Get Mystery Box with random crypto!

በአዲስ አበባ 49,203 ተማሪዎች ፈተናውን ለመውሰድ ተመዝግበዋል የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ | 🇪🇹 ኢትዮ Students

በአዲስ አበባ 49,203 ተማሪዎች ፈተናውን ለመውሰድ ተመዝግበዋል የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ቅድመ ዝግጅት ዙሪያ ፈተናው ከሚሰጥባቸው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አመራሮች ጋር ውይይት አካሂዷል።

ዘንድሮ ፈተናው በሀገር አቀፍ ደረጃ ከመስከረም 30/2015 ዓ.ም ጀምሮ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እንደሚሰጥ ቀደም ብሎ በትምህርት ሚኒስቴር የተገለጸ ሲሆን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም ፈተናውን ፦

- አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
- ኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ
- ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ
- አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ለመስጠት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ መሆኑ ተገልጻል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ዘንድሮ ፈተናው ለመጀመሪያ ጊዜ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚሰጥ እንደመሆኑ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የፈተና ሂደቱ በስኬት እንዲጠናቀቅ የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን በመስራት ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

ፈተናው የተማሪዎችን የቀጣይ የህይወት ምዕራፍ የሚወስን በመሆኑ በአዲስ አበባ ፈተናው የሚሰጥባቸው ተቋማትም ሆኑ ሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል፡፡

በአዲስ አበባ 49,203 ተማሪዎች ፈተናውን ለመውሰድ መመዝገባቸውንና ፈተናውም ከመስከረም 30 ጀምሮ በቅድሚያ የሶሻል ሳይንስ ተማሪዎች ተፈትነው ሲጨርሱ የናቹራል ሳይንስ ተማሪዎች ቀጥለው እንደሚፈተኑ የተገለጸ ሲሆን ተፈታኝ ተማሪዎች በፈተና ወቅት የምግብና የመኝታ አገልግሎቶች በየተቋማቱ እንደሚያገኙም ተጠቁማል።

የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS