋን እንደ አንድ የትምህርት ዓይነት ይወስዳሉ፤

ሦስተኛ ክፍል ላይ ተጨማሪ ቋንቋዎችን መስጠት ይጀመራል፤  በክልሎቹ ውስጥ በስፋት የሚነገረውን ተጨማሪ ቋንቋ በመምረጥ ተማሪዎቹ እንደ አንድ የትምህርት አይነት እንዲወስዱት ይደረጋል፤ 

በቀድመው የትምህርት ሥርዓት 10ኛ ክፍል ይሰጥ የነበረው አገራዊ የመልቀቂያ ፈተና ይቀርና በምትኩ አጠቃላይ ፈተናው በክልል ደረጃ ስድስተኛ ክፍል እንዲሁም በአገር አቀፍ ደረጃ ስምንተኛ እና 12ኛ ክፍል ላይ ይሰጣል፤

ከዚህ ቀደም ሦስት ዓመት የነበረው የተማሪዎች የዩኒሸርስቲ ቆይታ ደግሞ ዝቅተኛዉ አራት ዓመት ይደረጋል፤
ለሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ተማሪዎች በመጀመሪያ ዓመት ከሚሠጡ ትምህርቶች ውስጥ እንደ ጂኦግራፊ፣ አንትሮፖሎጂ፣ ሶሺዮሎጂና ሥነ-ምግባር የመሳሰሉት ይካተታሉ፤

ከአንደኛ እስከ ስድስተኛ ክፍል የግብረገብ ትምህርት ይሰጣል፤  በተጨማሪም የማህበራዊና የተፈጥሮ ሳይንስ ውህድ የሆነ ትምህርት ይሰጣል፤ 

ሰባተኛና ስምንተኛ ክፍል በተናጠል ይሰጡ የነበሩት ፊዚክስ፣ ኬሚስትሪና ባይሎጂ  አጠቃላይ ትምህርት ወይም ጀነራል ሳይንስ ተብለው እንዲሁም ጆግራፊና ሂስትሪም ተቀናጅተው የሚሰጡ ይሆናል፤

የሰባተኛና ስምንተኛ ክፍል ተማሪዎች የእርሻ ትምህርት፣ አካውንቲንግ፣ ቢዝነስና ጀነራል የሆነውን የሥራና ክህሎት ትምህርት በሙያ ትምህርት ተካቶላቸው የሚሰጣቸው ይሆናል፤

11ኛ እና 12ኛ ክፍሎች ላይ ደግሞ ጤና ፣ ግብርና፣ የእርሻ ትምህርት፣ ማኒፋክቸሪንግ፣ ኮንስትራክሽን፣ ቢዝነስ፣ አካውንቲንግ የመሳሰሉት የሙያ ትምህርትነቶችን እንዲማሩ ይደረጋል፤

የዘጠነኛና የአስረኛ ክፍልን እንዲሁም  ከአንድ እስከስምንተኛ ክፍል ያሉ የተመረጡ አምስት የትምህርት አይነቶችን መጸሐፍት ዝግጅት ትምህርት ሚኒስቴር ያከናውነዋል፤  

ከአንደኛ እስከ ስምንተኛ ክፍል ያለውን የትምህርት መፀሐፍት ክልሎች በራሳቸው ባህልና አካባቢያዊ ሁኔታ ቃኝተው ያዘጋጁታል፤

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት (በጽጌረዳ ጫንያለው)

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
13.1K viewsedited  09:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-14 11:26:36
የ12ኛ ክፍል ፈተናን በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ መስጠቱ ፋይዳው ምንድነው ?

በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በዩኒቨርሲቲዎች መሰጠቱ በርካታ ጠቀሜታዎች እንደሚኖሩት  የፈተናዎች አገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር እሸቱ ከበደ ገልፀዋል፡፡

ዶ/ር እሸቱ ከበደ ፦

- የፈተና ስርቆትና ኩረጃ  ላይ ከፍተኛ ቁጥጥር በማድረግ ተማሪዎች የራሳቸውን ብቻ እንዲሰሩ አስተዋጽኦ ይኖረዋል።

- ፈተናውን በማጓጓዝ ወቅት የሚያጋጥሙ ችግሮችንም ለመፍታት ትልቅ እገዛ ይኖረዋል።

- የፈተናውን ሂደት ለማበላሸት ጥረት ከሚያደርጉ ሰዎች ለመጠበቅ ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል።

- ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ መፈተናቸው ቀድመው ዩኒቨርሲቲዎቹን በአካል እንዲያውቋቸው ያደርጋል ብለዋል።

ለፈተናው ተማሪዎች ተገቢውን ዝግጅት እንዲያደርጉና ወላጆችም አስፈላጊውን ድጋፍ ለልጆቻቸው እንዲያደርጉ ዋና ዳይሬክተሩ ጠይቀዋል።

የ2014ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሁለት ዙር በዩኒቨርሲቲዎች ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ እንዳለ ይታወቃል፡፡

(ትምህርት ሚኒስቴር)

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
19.3K views08:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-14 11:24:08
በአዲስ አበባ 49,203 ተማሪዎች ፈተናውን ለመውሰድ ተመዝግበዋል የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ቅድመ ዝግጅት ዙሪያ ፈተናው ከሚሰጥባቸው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አመራሮች ጋር ውይይት አካሂዷል።

ዘንድሮ ፈተናው በሀገር አቀፍ ደረጃ ከመስከረም 30/2015 ዓ.ም ጀምሮ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እንደሚሰጥ ቀደም ብሎ በትምህርት ሚኒስቴር የተገለጸ ሲሆን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም ፈተናውን ፦

- አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
- ኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ
- ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ
- አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ለመስጠት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ መሆኑ ተገልጻል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ዘንድሮ ፈተናው ለመጀመሪያ ጊዜ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚሰጥ እንደመሆኑ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የፈተና ሂደቱ በስኬት እንዲጠናቀቅ የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን በመስራት ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

ፈተናው የተማሪዎችን የቀጣይ የህይወት ምዕራፍ የሚወስን በመሆኑ በአዲስ አበባ ፈተናው የሚሰጥባቸው ተቋማትም ሆኑ ሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል፡፡

በአዲስ አበባ 49,203 ተማሪዎች ፈተናውን ለመውሰድ መመዝገባቸውንና ፈተናውም ከመስከረም 30 ጀምሮ በቅድሚያ የሶሻል ሳይንስ ተማሪዎች ተፈትነው ሲጨርሱ የናቹራል ሳይንስ ተማሪዎች ቀጥለው እንደሚፈተኑ የተገለጸ ሲሆን ተፈታኝ ተማሪዎች በፈተና ወቅት የምግብና የመኝታ አገልግሎቶች በየተቋማቱ እንደሚያገኙም ተጠቁማል።

የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
15.2K views08:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ