Get Mystery Box with random crypto!

ካናዳ በቀጣዩ የፈረንጆቹ አመት  50,000 ኢትዮጵያንን  ወደ ሀገሯ ለስራ ለትወስድ ትችላለች | 🇪🇹 ኢትዮ Students

ካናዳ በቀጣዩ የፈረንጆቹ አመት  50,000 ኢትዮጵያንን  ወደ ሀገሯ ለስራ ለትወስድ ትችላለች

ፊደል ፖስት   ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸው  ሰዎች የሰማው መረጃ ይሄን ይመስላል;

እነማን ነው የሚሂዱት?

ዘጠኝ ሙያዎች የተለዩ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ ፣ የምግብ ምርት  ማምረትና ማቀነባበር እና ማሸግ፣  አናጢነት ፣ የኤሌትሪክ ባለሙያ ፣ ነርሲንግ ፣ የኤርፖርት አስተናጋጅ ፣  ኮምፒዊተር ሳይንስ እና አይቲ  የሰለጠኑ ባለሙያዎች የሚፈለጉ ይሆናል።

ለመሄድ ምን ያስፈልጋል ?

በነዚህ ሙያዎች የሰለጠነ ባለሙያ   በኦንላየን እና  በአካል  ፈተና እዚሁ ኢትዮጰያ ውስጥ  ይፈተንና  ፈተናውን ካለፈ / ች  ካናዳ ካሉት ከቀጣሪ ድርጅቶቹ ጋር ወደ ሚያገናኙት፣ የፓስፖርትና አስፈላጊ ፎርም  ወደ ሚሞሉለት የስራ አገናኝ ኤጀንሲዎች ጋር ተልኮ  የጉዞው ሂደት ተጀምሮለት በአጭር ጊዜ ይሄዳል።

መቼ ይጀመራል?

የወረቀት ስራዎች የተጀመሩ ሲሆን በቅርቡ በኢትዮጵያና በካናዳ መንግስት በኩል  የሰለጠነ ባለሙያ ወደ ካናዳ በመላክ ጉዳይ ላይ  የመግባቢያ ሰነድ ይፈረማል ተብሎ ይጠበቃል።

በካናዳ ያለው  Ministry of Labour, Training and Skills Development,  የኢሚግሪሽን  ቢሮ እና የካናዳ መንግስት   በጉዳዩ ላይ ማብሪሪያ ተሰጥቷቸው ጉዳዩንም አምነውበታል። 

በኢትዮጵያ በኩል  የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር  ስራውን ተግባራዊ ለማድረግ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር  ጋር እየሰራ ነው።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS