Get Mystery Box with random crypto!

ቻይና የዓለማችን ፈጣኑን የኢንተርኔት አገልግሎት ስራ ላይ አዋለች ቻይና በሰኮንድ 1 ነጥብ 2 | 🇪🇹 ኢትዮ Students

ቻይና የዓለማችን ፈጣኑን የኢንተርኔት አገልግሎት ስራ ላይ አዋለች

ቻይና በሰኮንድ 1 ነጥብ 2 ቴራባይት ፍጥነት ያለው ዓለማችንን ፈጣኑን የኢንተርኔት አገልግሎት ስራ ላይ አውላለች፡፡

የኢንተርኔት አገልግሎቱ በሰኮንድ 150 ፊልሞችን መላክ የሚያስችል የዓለማችን ፈጣኑ ኢንተርኔትም ነው ተብሏል፡፡

"ሁዋዌ" እና "ቻይና ሞባይል" የተሰኙት ሁለት ኩባንያዎች በጋራ ስራ ላይ ያዋሉት ይህ የኢንተርኔት አገልግሎት በሰኮንድ 1 ሺህ 200 ጊጋ ባይት ፍጥነት ያለው ነው፡፡

ፈጣኑ የኢንተርኔት አገልግሎት ከቤይጂንግ ወደ ጉዋንዡ ከተማ በተዘረጋ 300 ኪሎሜትር ኦብቲክ የፋይበር መስመር ነው አገልግሎት ላይ የዋለው፡፡

አገልግሎቱ ይጀምራል ተብሎ ከተገመተበት ሁለት አመት አስቀድሞ ስራ ላይ መዋሉም ተጠቅሷል፡፡

አሁን ላይ አሜሪካን ጨምሮ በተለያዩ ሀገራት ያለው የኢንተርኔት ፍጥነት ከ100 እስከ 400 ባይት በሰኮንድ ነው፡፡

አሁን ቻይና ስራ ላይ ያዋለችው በሰኮንድ 1 ነጥብ 2 ቴራ ባይት ፍጥነት ያለው ኢንተርኔት ለቤት አገልግሎት አይውልም መባሉን አሪራንግ ዘግቧል፡፡

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS