Get Mystery Box with random crypto!

🇪🇹 ኢትዮ Students

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiostudents — 🇪🇹 ኢትዮ Students
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiostudents — 🇪🇹 ኢትዮ Students
የሰርጥ አድራሻ: @ethiostudents
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 56.17K
የሰርጥ መግለጫ

Our Bot :
@EthioExamBot
Contact : @ethioexamsupport
Or
@Etssupport

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 22

2022-09-12 12:20:22 * ብሔራዊ ፈተና

የ2014 ዓ/ም 12ኛ ክፍል ፈተናን በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ነው።

በዚህም መሰረት ዩኒቨርሲቲዎች በአካዳሚክ ካላንደራቸው ላይ ማስተካከያ እያደረጉ ይገኛሉ።

ይህ እየተደረገ ያለው ተማሪዎች ፈተናቸውን በሚወስዱበት ወቅት በቅጥር ግቢዎቹ ውስጥ ማንኛውም የዩኒቨርሲቲ ተማሪ መገኘት ስለሌለበት ነው።

በሌላ በኩል ፤ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት #ለሪፖርተር_ጋዜጣ በሰጠው ቃል ፦

- ዩኒቨርሲቲዎች ለተፈታኝ ተማሪዎች የሚያስፈልጉ የምገባና መኝታ አገልግሎቶችን ለመስጠት ቁሳቁሶችን እያሟሉ ነው።

- ተፈታኝ ተማሪዎችን በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ተመድበዋል። ምደባው ሲዘጋጅ በተቻለ መጠን ተማሪዎች በአቅራቢያቸው በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንዲመደቡ ተደርጓል። በአቅራቢያቸው ያለው ዩኒቨርሲቲ በመኝታ ወይም በመፈተኛ ክፍሎች ብዛት ውስንነት ካለበት ወደ ሌላ ዞንና ክልል የመሄድ ዕድል ይኖራል።

- ገጠር አካባቢዎች ላይ ያሉ ተማሪዎች ወደ ተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ ለመጓዝ አስቸጋሪ ሁኔታ ሊገጥማቸው ስለሚችል ከክልል ትምህርት ቢሮዎች ጋር በመሆን ተማሪዎቹን ወደ ዩኒቨርሲቲ ይጓጓዛሉ።

- ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲዎች በመፈተናቸው ምክንያት ግን ወደ ተማሪዎችም ሆነ ወደ ወላጆች የሚሄድ ወጪ አይኖርም።

- ተማሪዎቹ የተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ አካባቢ እንዲላመዱት ለማድረግ ሲባል ፈተናው ከሚጀመርበት ቀናት ቀደም ብለው ወደ ዩኒቨርሲቲው ይጓዛሉ። ወደ ዩኒቨርስቲ ሲገቡ ድምፅም ሆነ ምሥል የሚቀዳና የሚቀርፅ አሊያም ሌላ የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያ ይዘው መግባት አይችሉም።

- በሚኖሩበት ከተማ ውስጥ በሚገኝ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ ተፈታኞችም በዩኒቨርስቲው ውስጥ እንዲያድሩ ለማድረግ ታቅዷል።

መልካም አዲስ አመት

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
19.8K viewsedited  09:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-11 10:37:54
የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች የመጓጓዣና ሌሎች ወጪዎችን በመንግሥት እንደሚሸፈን ተገለጸ

ከመስከረም 2015 ዓ.ም. መጨረሻ አንስቶ በሁለት ዙር የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚወስዱ አንድ ሚሊዮን ገደማ ተፈታኝ ተማሪዎች፣ ወደ ዩኒቨርሲቲዎች የሚጓጓዙበትን የትራንስፖርትና ሌሎች ወጪዎች በመንግሥት እንደሚሸፈኑ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ማስታወቁን ሪፖርተር ዘግቧል፡፡

ዩኒቨርሲቲዎች ለተፈታኝ ተማሪዎች የሚያስፈልጉ የምገባና መኝታ አገልግሎቶችን ለመስጠት ቁሳቁሶችን እያሟሉ መሆኑን አስታውቆ፣ ፈተናውን በዩኒቨርሲቲዎች ለማከናወን የሚያስችለውን ወጪ ለመሸፈን ተጨማሪ በጀት እንዲፈቀድለት ንግግር ላይ መሆኑን አገልግሎቱ ገልጿል። ፈተናው በትምህርት ቤቶች ሳይሆን በዩኒቨርስቲዎች እንደሚሰጥ መገለፁ ይታወሳል፡፡

መልካም አዲስ አመት

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
5.2K views07:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-03 21:55:06
ኢትዮ Students የ8ኛ ክፍል የፈተና ውጤት፣ በቀላሉ ማግኘት እንዲቻል @ethioexambot ላይ ኣካቷል!


የሚኒስትሪ ውጤትዎን ለማየት ወደ @ethioexambot በመሄድ ፣

በመጀመሪያ "Exam Result" የሚለውን መጫን
በመቀጠል "Grade 8" የሚለውን መምረጥ
ከዝያም "Admission Number" በማስገባት ማየት ይላሉ።

ለበለጠ መረጃ የተያያዘዘውን ምስል ይመልከቱ።


    @neagovetbot
     @Neagovet_bot
     @Ethioresultbot
     @examplusbot

@EthioStudents            @EthioStudents
2.0K views18:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-03 21:38:02
ኢንትራንስ ተፈታኝ ተማሪዎች ከመስከረም 03/2015 እስከ መስከረም 08/2015 ድረስ የማጠናከሪያ ትምህርት በየትምህርት ቤታቸው ይወስዳሉ

በግልም በመንግስትም ትምህርት ቤቶች ስትማሩ የነበራቹህ የአዲስ አበባ ከተማ ተማሪዎች ከመስከረም 03/2015 ጀምሮ የማጠናከሪያ ትምህርት በየትምህርት ቤቶቻቹህ እንዲሰጣቹህና እንድትዘጋጁም መመሪያ ወርዷል።

ለማጠናከሪያ ትምህርቱ ሲባል የ2015 የትምህርት ዘመን መጀመሪያ ቀን ላይ ማስተካከያ ተደርጓል።


@ethiostudents
@ethiostudents
2.8K views18:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 19:06:02
"አዲሱ ስርዓተ ትምህርት በኦሮሚያ ክልል በሁሉም የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ከመስከረም 09/ 2015 ዓ.ም ጀምሮ ይተገበራል።"

የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ


አዲሱን ስርዓተ ትምህርት በኦሮሚያ ክልል በሁሉም የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለማስጀመር የሚያስችል መድረክ በአዳማ ከተማ ተካሂዷል።

አዲሱ ስርዓተ ትምህርት የአይሲቲ እንዲሁም የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ከ7ኛ ክፍል ጀምሮ እንደሚሰጥ በኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ የስርዓተ ትምህርት ትግበራ ዳይሬክተር ደረጀ ታደሰ ገልጸዋል።

ስርዓት ትምህርቱ ትውልድን በዕውቀት፣ ሙያና ክህሎት ለማነፅ ትኩረት ያደረገ እንዲሁም የመማር ማስተማር ሂደቱ ተማሪ-ተኮር እንዲሆን የሚያስችል መሆኑንም ጠቁመዋል።

አዲሱ ስርዓተ ትምህርት በ2014 ዓ.ም በክልሉ 75 የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በሙከራ ደረጃ መተገበሩ ተገልጿል።

የአዲሱ ስርዓተ ትምህርት የመማሪያ መጽሀፍቶችና የመምህራን ማስተማሪያ ሞጁሎች መዘጋጀታቸውን የኢዜአ ዘገባ ያሳያል።

አዲሱ ስርዓተ ትምህርት በኦሮሚያ ክልል በሁሉም የመጀመሪያ ደረጃ የግልና የመንግስት ትምህርት ቤቶች ከመስከረም 09/ 2015 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚተገበር ተመላክቷል።

@ethiostudents
@ethiostudents
7.5K views16:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 22:55:01
በአዲስ አበባ ከተማ አንዲት የቤት ሠራተኛ ሁለት ህጻናትን በአሰቃቂ ሁኔታ ከገደለች በኋላ በቁጥጥር ሥር መዋሏን ፖሊስ አስታወቀ።

በሕጻናቱ ላይ የተፈጸመው ይህ የግድያ ወንጀል ያጋጠመው በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አራብሳ ኮንዶሚንየም ተብሎ በሚጠራው የጋራ መኖሪያ ቤት መንደር መሆኑን ፖሊስ ገልጿል።

የግድያ ወንጀል ድርጊት የተፈጸመባቸው ሁለቱ ህጻናት የሁለት እና የሦስት ዓመት እድሜ ያላቸው ወንድ እና ሴት ወንድም እና አህት ናቸው።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ለቢቢሲ እንደተናገሩት “እጅግ በጣም አሳዛኝ እና ዘግናኝ” በተባለው በዚህ ወንጀል የተጠረጠረችው የቤት ሠራተኛ የ19 ዓመት ወጣት መሆኗን ገልጸዋል።

ኮማንደር ማርቆስ የወንጀል ድርጊቱ የተፈጸመው ዛሬ ሐሙስ ነሐሴ 26/2014 ዓ.ም. ከረፋዱ ከ3፡30 እስከ 4 ሰዓት መሆኑን ገልጸው፤ ተጠርጣሪዋ ህጻናቱን አንቃ እና ስለት ተጠቅማ በአስቃቂ ሁኔታ መግድሏ የሚያመላክቱ መላምቶች አሉ ብለዋል።

የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተሩ ተጠርጣሪዋ ወንጀሉን ለመፈጸም ምን እንዳነሳሳት ወይም የአእምሮ ጤና ችግር እንዳለበት ለማወቅ ምርመራዎች እየተካሄዱ ነው ሲል የዘገበው ቢቢሲ ነዉ።

ለወቅታዊ እና ለፈጣን መረጃዎች አጋር ቻናላችንን ይቀላቀሉ

https://t.me/ethiogeeks
https://t.me/ethiogeeks
2.5K views19:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 22:46:13 በአዲሱ  የሥርዓተ-ትምህርት  እንደ አዲስ የሚጨመሩና የሚቀነሱ የትምህርት አይነቶች ይኖራሉ

በአዲሱ  የሥርዓተ-ትምህርት ትግበራ  ከአንደኛ ደረጃ እስከ መሰናዶ ትምህርት ቤት ያሉ ትምህርቶች ላይ የሚቀነሱ እና እንደ አዲስ የሚጨመሩ የትምህርት አይነቶች መኖራቸው ተገለጸ።

የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ምክትል  ኃላፊ አድማሱ ደቻሳ እንደገለጹት አዲሱ ሥርዓተ-ትምህርት በ2015 የትምህርት ዘመን በከፊል በተወሰኑ በቅድመ አንደኛ ደረጃ እና በአጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ  ትምህርት ቤቶች ላይ ይተገበራል።

በአዲሱ  የሥርዓተ-ትምህርት ትግበራ  ከአንደኛ ደረጃ እስከ መሰናዶ ትምህርት ቤት ያሉ ትምህርቶች ላይ የሚቀነሱ እና እንደ አዲስ የሚጨመሩ የትምህርት አይነቶች መኖራቸውን ተናግረዋል።

በ7ኛ እና 8ኛ ክፍሎች ላይ ከዚህ በፊት ሦስቱ ሳይንሶች ተብለው ይሰጡ የነበሩት (ኬሚስትሪ፣ ፊዚክስና ባዮሎጂ) አሁን  አጠቃላይ ሳይንስ ተብለው በአንድ ይሰጣሉ ብለዋል።

በ9ኛ እና 10ኛ ክፍል የኢኮኖሚክስ ትምህርት አሁን ላይ “ፐርፎርም ኤንድ ቪዥዋል አርት” በሚል መተካቱንም ጠቁመዋል።

በተመሳሳይ በ11ኛ እና 12ኛ ክፍል በድጋሚ ከሚሰጡ የትምህርት አይነቶች በተጨማሪ ሥራና ቴክኒክ ላይ የሚያተኩሩ የማኑፋክቸሪንግና ኮንስትራክሽን  የትምህርት አይነቶች በየደረጃው ተለይተው መጨመራቸውን ገልጸዋል።

በ2015 የትምህርት ዘመን የተማሪ ዩኒፎርሞችና የመማሪያ ቁሳቁሶች በፍጥነት ተደራሽ ለማድረግ ዝግጅት የተደረገ ሲሆን የትምህርት ቤቶችን አካባቢ ከአዋኪ ነገሮች ነፃ ማድረግም ትኩረት ተሰጥቶታል ተብሏል።

ለአዲሱ ሥርዓተ-ትምህርት ስኬታማነት ከወላጆችና አጠቃላይ ከትምህርት ማኅበረሰቡ ጋር እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል።

ለዚህም ስኬታማነት በትምህርት ቢሮ በኩል የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን ነው የገለጹት።

በየደረጃው ካሉ የወላጅ ኮሚቴዎች፣ የትምህርት አመራሮችና የግል ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ የተለያዩ መድረኮችን በመፍጠር ሰፊ ውይይት ስለመደረጉም አብራርተዋል።

አዲሱ ሥርዓተ-ትምህርት በ2016 ዓ.ም ወደ ሙሉ ትግበራ የሚገባ መሆኑም ታውቋል።
(ኢዜአ)

@ethiostudents
@ethiostudents
2.8K viewsedited  19:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 20:20:44
የ2014 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 11 ቀን 2015 ድረስ በሁለት ዙር እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል

ለዚህም ተማሪዎች እራሳቸውን እንዲያዘጋጁ ጥሪ አቅርቧል።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ረዲ ሽፋ ለኦቢኤን በሰጡት ቃል ፤ በአጠቃላይ በሁለት ዙር በሚሰጠው ፈተና ከ984,000 በላይ ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ ገልፀዋል።ፈተናውን ከሚወስዱት ውስጥ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ቁጥር 622,739 መሆኑን አመልክተዋል።

የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ብዛት ያላቸው በመሆኑ በመጀመሪያው ዙር ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 3 /2015 አስቀድሞ ፈተናው እንደሚሰጣቸው አቶ ረዲ ተናግረዋል።

የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ቁጥር ደግሞ 361,279 ሲሆን በሁለተኛው ዙር ከጥቅምት 8 እስከ 11/2015 ፈተናውን እንደሚወስዱ አስረድተዋል።

ከዚህ ቀደም የነበሩ የፈተና ችግሮችን ለመፍታት ፈተናው በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እንደሚሰጥ አረጋግጠዋል ፤ ፈታኞቹ ደግሞ የዩኒቨርሲቲ መምህራን መሆናቸውን አሳውቀዋል።

በተጨማሪም ፤ ፈተናው ከዚህ ቀደም ከነበረው ከ4 ኮድ ከፍ ማለቱን ገልፀዋል። ፈተናው ተዘጋጅቶ እየታተመ ሲሆን ፈተናው እስከሚሰጥበት ቀን ድረስ ተፈታኞች እራሳቸውን ማዘጋጀት እንዳለባቸውም አሳስበዋል።

@ethiostudents
@ethiostudents
12.8K views17:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 11:20:11
#ExitExam

ትምህርት ሚኒስቴር በሚቀጥለው ዓመት 2015 ትምህርት ዘመን የሚጀምረውን የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና የአፈፃፀም መመሪያን በማጸደቅ ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ማሰራጩት ይታወቃል።

ለመሆኑ መመሪያው ምን ይላል ?

- የመውጫ ፈተናው የመጀመሪያ ዲግሪ የመንግስት እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችን ይመለከታል።

- መመሪያው የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ እና ሀገሪቱ የምትፈልገውን የሰለጠነ የሰው ኃይል ለማፍራት ከሚከወኑ የማስፈፀሚያ ስልቶች አንዱ ነው።

- የመውጫ ፈተናውን ወስዶ 50 በመቶ ውጤት ማምጣት ያልቻለ ተማሪ መመረቅም ሆነ ከተማረበት ዩኒቨርሲቲ የዲግሪ ሰርተፊኬት ማግኘት አይችልም።

- በመውጫ ፈተና 50 በመቶ ማምጣት ያልቻለ ተጨማሪ ጊዜ ወስዶ በአግባቡ አጥንቶ ፈተናውን 50 በመቶ እና ከዛ በላይ አምጥቶ ማለፍ እንዲችል ለሁለት ተጨማሪ ጊዜ የመፈተን እድል ይሰጠዋል። ተፈታኙ እድሉን መጠቀም ያለበት የመጀመሪያውን ፈተና ከወሰደ በ3 ዓመታት ጊዜ ውስጥ ብቻ ነው።

- አንድ ተማሪ ለምርቃት ብቁ የሚሆነው የመውጫ ፈተናውን ካለፈ ብቻ ሲሆን 3 ጊዜ ተፈትኖ የማለፊያ ነጥብ ያላገኘ ተፈታኝ ከብሄራዊ የብቃት ማዕቀፍ ተገቢው ማስረጃ ይሰጠዋል።

- የቅድመ ምረቃ የመውጫ ፈተና እንደየትምህርት ፕሮግራሙ ባህሪ በዓመት ሁለቴ እና ከዛም በላይ ሊሰጥ ይችላል።

- የመውጫ ፈተና የሞያ ማህበራት ተጠናክረው የሞያ ፍቃድ ፈተና መስጠት እስከሚጀምሩ በትምህርት ሚኒስቴር ወይም ውክልና በሚሰጠው ተቋም ይዘጋጃል።

መውጫ ፈተና ላይ ሚካተቱ ኮርሶችን በተመለከተ በመጪው ጊዜ በየትምህርት መስኩ በሚዘጋጁ የማስፈፀሚያ ዝርዝር መመሪያዎች ይለያል መባሉን ሸገር ኤፍ ኤም ሬድዮ ጣቢያ ትምህርት ሚኒስቴርን ዋቢ አድርጎ ካሰራጨመው ዘገባ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@EthioStudents
19.9K views08:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-24 17:25:29
የቴክኖሎጂ መረጃ ላይ የተመሰረቱ ጥያቄዎችን በመመለስ በየእለቱ የተለያዩ የኢንተርኔትና የድምፅ ጥቅሎችን ያሸንፉ!!

የዚህ ሳምንት ሽልማት ያልተገደበ የኢንተርኔት ጥቅል(package)።

ጥቅሉን ለማሸነፍ:

ወደ 9677 OK ብለው ይላኩ።
የሚላክልዎትን ሊንክ በመጫን የስልክ ቁጥሮን አስገብተው ለጥያቄዎች ይዘጋጃሉ።
የሚፈልጉት የጥያቄ አይነት መርጠው ሳይሳሳቱ ተከታታይ 10 ጥያቄዎችን መመለስ ብቻ ነው።

ሲያሸንፉ የኢንተርኔት ጥቅል ወይም የድምፅ ጥቅል ወደ ስልኮ ይላክሎታል::

መልካም እድል
27.4K views14:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ