Get Mystery Box with random crypto!

የ12ኛ ክፍል ውጤቴ ትዝ አለኝ! የዛሬ ስንት አመት እኔም የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ነበርኩኝ፡፡ አ | 🇪🇹 ኢትዮ Students

የ12ኛ ክፍል ውጤቴ ትዝ አለኝ!

የዛሬ ስንት አመት እኔም የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ነበርኩኝ፡፡ አሁን ብዙዎቻችሁ እንደሆነባችሁ የያን ጊዜ ውጤቴ በፍጹም ያልጠበኩት ነበር፡፡ ያገኘሁት ውጤቴ ይቅርባችሁ፣ አይገለጽ 

በዚያ ጊዜ መጥቶብኝ የነበረውን ስሜት እስካሁን አስታውሰዋለሁ፡፡

•  ከትምህርት አንጻር አቅጄው የነበረኝ ህልሜ ሁሉ ጨልሞብኝ ነበር፡፡

•  ለትምህርት ትኩረት የሰጠውም ሆነ ያልሰጠውም ሰው አንድ አይነት እንደሆነና የመማር ትጋት ትርጉም እንደሌለው እንዳስብ ሆኜ ነበር፡፡

•  ከእኔ ብዙ ይጠብቁ የነበሩት የወላጆቼና የቤተሰቦቼ ነገር አስጨንቆኝ ነበር፡፡

•  ሕይወቴን እንዴት እንደምቀጥልና ምን ማድረግ እንዳለብኝ ግራ ግብት ብሎኝ ነበር፡፡

•  ስለውጤቴ የሚጠይቁኝ ሰዎች ሁኔታ አሸማቆኝ ነበር፡፡

•  በአጭሩ ዞሮብኝ ነበር!!!

ሆኖም፣ የያን ጊዜው ውጤቴ የዛሬውን ሕይወቴን አልወሰነውም፡፡ የዛሬውን ሕይወቴን የወሰነው ለነበረኝ ውጤት የሰጠሁት ምላሽ ነው፡፡

የፈተና ውጤት ላልመጣላችሁ . . .

1.  ሁኔታው ስሜታችሁን መንካቱ ጤናማ ሂደት እንደሆነ አስታውሱ

2.  የእናንተን የወደፊት ሕይወት የሚወስነው ራእያችሁን ማወቃችሁና ያንን መከተላችሁ እንጂ በየጊዜ የምትወድቁትና የምትነሱት ልምምድ እንዳልሆነ እወቁ

3.  ሰዎች ለሚሰነዝሩት ሃሳብ ብዙ ቦታ አትስጡ፡፡ ብዙዎቹ ሰዎች ለራሳቸው እንኳን ያላወቁበት ሰዎች ናቸው፡፡

4.  ለሁኔታው የምትሰጡትን ምላሽና የሚቀጥለው እርጃችሁ ምን ሊሆን እንደሚገባው ተረጋግታችሁ አስቡ፡፡

ወደቃችሁ እንጂ ውዳቂ አይደላችሁም!

ውጤት ባይመጣም እናንተ ግን ወደ ወደፊት ራእያችሁና መልካም ፍጻሜያችሁ ትቀጥላላችሁ!

Dr Eyob mamo

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS