Get Mystery Box with random crypto!

* ብሔራዊ ፈተና የ2014 ዓ/ም 12ኛ ክፍል ፈተናን በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ለመስጠት ዝግጅት | 🇪🇹 ኢትዮ Students

* ብሔራዊ ፈተና

የ2014 ዓ/ም 12ኛ ክፍል ፈተናን በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ነው።

በዚህም መሰረት ዩኒቨርሲቲዎች በአካዳሚክ ካላንደራቸው ላይ ማስተካከያ እያደረጉ ይገኛሉ።

ይህ እየተደረገ ያለው ተማሪዎች ፈተናቸውን በሚወስዱበት ወቅት በቅጥር ግቢዎቹ ውስጥ ማንኛውም የዩኒቨርሲቲ ተማሪ መገኘት ስለሌለበት ነው።

በሌላ በኩል ፤ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት #ለሪፖርተር_ጋዜጣ በሰጠው ቃል ፦

- ዩኒቨርሲቲዎች ለተፈታኝ ተማሪዎች የሚያስፈልጉ የምገባና መኝታ አገልግሎቶችን ለመስጠት ቁሳቁሶችን እያሟሉ ነው።

- ተፈታኝ ተማሪዎችን በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ተመድበዋል። ምደባው ሲዘጋጅ በተቻለ መጠን ተማሪዎች በአቅራቢያቸው በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንዲመደቡ ተደርጓል። በአቅራቢያቸው ያለው ዩኒቨርሲቲ በመኝታ ወይም በመፈተኛ ክፍሎች ብዛት ውስንነት ካለበት ወደ ሌላ ዞንና ክልል የመሄድ ዕድል ይኖራል።

- ገጠር አካባቢዎች ላይ ያሉ ተማሪዎች ወደ ተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ ለመጓዝ አስቸጋሪ ሁኔታ ሊገጥማቸው ስለሚችል ከክልል ትምህርት ቢሮዎች ጋር በመሆን ተማሪዎቹን ወደ ዩኒቨርሲቲ ይጓጓዛሉ።

- ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲዎች በመፈተናቸው ምክንያት ግን ወደ ተማሪዎችም ሆነ ወደ ወላጆች የሚሄድ ወጪ አይኖርም።

- ተማሪዎቹ የተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ አካባቢ እንዲላመዱት ለማድረግ ሲባል ፈተናው ከሚጀመርበት ቀናት ቀደም ብለው ወደ ዩኒቨርሲቲው ይጓዛሉ። ወደ ዩኒቨርስቲ ሲገቡ ድምፅም ሆነ ምሥል የሚቀዳና የሚቀርፅ አሊያም ሌላ የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያ ይዘው መግባት አይችሉም።

- በሚኖሩበት ከተማ ውስጥ በሚገኝ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ ተፈታኞችም በዩኒቨርስቲው ውስጥ እንዲያድሩ ለማድረግ ታቅዷል።

መልካም አዲስ አመት

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS