Get Mystery Box with random crypto!

የ12ኛ ክፍል ፈተናን በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ መስጠቱ ፋይዳው ምንድነው ? በ2014 ዓ.ም የ12ኛ | 🇪🇹 ኢትዮ Students

የ12ኛ ክፍል ፈተናን በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ መስጠቱ ፋይዳው ምንድነው ?

በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በዩኒቨርሲቲዎች መሰጠቱ በርካታ ጠቀሜታዎች እንደሚኖሩት  የፈተናዎች አገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር እሸቱ ከበደ ገልፀዋል፡፡

ዶ/ር እሸቱ ከበደ ፦

- የፈተና ስርቆትና ኩረጃ  ላይ ከፍተኛ ቁጥጥር በማድረግ ተማሪዎች የራሳቸውን ብቻ እንዲሰሩ አስተዋጽኦ ይኖረዋል።

- ፈተናውን በማጓጓዝ ወቅት የሚያጋጥሙ ችግሮችንም ለመፍታት ትልቅ እገዛ ይኖረዋል።

- የፈተናውን ሂደት ለማበላሸት ጥረት ከሚያደርጉ ሰዎች ለመጠበቅ ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል።

- ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ መፈተናቸው ቀድመው ዩኒቨርሲቲዎቹን በአካል እንዲያውቋቸው ያደርጋል ብለዋል።

ለፈተናው ተማሪዎች ተገቢውን ዝግጅት እንዲያደርጉና ወላጆችም አስፈላጊውን ድጋፍ ለልጆቻቸው እንዲያደርጉ ዋና ዳይሬክተሩ ጠይቀዋል።

የ2014ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሁለት ዙር በዩኒቨርሲቲዎች ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ እንዳለ ይታወቃል፡፡

(ትምህርት ሚኒስቴር)

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS