Get Mystery Box with random crypto!

#Update ትምህርት ሚኒስቴር በአማራ ክልል የሚገኙ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ከጥር 1/2016 | 🇪🇹 ኢትዮ Students

#Update

ትምህርት ሚኒስቴር በአማራ ክልል የሚገኙ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ከጥር 1/2016 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 2 ሳምንታት ትምህርት ይጀምራሉ ማለቱ ይታወሳል።

ይህ ተከትሎ አንዳንድ ተቋማት ለተማሪዎቻቸው ጥሪ አድርገዋል።

ጥሪ ካደረጉት ውስጥ አንዱ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ነው።

ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለነባር እና አዲስ የቅድመ-ምረቃ ተማሪዎቹ ባደረገው ጥሪ ፤ የ1ኛ ዓመት 2ኛ ወሰነ ትምህርት ተማሪዎች እንዲሁም የ3ኛ ዓመትና ከዚያ በላይ ነባር መደበኛ እና የማታ የቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች ከጥር 15-17/2016 ዓ.ም ወደ ተቋማቸው እንዲገቡ ብሏል።

በ2016 ዓ.ም አዲስ የተመደቡ (Freshman፣ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች እንዲሁም በ2015 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርት ወስዳችሁ የማለፊያ ውጤት ያላቸው ተማሪዎ ከጥር 21-23/2016 ዓ.ም ወደ ተቋማቸው እንዲገቡ ጥሪ አድርጓል።

የወልድያ ዩኒቨርሲቲ የመደበኛ መርሐግብር ተማሪዎቹ የ2016 ዓ.ም የመግቢያ ጊዜ ጥር 6 እና 7/2016 ዓ.ም መሆኑን ገልጿል።

በዚህ ጥሪ መሰረት ፤ ነባር የ2ኛ እና የ3ኛ ዓመት ተማሪዎች፣ በ2015 ዓ.ም በአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም ትምህርታቸው ሲከታተሉ የቆዩና የማለፊያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች፣ በ2014 ዓ.ም እና በ2015 ዓ.ም በተለያዩ ምክንያቶች Withdrawal በመሙላት ያቋረጡ ተማሪዎች እንዲሁም በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስደው የማለፊያ ውጤት አምጥተው ወልድያ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ አዲስ ተማሪዎች ሪፖርት እንዲያደርጉ ብሏል።

ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም በሪሚዲያል ፕሮግራም አዲስ ለተመደቡ ተማሪዎች ጥሪ እስከሚደረግ በትዕግስት እንድጠብቁ ጥሪ አቅርቧል።

ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ በበኩሉ ሁለተኛ ዓመት እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ነባር ተማሪዎቹ ጥር 2 እና 3/2016 ዓ.ም ምዝገባ እንዲያከናውኑ ጥሪ አቅርቧል።

ለአንደኛ ዓመት እና ለሪሚዲያል ተማሪዎች ጥሪ እሰከሚደረግ በትዕግስት እንዲጠብቁ ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል፡፡

ወሎ ዩኒቨርሲቲ በቅርቡ ለተማሪዎቹ ጥሪ እንደሚያደርግ ገልጿል።

ሌሎች በክልሉ የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች እስካሁን ያሉት ነገር የለም።

በአማራ ክልል ያሉት ዩኒቨርሲቲዎች አስር ሲሆን በክልሉ ባለው የፀጥታ ችግር ምክንያት ተማሪዎችን ሳይጠሩ ወራትን አስቆጥረዋል።

ተማሪዎች መፍትሄ እንዲፈለግላቸው በተለያዩ መንገዶች ጭና ሲፈጥሩ የቆዩ ሲሆን በቅርቡ የትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ዩኒቨርሲቲዎች ከጥር 1 አንስቶ ባሉት 2 ሳምንታት ትምህርት እንደሚጀምሩ ማሳወቁ አይዘነጋም።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS