Get Mystery Box with random crypto!

AHADU RADIO FM 94.3

የቴሌግራም ቻናል አርማ ahaduradio — AHADU RADIO FM 94.3 A
የቴሌግራም ቻናል አርማ ahaduradio — AHADU RADIO FM 94.3
የሰርጥ አድራሻ: @ahaduradio
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 22.23K
የሰርጥ መግለጫ

አሐዱ ራድዮ 94.3
Your source for top local and international news and analysis.
"Voice of Ethiopian"
የአሐዱ የቴሌግራም ቻናል ቤተሰብ በመሆን ወቅታዊና እውነተኛ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2023-05-17 15:00:46
በትግራይ ክልል የወደሙ የጤና ተቋማትን መልሶ ለማቋቋም እና አገልግሎት ለመስጠት እየተሰራ እንደሆነ ተገለጸ፡፡

የፕሪቶርያውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ በትግራይ ክልል በጦርነቱ ምክንያት የወደሙ ተቋማትን መልሶ የመገንባት ስራዎች በመንግስትም ሆነ በተራድኦ ተቋማት በኩል እየተሰሩ እንደሆነ ይታወቃል፡፡
በጦርነቱ ምክንያት ጉዳት ከደረሰባቸው አገልግሎት ሰጪ ተቋማት መካከል የጤናው ዘርፍ ቅድሚያ ሊሰጠው እንደሚገባም እሙን ነው፡፡
በኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ መስኮች ከተሰማሩ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች መካከል አንዱ የሆነው የህጻናት አድን ድርጅት በትግራይ ክልል በጦርነቱ ምክንያት የወደሙ ተቋማትን መልሶ ለመገንባት ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ በኢትዮጵያ የህጻናት አድን ድርጅት የትግራይ ክልል አስተባባሪ አቶ አታክልቲ ገብረ ዮሃንስ ለአሃዱ ተናግረዋል፡፡

በጦርነቱ ምክንያት ድርጅቱ የሚሰራባቸው የጤና ተቋማት ወድመው እንደነበር ያስታወሱት አስተባባሪው ከሰላም ስምምነቱ በኋላ እነዚህን የጤና ተቋማት መልሶ ለማቋቋም በካታ ስራዎች መሰራታቸውን ተናግረዋል፡፡ የጤናው ዘርፍ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ በመሆኑ የወደሙ ተቋማትን መልሶ ለማቋቋም ጥረት መደረጉ ተገቢ መሆኑን ያነሱት አስተባባሪው፤ ከጤናው ዘርፍ በተጨማሪ በሌሎች ድርጅቱ በሚሰራባቸው ማህበራዊ ጉዳዮች ላይም ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ:https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24
2.2K views12:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-17 13:35:25
በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል ጥሩ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንዲፈጠር የሁለቱ ሀገራት ድንበር በሆነችው በትግራይ ክልል ላይ ሰላም እና መረጋጋት እንዲሰፍን ሁለቱም ሀገራት መስራት እንዳለባቸው ተገለጸ፡፡

የኤርትራ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ከኢትዮጵያ ጋር ያለንን ግንኙነት ለማሻከር የሚጥሩ ሃይሎች አሉ ሲሉ በቅርቡ በትዊተር ገፃቸው ላይ መፃፋቸውን ተከትሎ አሐዱም እነዚህ ጣልቃ የሚገቡ ሀገራት እነማን ሊሆኑ ይችላሉ ሁለቱ ሀገራትስ ምን ማድረግ አለባቸው ሲል የፖለቲካ እና ዓለማቀፍ ግንኙነት ምሁራንን አነጋግሯል፡፡
የፖለቲካ እና ዓለማቀፍ ግንኙነት መምህሩ አቶ ግደይ ደገፉ እንደሚሉት አሁንም ኤርትራ በትግራይ ክልል በኩል በኢትዮጵያ ላይ በተደጋጋሚ ድንበር አልፋ በምታደርገው እና በምታሳየው አቋም ምክንያት የውጪ ሀገራት ጣልቃ መግብታቸው ጥሩ ነው ፣ እነዚህ ጣልቃ የሚገቡት ሀገራትም ምናልባትም አሜሪካ እና አውሮፓውያኑ ናቸው፡፡
በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል ጥሩ ግንኙነት እንዲፈጠር በትግራይ ክልል ሰላም እና መረጋጋት እንዲፈጠር ሁለቱ ሀገራት መስራት አለባቸው ብለዋል፡፡

ሌላኛው የፖለቲካ እና ዓለማቀፍ ግንኙነት መምህር ዶክተር ደጉ አስረስ በበኩላቸው በቅርቡ የኢትዮጵያ መንግስትም አንዳንድ የውጪ አካላት ጣልቃ እየገቡብኝ ነው በሚል መግለፁ ታወሳል፣ በተመሳሳይ የኤርትራ መንግስትም ይሄንን ሲናገር ለሁለቱም ህዝቦች በግልጽ እነማን እንደሆኑ መገለጽ ነበረበት ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ ውስጥ አሁን ያለው አለመረጋጋት ለሀገሪቱም ሆነ ለቀጠናው የሚፈጥረው ስጋት ስላለው በተለይ ምራባውያኑ ጉዳዩን ለማስተካከል ጣልቃ ሊገቡ ይችላሉ ብለዋል፡፡

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
2.5K views10:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-16 18:01:22
የቻይና ከፍተኛ ልዑክ ዩክሬንና ሩሲያን ሊጎበኝ ነው ተባለ፡፡

ልዑኩ ለዩክሬን ቀውስ መፍትሄ ለማበጀት ሰላማዊ ተልዕኮ ይዘው ወደ ዩክሬን፣ ሩሲያ እና ሌሎች የአውሮፓ ሀገራት ጉዞ ያደርጋሉ ነው የተባለው፡፡
በሩሲያ የቀድሞ የቻይና አምባሳደር የነበሩት ሊ ሁይ ጦርነቱ ከተጀመረ በኋላ የክሬንን የሚጎበኙ የመጀመሪያው ከፍተኛ የመንግስት ተወካይ ናቸው ተብሏል፡፡
ልዑኩ ዩክሬንን ዛሬና ነገ ይጎበኛሉ ሲል የዩክሬን መንግስት ባለስልጣን ለሮይተርስ ተናግሯል ነው የተባለው፡፡
ጉብኝቱ ባሳለፍነው ሚያዝያ የቻይናው ፕሬዝዳንት ከዩክሬኑ አቻቸው ጋር የስልክ ንግግር ማድረጋቸውን ተከትሎ እንደሆነ ተነገሯል፡፡

የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት የስልክ ውይይቱን ረጅምና ትርጉም ያለው ውይይት አንደነበር በትዊተር ገጻቸው ገለጸውታል ተብሏል፡፡ ቻይና ካሳለፍነው ወርሃ የካቲት ጀምሮ ለዩክሬን ቀውስ ፖለቲካዊ መፍትሄ ይሆናል ያለችውን ባለ አስራ ሁለት ነጥብ የመፍትሄ ሀሳብ አቅርባለች ሲል ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ:https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24
3.2K views15:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-16 16:10:08 ከለላ ለሚሹ ሴቶች ድምጽ ለመሆን በማለም የተቋቋሙ ማህበራት ሃላፊነታቸውን እየተወጡ እንዳልሆነ ተገለጸ፡፡

በኢትዮጵያ በየጊዜው በሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች ፍትህ እንዲያገኙ ለማስቻልና ለእነዚሁ ሴቶች ድምጽ ለመሆን ባለመ መልኩ የተቋቋሙ የሴት ማህበራት ሃላፊነታቸውን በአግባቡ እየተወጡ እንዳልሆነ አሃዱ ያነጋገራቸው የሲቪል ማህበራት ገልጸዋል፡፡
የቪ-ኮድ ኢትዮጵያ መስራችና የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ጥምረት ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚደንት አቶ ታደለ ደርሰህ ባለፉት አመታት በሃገሪቱ የተከሰቱትን ግጭቶች እንዲሁም የሰሜኑን ጦርነት ተከትሎ በርካታ ሴቶች የጾታዊ ሆነ ስነ ልቦናዊ ጥቃት ሰለባ ቢሆኑም በርካታ የሴት ማህበራት ግን ዝምታን በመምረጥ አፈግፍገዋል ብለዋል፡፡

ነገር ግን አሁን ላይ የሰላም አየር ሲነፍስ ጠብቀው ብቅ ብቅ የሚሉ የሴት ማህበራት በስፋት ተስተውለዋል ያሉት አቶ ታደለ ይህ ፍጹም ተቀባይነት የሌለዉና የተቋቋሙበትን አላማ የሳተ ነው ሲሉም ተችተውታል፡፡
ሌላኛው አሃዱ ያነጋገራቸው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ ምክትል ስራ አስፈጻሚ አቶ ዘየደ ገብረጻዲቅ በበኩላቸው የአቶ ታደለን ሃሳብ በመጋራት ለሴቶች ከለላ ከመስጠት አኳያ አለማቀፍ ህጎች እንዲከበሩ ከመስራት ይልቅ ከአላማቸው በሚቃረኑ ተግባራት ላይ ተሳታፊ ሆነው መገኘታቸው ተገቢ አይደለም ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በማህበራቱ በኩል እየተነሱ ያሉ ቅሬታዎችን አስመልክቶ ምን እየሰራችሁ ትገኛላችሁ ሲል አሃዱ ያነጋገራቸው የኢትዮጲያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ምክትል ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላም ሃላፊነታቸውን የማይወጡ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የክዋኔ ሪፖርትን ጨምሮ የተለያዩ ክትትሎችን በማድረግ ከማስጠንቀቂያ ጀምሮ እስከ ማገድ ድረስ የሚወሰዱ እርምጃዎች እንዳሉ አስረድተዋል፡፡

የግጭትና ጦርነት ቀጠና ሆነው በቆዩ የሃገሪቱ አካባቢዎች የሚገኙ በሺዎች የሚቆጠሩ ሴቶች የጾታዊ ጥቃት ሰለባ መሆናቸው አሳሳቢ ሆኖ ቢቆይም አብዛኛዎቹ ለሴት ብለዉ የተቋቋሙ ማህበራት በሌሎች ስራዎች ከመደመጣቸዉ በላይ ስለ ጉዳዩ ምንም ሳይሉ ዝምታን መምረጣቸዉ ይታወቃል፡፡

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ:https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24
3.1K views13:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-16 15:02:03 ፍሉሃ አካባቢ ይኖሩ የነበሩ ነዋሪዎች ከተማ አስተዳደሩ ቃል የገባልንን ምትክ ቤት ሳይሰጠን ከቦታዉ እንድንነሳ በህግ አካላት እየተገደድን ነዉ ሲሉ ቅሬታቸዉን ተናግረዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በበኩሉ የቀበሌ ቤትና ህጋዊ የግል ይዞታ ለነበራቸው በፍልውሃ አካባቢ ለነበሩ የልማት ተነሺዎች በሙሉ ቃል የተገባላቸውን መኖሪያ ቤት አስረክቤያለሁ ሲል አስታውቋል፡፡ በፍልውሃ አካባቢ ኑሯቸውን በሸራ መጠለያ ውስጥ ያደረጉ የልማት ተነሺዎች ቃል የተገባልን የመኖሪያ ቤት ድጋፍ አልተፈጸመልንም ብለው ቅሬታ ያቀረቡ ሲሆን ለረጅም አመታት በሸራ መጠለያ ውስጥ ኑሯችንን ስንመራ ነበር ነገር ግን ምንም አይነት ምትክ ቦታ ሳይሰጠን በቀጣዮቹ ቀናት ውስጥ ከቦታዉ ላይ እንድንነሳ ተገደናል ሲሉ ለአሃዱ እንዲህ ቅሬታቸዉን አሰምተዋል፡፡ አሃዱም በጉዳዩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ፕሬስ ሴክሬተሪ አቶ በረከት ታከለን አነጋግሯል፡፡አቶ በረከት በምላሻቸውም በፍልውሃ አካባቢ የሚገኙ የግል ይዞታ መሬት ለነበራቸው የልማት ተነሺዎች 1.1 ቢሊየን ብር ካሳ መከፈሉንና 5.6 ሄክታር ተለዋጭ መሬት መሰጠቱን ገልጸዋል፡፡
በቀበሌ ቤት ይኖሩ ለነበሩ ከ400 በላይ ዜጎች ደግሞ ተለዋጭ የቀበሌ ቤት አስረክበናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ የቀበሌ ቤት ወይም የግል ይዞታ ለነበራቸው ዜጎች ሙሉ በሙሉ ማለት በሚያስችል ሁኔታ ምላሽ መሰጠቱን ገልጸው አሁን እየተነሱ ያሉ ቅሬታዎች ግን የቀበሌ ቤት ሳይኖራቸው ሸራ ወጥረው ኑሯቸውን ይመሩ በነበሩ ዜጎች ነው ብለዋል፡፡ በመሆኑም ለእነዚህ ዜጎች በከተማ አስተዳደሩ የተዘጋጀ ምንም አይነት ተለዋጭ ቤት እንደሌለም አክለው ተናግረዋል፡፡
ቅሬታ አቅራቢዎቹ ቦታዉ ላይ ተጠልለዉ ሲኖሩ 30 እና 40 አመታት እንዳለፋቸዉ ገልጸዉ ካለባቸዉ የኑሮ ጫና እና የቤተሰብ ቁጥር አኳያ የትኛዉን ቤት ተከራይተዉ ለመኖር አቅም እንደሌላቸው ተናግረዋል፡፡ አካባቢዉ ለፈርስ ሲል የከተማ አስተዳደሩ የደሃ ደሃ ቤት ለእናንተም ይሰጣችኃል ብሏቸው እንደነበር ጠቅሰዉ አሁን ይህ ቃል የተገባዉ ነገር ለአንዳንድ ሰዎች ተመርጦ ሲሰጥ ተመልክተናል ሲሉ ጣቢያችን ድረስ በአካል መጥተዉ ቅሬታ አቅርበዋል፡፡
የከተማ አስተዳደሩ ቀበሌ ቤት ወይም የግል ይዞታ ኖሯቸው ምንም አይነት ተለዋጭ ቦታ አላገኘንም ብለው ቅሬታ ለሚያነሱ የልማት ተነሺዎች ግን ቅሬታቸውን ለማስተናገድ ዝግጁ ነዉ ሲሉ አቶ በረከት ተናግረዋል፡፡

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ:https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24
2.9K views12:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-16 11:56:18
በታይላንድ ሁለት ዋና ዋና ተቀናቃኝ ፓርቲዎች የጥምር መንግስት ለመመስረት ተስማምተዋል ተባለ፡፡

የዴሞክራሲ ስርዓት አቀንቃኝ ናቸው የተባሉት ሁለቱ ፓርቲዎች ለአስርት አመታት በጦር ሰራዊቱና በዘውድ አገዛዝ ፖለቲካ ስርዓት ስር የነበረችውን ሀገር አስገራሚ ነው በተባለ የምርጫ ውጤት በማሸነፍ የጥምር መንግስቱን ለማቋቋም ነዉ የተስማሙት ተብሏል፡፡
ሰኞ እለት ጠዋት በተደረገው የአጠቃላይ ድምጽ ቆጠራ ሙቭ ፎር ዋርድ የተባለው ፓርቲ መቶ ሀምሳ አንድ መቀመጫ ማግኘቱን ሲያረጋግጥ ተቀናቃኙ ፔ ሁ ታይ ፓርቲ ደግሞ አንድ መቶ አርባ አንድ መቀመጫዎችን አግኝቷል ነው የተባለው፡፡
የሙቭ ፎር ዋርድ ፓርቲ መሪ የታይላንድ ህዝብ ፍላጎቱን በምርጫው አሳውቋል እኔም የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር ለመሆን ዝግጁ ነኝ ማለታቸዉ ተሰምቷል፡፡
ዘገባው፡-የዩፒ አይ ነው
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ:https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24
3.1K views08:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-16 11:51:44 በጦርነት እና ግጭቶች ምክንያት ንብረት የወደመባቸው ተቋማት ከቀረጥ ነጻ እንዲያስገቡ እና የባንክ ብድር ክፍያ እንዲራዘም ቢወሰንም ተግባራዊ ሊሆን እንዳልቻለ ተገለጸ፡፡

ባለፉት ጥቂት አመታት አገራችን ውስጥ በነበረው ተከታታይ ጦርነት እና ግጭቶች ምክንያት ንብረት የወደመባቸው ተቋማት መልሶ ለመቋቋም የሚያስፈልጋቸውን ቁሳቁስ ከቀረጥ ነፃ እንዲያስገቡ በሚንስቴሮች ምክር ቤት ቢወሰንም እስካሁን ተግባራዊ አለመደረጉን የኢትዮጵያ አሰሪዎች ኮንፌዴሬሽን ፕሬዘዳንት ኢንጂነር ጌታሁን ሁሴን ገልጸዋል፡፡

የሚንስቴሮች ምክር ቤት በ89 ኛው ጉባኤው ተቋማቱ ከቀረጥ ነፃ እንዲያስገቡ ከመወሰኑ በተጨማሪም ከባንክ የወሰዱትን ገንዘብ የሚከፍሉበት ጊዜ እንዲራዘምላቸው እንዲሁም የግብር ቅነሳ እንዲደረግላቸው ውሳኔ እንዳሳለፈ አስታውሰዉ ዉሳኔዉ አለመተግበሩ ግን ተቋማቱ ዘርፈ ብዙ ለሆኑ ችግሮች ተጋላጭ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል ብለዋል፡፡

እነዚህ አምራች ተቋማት ከፍተኛ ቁጥር ላላቸው ዜጎች የስራ እድል የፈጠሩ እንደመሆኑ መጠን መሰል በህግ የተፈቀደላቸውን አገልግሎት ማግኘት አለመቻላቸው ከስራው እንዲወጡ ከማድረጉ በተጨማሪም ሌሎች የውጪ ባለሃብቶች ወደ አገር ውስጥ ገብተው የመስራት ፍላጎት እዳይኖራቸው ያደርጋል ሲሉም ተናግረዋል፡፡
አያይዘውም የሚንስቴሮች ምክር ቤት ውሳኔ ወደ ገንዘብ ሚንስቴር፣ ቀጥሎም ወደ ባንኮች የወረደ ቢሆንም ተግባራዊ ሊያደርጉ አለመቻላቸውን አስታውቀዋል፡፡

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ:https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24
2.9K viewsedited  08:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-16 11:50:28
በኢትዮጵያ ዝቅተኛ የሰራተኞች ደሞዝ የሚወስነው የደሞዝ ቦርድ ባለመቋቋሙ ምክንያት እስካሁን የአገራችንን ዝቅተኛ የደሞዝ ወለል መወሰን እንዳይቻል ማደረጉ ተገለጸ፡፡

በአገራችን የሰራተኞችን ዝቅተኛ የደሞዝ ወለል አለመኖሩን ተከትሎ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ዜጎች በሰሩት ልክ እንዳያገኙ እና በተገቢው መንገድ ለመኖር ስለሚያቅታቸዉ ስደትን የመጨረሻ ምርጫቸዉ እንዲያደርጉ ይገደዳሉ፡፡
ይህንን ተከትሎም በኢትዮጵያ ዝቅተኛ የሰራተኞች ደሞዝ ወለል የሚወስን የደሞዝ ቦርድ እንዲቋቋም በ2011 ዓ.ም በወጣው አሰሪ እና ሰራተኛ አዋጅ ላይ የተወሰነ ቢሆንም ቦርዱ እስካሁን እንዳልተቋቋም የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን ፕሬዘዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ ለአሀዱ ገልፀዋል፡፡

የደሞዝ ቦርዱን እንዲያቋቁም ስልጣን የተሰጠው የሚንስቴሮች ምክር ቤት እንደሆነ ገልጸው በዚህም ምክንያት እስካሁን ዝቅተኛ የደሞዝ ወለል ለመወሰን ሳይቻል መቆየቱን አስታውቀዋል፡፡
አያዘውም በአገራችን ዝቅተኛ ደሞዝ ከሚከፍሉ ተቋማት ውስጥ ከፍተኛውን ድርሻ የሚይዙት ከፍተኛ የደሞዝ ክፍያ ከሚከፈልባቸው አገራት የመጡ የውጪ ባለሃብቶች እንደሆኑ ገልጸው በተቻለው ፍጥነት ቦርዱ እንዲቋቋም ማድረግ እና ዝቅተኛ የደሞዝ ወለል መወሰን እንደሚያስፈልግ አመላክተዋል፡፡

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ:https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24
3.0K views08:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-15 11:34:58
ኢትዮጵያ ለነዳጅ ግዢ በዓመት የምታወጣውን ከፍተኛ ወጪ ለመቀነስ የነዳጅ ፍጆታ ያላቸውን ተሽከርካሪዎች በሂደት ከአገልግሎት ውጪ ማድረግ ይገባል ተባለ፡፡

ኢትዮጵያ ለነዳጅ ግዢ የምታወጣውን ከፍተኛ ገንዘብ ለመቀነስ የነዳጅ ፍጆታ ያላቸውን ተሽከርካሪዎች በነዳጅ ቆጣቢ ተሽከርካሪዎች መተካት ያስፈልጋል ሲሉ የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት የህዝብ ግንኙነት ከፍተኛ ባለሙያ አቶ አለማየሁ ጸጋዬ ተናግረዋል፡፡ ኢትዮጵያ በዓመት ከ4 ቢሊየን ዶላር በላይ ለነዳጅ ግዢ እንደምታወጣ ገልጸው ነዳጅ አስፈላጊ ምርት በመሆኑ በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እንደሚገባ ነው ያነሱት፡፡ ይህን ከፍተኛ ወጪ ለመቀነስም የነዳጅ አጠቃቀማችንን ማስተካከል አለብን ብለዋል፡፡

ነዳጅ ለመቆጠብም አንዱ ሊታሰብበት የሚገባው መፍትሄ ከፍተኛ የነዳጅ ፍጆታ ያላቸውን ተሽከርካሪዎች በጊዜ ሂደት ወደ ነዳጅ ቆጣቢ ተሽከርካሪዎች መቀየር ነው ብለዋል፡፡ የሚመለከታቸው አካላትም በፖሊሲ ደረጃ አዘጋጅተው ተፈጻሚ ማድረግ አለባቸው ሲሉ አሳስበዋል፡፡ ቀደም ሲል የነበረው ተሰብሳቢ ገንዘብ በየጊዜው በሚደረግ የዋጋ ክለሳ ተመላሽ ስለማይደረግ መንግስት በኪሳራ ለመሸጥ ተገዶ እንደነበር አንስተው ይህም ሀገሪቷን ከፍተኛ ዕዳ ላይ መጣሉንም አክለው ገልጸዋል፡፡

የነዳጅ ዋጋን ለማረጋጋት መንግስት ተግባራዊ ባደረገው የነዳጅ ዋጋ ማረጋጊያ ፈንድ እስካሁን ኢትዮጵያ የ194 ቢሊየን ብር ዕዳ እንዳለባት የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር መግለጹ አይዘነጋም፡፡

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ:https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
3.6K views08:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-15 11:31:06
በዓላትና ስብሰባዎችን ምክንያት በማድረግ ያለፈቃዳቸው ከጎዳና ላይ እንዲነሱ የሚደረጉ ዜጎች እንዳሉ ኢሰመኮ ባወጣው ሪፖርት ቢገልጽም የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ግን ጉዳዩን አስተባብሏል፡፡

ኑሯቸውን በጎዳና ላይ ያደረጉ ዜጎችን በተመለከተ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ክትትል እና ሰፊ ጥናት መደረጉን የተናገሩት የኢትዮጲያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የህግና ፖሊሲ ስራ ክፍል ዳይሬክተር ታሪኳ ጌታቸው ናቸው፡፡ የኮሚሽኑ የ9 ወራት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርቱን ባቀረበበት ወቅት በዓላትና ስብሰባዎችን ምክንያት በማድረግ ከጎዳና ላይ እንዲነሱ የሚደረጉ ዜጎች እንዳሉ መግለጻቸውም ይታወሳል፡፡

አሀዱም ስለጉዳዩ በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የህገወጥ የሰዎች ዝውውር መከላከል እና የተመላሽ ዜጎች ድጋፍ እና ክትትል መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ደረጄ ተግይበሉን ጠይቋል፡፡
በምላሻቸውም የሚወጡ ሪፖርቶች በማስረጃ እና መረጃ ላይ የተደገፉ ሊሆኑ ይገባል ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን እንዲህ አይነት መረጃ አለኝ ካለ ለሚመለከተው የህግ አካል ማቅረብ ነበረበት ያሉት አቶ ደረጄ፤ የተለያዩ ስብሰባዎችን እና በዓላትን ምክንያት በማድረግ ከጎዳና ላይ የሚነሱ ዜጎች የሉም ሲሉም ገልጸዋል፡፡

መልሶ ለማቋቋም ሲባል ብቻ ዜጎች ከጎዳና ላይ ይነሳሉ እንጂ ስብሰባዎችን እና በዓላትን ምክንያት በማድረግ አይደለም ብለዋል፡፡ ከጎዳና የሚነሱ ዜጎች ወደ ማገገሚያ ማዕከላት ሲገቡም ተገቢው ድጋፍ ሊደረግላቸው እንደሚገባ እና የተቋማትን ተናቦ መስራት እንደሚጠይቅም ተመላክቷል፡፡

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ:https://www.facebook.com/ahaduradio
3.2K views08:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ