Get Mystery Box with random crypto!

ጥንቃቄ ለወላጆች! 15 አመቱ ነው። ሳቢር ሬድዋን። አጋቾች ከቤት አባብለው አውጥተውት ካገቱት | 🇪🇹 ኢትዮ Students

ጥንቃቄ ለወላጆች!

15 አመቱ ነው። ሳቢር ሬድዋን። አጋቾች ከቤት አባብለው አውጥተውት ካገቱት በኋላ ቤተሰቡን ከፍተኛ ብር ጠይቁ። ገዳዮቹ ገንዘብ እንኳን እስኪሰበሰብ አልጠበቁም። በአሰቃቂ ሁኔታ ገድለውት ሲያበቁ በሸገር - ጣዊል ሪልስቴት አካባቢ ቆሻሻ መጣያ ገንዳ ውስጥ ጥለውት ተሰውረዋል።

ሟች ተማሪ ሳቢር ሬድዋን ከአንዲት ሴት በተደጋጋሚ ስልክ ሲደወልለት እንደነበር። ደዋይዋ ደብዳቤ ልታደርስልኝ ስለምፈልግ ስልክህን ይዘህ ውጣ እንዳለችው ታውቋል፡፡ ሳቢር ስልክ ሳይዝ ደዋይዋ ወዳለችበት ቦታ መሄዱንና እዚያው መታገቱን ለማወቅ ተችሏል፡፡

እንዲህ አይነቱ ወንጀል ተስፋፍቶ የስራ እድል እስከመሆን ስለደረሰ ወላጆች ከባድ ጥንቃቄ ሊያርጉ ይገባል።

Zehabesha

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS