Get Mystery Box with random crypto!

እንደ ፎርብስ ዘገባ ከ180 ሚሊየን ዶላር በላይ ንብረት ያፈራው ፡ የ25 አመቱ ፈረንሳዊው የእግ | 🇪🇹 ኢትዮ Students

እንደ ፎርብስ ዘገባ ከ180 ሚሊየን ዶላር በላይ ንብረት ያፈራው ፡ የ25 አመቱ ፈረንሳዊው የእግር ኳስ ኮከብ Kylian Mbappe አሁን የናፈቀው ወጣትነቱን በነጻነት መኖር ነው ።

ፈርምልኝ ፡ አብረን ፎቶ እንነሳ ሳይባል ፡ መጣ ሄደ ፡ በዚህ አለፈ ፡ ሳይባል በነጻነት መንቀሳቀስና ፡ መኖር ናፍቆታል ዝና እና እውቅናው ፡ ከምቾት ይልቅ ሰላሙን ነስቶታል ። " እንደ ማንም ሰው ዳቦ ቤት ሄጄ መግዛት እፈልጋለሁ ።

በምፈልገው ሬስቶራንት በፀጥታ መመገብ መቻል ናፍቆኛል ። ከጓደኞቼ ጋር ማንም መጥቶ ሳይረብሸኝ ፓርቲ ወጥቶ መዝናናት ፡ ይህንና ይህን መሰል ለሰው ቀላል የሚመስሉ ሰውኛ ነገሮችን ማድረግ ብፈልግም በዚህ ወቅት ይህ ነገር ለኔ ምኞት ብቻ ሆኗል ። በርግጥ ይህ ነገር ለአብዛኛዎቹ ሰወች ቀላል ወይም ተራ ነገሮች ቢሆኑም ለኔ ግን ምኞት ብቻ ሆኖ ቀርቷል ። እናም እንደ ማንም ሰው መንቀሳቀስ የምችልበት ነገር ቢኖር ምንም አይነት ገንዘብ ብከፍል አይቆጨኝም ። ሲል ተናግሯል ።
......
የአንዱ ትልቅ ምኞት ፡ ለአንዱ ተራ ነገር ነው

Wasihune Tesfaye

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS