Get Mystery Box with random crypto!

አርቲስት ሀናን ታሪክ 10,000,000.00 ብር ተከፈላት አርቲስት ሀናን ታሪክ የብራንድ አምባሳ | 🇪🇹 ኢትዮ Students

አርቲስት ሀናን ታሪክ 10,000,000.00 ብር ተከፈላት

አርቲስት ሀናን ታሪክ የብራንድ አምባሳደር በመሆን ለ2 አመት አስር ሚሊዮን ብር ተከፈላት።

ሀናን ስምምነቱን ያደረገችው ድሪመር ፉድ ማኑፋክቸሪንግ ከተሰኘ ታዋቂና ግዙፍ የቻይና ኩባንያ ጋር ነው፡፡

ኩባንያው በኢትዮጵያ ውስጥ በከፍተኛ ኢንቨስትመንት የምግብ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ያቋቋመ ሲሆን በዚህም ‹‹ኤስ›› በሚል ብራንድ ያልተለመዱና አዳዲስ የታሸጉ የኬክ ወይንም የጫፋጭ ምግቦችን እያመረተ በመላው አገሪቱ እያከፋፈለ ይገኛል፡፡ ድርጅቱ ይህንን ‹‹ኤስ›› የተሰኘ ብራንድ ምርቶቹን በስፋት ለማስተዋወቅና ስርጭቱን ለማሳደግ የአንድ አመት የኮርፖሬት ብራንድ ፕሮሞሽን እቅድ ማውጣቱን ገልጿል፡፡

በዚህ እቅዱ ውስጥም ታዋቂዋን አርቲስት ሀናን ታሪክን ማካተቱን አስረድቷል፡፡ ‹‹የኤስን ብራንድ ፕሮሞሽን ውጤታማና ስኬታማ ለማድረግ አርቲስት ሀናን እንደምትጠቅመን አምነንበታል›› ብሏል ድርጅቱ፡፡

ይህን የ10ሚሊዮን ብር ስምምነት ዛሬ በስካይ ላይት ሆቴል አከናውናለች።

ይህ ክፍያ በኢትዮጵያ ብራንድ አምባሳደርነት ታሪክ ሪከርድ የሰበረ ሆኗል።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS