Get Mystery Box with random crypto!

AHADU RADIO FM 94.3

የቴሌግራም ቻናል አርማ ahaduradio — AHADU RADIO FM 94.3 A
የቴሌግራም ቻናል አርማ ahaduradio — AHADU RADIO FM 94.3
የሰርጥ አድራሻ: @ahaduradio
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 22.23K
የሰርጥ መግለጫ

አሐዱ ራድዮ 94.3
Your source for top local and international news and analysis.
"Voice of Ethiopian"
የአሐዱ የቴሌግራም ቻናል ቤተሰብ በመሆን ወቅታዊና እውነተኛ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2023-06-10 11:02:56
በጊኒ በተደረገ ምርጫ የተቀናቃኝ ፓርቲዎች ጥምረት አሸንፏል፡፡
የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ኡማሮ ሲሶኮ እምባሎ ከአንድ አመት በፊት የቀድሞውን ብሄራዊ ምክርቤት ካፈረሱ በኋላ በተደረገው የመጀመሪያ ምርጫ የተቀናቃኝ ፓርቲዎች ጥምረቱ ብዙውን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ እንዳገኘ ተነግሯል፡፡
የአምስት ፓርቲዎች ስብስብ የሆነው ጥምረቱ ባሳለፍነው እሁድ በተደረገው ምርጫ ከ102 አጠቃላይ መቀመጫዎች ሀምሳ አራቱን ማሸነፉ ነው የተዘገበው፡፡
የፕሬዝዳንት እመባሎ ፓርቲ በበኩሉ ሀያ ዘጠኝ መቀመጫዎችን ብቻ ማግኘቱን የሀገሪቱ ምርጫ ኮሚሽን ይፋ ባደረገው የድምጽ ቆጠራ ውጤት ታውቋል፡፡
አሁን ባለው የሀገሪቱ የፖለቲካ ስርዓት አብላጫ ድምጽ ያገኘው ፓርቲ ወይም ጥምረቱ አስተዳደር መመስረት የሚችል ሲሆን በአንዳንድ ሁኔታዎች ግን ፕሬዝዳንቱ አስተዳደሩን ሊያፈርሱት እንደሚችሉ ተጠቁሟል፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24
2.9K views08:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-10 10:59:50
ብሄርን መሰረት አድርገው የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የዜግነት እሳቤን የሚያራምዱ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ለማደከም አበክረው እንደሚሰሩ ኢዜማ አስታወቀ፡፡
እንደ ሀገር ያለውን የፖለቲካ ምህዳር ለማስፋት እና ገዢ የሆኑ ሃሳቦችን ለዜጎች በማቅረብ ተወዳዳሪ በመሆን ረግድ በፓርቲዎች ላይ የሚነሱ በርካታ ቅሬታዎች መኖራው ይታወቃል፡፡
አብዛኞቹ ፍቃድ ተሰጥቷቸው የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ብሄር ተኮር መሆናቸው ሃገራዊ መግባባት ለመፍጠር በሚደረገው ጥረት ላይ የራሱ የሆነ አሉታዊ ተጽእኖ እንዳሳደረም ይታመናል፡፡
ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ከአሃዱ መድረክ ጋር በነበራቸው ቆይታ ላይ ለተነሳላቸው ጥያቄ ምላሽ የሰጡት የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ፓርቲ ምክትል መሪ አርክቴክት ዮሃንስ መኮንን በሃገሪቱ እየተንቀሳቀሱ ያሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ብሄር ተኮር እና ዜግነትን የሚያቀነቅኑ ሁለት ጽንፎች መሆናቸውን አስታውሰው ይህ መሆኑ ከፍተኛ የሃሳብ ልዩነት እንዲኖር ማድረጉን ተናግረዋል፡፡
አርክቴክት ዮሃንስ አክለውም በተለይ ብሄርን መሰረት አድርገው የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የአንድነት ሃይሉ ላይ የሚያሳድሩት ጫና የጎላ መሆኑንና ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ፓሪቲዎችን ለማዳከም እና ለማሽመድመድ አበክረው እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24
2.9K views07:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-09 15:10:00
በአማራ ክልል ምክር ቤት የሚገኙ የአብን ተወካዮች በህግ ማስከበር ሽፋን በክልሉ እየተካሄደ ያለው የመብት ጥሰት እንዲቆም ጠየቁ፡፡
በአማራ ክልል ምክር ቤት የሚሳተፉ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) አባላት ወቅታዊ የክልሉን ሁኔታ አስመልክተው መግለጫ ማውጣታቸው ይታወሳል፡፡
በመግለጫውም በአማራ ክልል ለአርሶ አደሮች በቂ የማዳበሪያ አቅርቦት እንዲደርስ ፣ በህግ ማስከበር ሽፋን እየተካሄዱ ያሉ የመብት ጥሰቶች እንዲቆሙ ፣ በክልሉ የሚስተዋለው የፌዴራል መንግስት የአስተዳደር ጣልቃ ገብነት እንዲቆምና ሌሎች ጉዳዮችም ተነስተዋል፡፡
ይህን አስመልክቶም አሃዱ በአማራ ክልል ምክር ቤት የአብን ተወካይ ፤ የባህር ዳርና አካባቢው አስተባባሪ ዶክተር በቃሉ ታረቀኝን አነጋግሯል፡፡
በህግ ማስከበር ሽፋን የክልሉ ዜጎች እየተሳደዱ ፣ እየተገደሉና ሰፊ ጦርነትም ተከፍቶባቸዋል ያሉት ዶክተር በቃሉ በዚህ ዘመቻም አድራሻቸው የት እንደሆነ የማይታወቁ ዜጎች አሉ በመሆኑም ይህ አይነቱ የመብት ጥሰትም በአስቸኳይ መቆም አለበት ሲሉ አሳስበዋል፡፡
እንዲህ ያሉ እንቅስቃሴዎች ከክልል አልፎ ለሃገር ቀጣይ ሰላምና መረጋጋትን ከማስፈን አንጻር ፈተና ስለሚሆን መንግስት በትኩረት እንዲያስብ በመግለጫችን ጠይቀናል ሲሉም አብራርተዋል፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24
3.8K views12:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-09 11:00:15
መንግስት በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሱ የኤርትራ ወታደሮችን ከክልሉ ለማስወጣት ቁርጠኛ መሆን እንደሚገባዉ የፓለቲካ ምሁራን ገለጹ፡፡
የፌዴራል መንግስትና ህዉሃት በፕሪቶሪያ በተካሄደው ድርድር መሰረት የሰላም ስምምነት ላይ መድረሳቸው የሚታወቅ ነው፡፡
ሁለቱ አካላት ጦርነቱን ቋጭተው ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴ መመለሳቸው ትልቅ ጉዳይ መሆኑን ያነሱት የፖለቲካ ሳይንስና አለም አቀፍ ግንኙነት መምህሩ አቶ ሱራፌል ጌታሁን ሲሆኑ በክልሉ አሁንም በህወሃት አመራሮች በኩል የጦርነት ጉሰማዎች ሲሰሙ ይሰተዋላል ብለዋል፡፡
በክልሉ በተፈጸመው የእርዳታ እህል ስርቆት ምክንያትም የአለም ምግብ ፕሮግራም እርዳታ ማቋረጡን አስታውሰው በተለያዩ አካባቢዎች እህሉ በገበያ ቦታዎች ላይ መሸጡም እንደተነገረ ገልጸዋል፡፡
እርዳታው ለዜጎቹ በከፍተኛ ሁኔታ ስለሚያስፈልጋቸው ድርጊቱ ተገቢ አለመሆኑን ጠቅሰው ክልሉ ድርጊቱን የፈጸሙትን በመለየትና ተጠያቂ በማድረግ እርዳታው በሚቀጥልበት ሁኔታ ላይ በትኩረት መስራት አለበት ብለዋል፡፡ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የኤርትራ ወታደሮችን በተመለከተም ሰራዊቱ ክልሉን ለቆ እንዲወጣ የማድረግ ዋነኛ ስራ የፌዴራል መንግስት በመሆኑ የተለያዩ የዲፕሎማሲ ስራዎችን በመስራት ተፈጻሚ ማድረግ አለበት ሲሉም አስገንዝበዋል፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24
3.8K views08:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-09 10:00:00
ኢዜማ ፓርቲ ከመንግስት ጋር በመሰራቱ የጣሰው ምንም አይነት የፓርቲ መርህ እንደሌለ ገለጸ፡፡
በቅርቡ የተፈጠረውን አለመግባባት ተከትሎ ከፓርቲው የለቀቁ አመራሮች እና አባላት ፓርቲው ከመንግስት ጋር በጋራ እየሰራበት ያለዉ ሂደት ከመርህ አንጻር ተገቢ እንዳልሆነ ማንሳታቸው ይታወሳል፡፡
ጉዳዩን አስመልክቶ ከአሃዱ መድረክ ጋር ቆይታ ያደረጉት የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ የብሄራዊ ስራ አስፈጻሚ አባል እና የሴቶች መምሪያ ሃላፊ ወ/ሮ ቅድስት ግርማ ፓርቲው ከመንግስት ጋር በትብብር በመስራቱ ምንም አይነት የፓርቲ መርህ ጥሰት እንዳልፈጸመ አስታውሰው ከመርህ ጥሰት አንጻር የተነሱት ጉዳዮች ተቀባይነት የሌላቸው ናቸው ብለዋል፡፡
አክለውም ፓርቲው ከመንግስት ጋር በጋራ ለመሰራት ሲወስን ጠቅላላ ጉባኤው በአብላጫ ድምጽ ተስማምቶበት እንደሆነ ገልጸው ከዛ ባለፈ በሃገሪቱ በአጠቃላይ መንግስት ፍጽሟቸዋል ብሎ ፓርቲው ያመነባቸውን ስህተቶች በሙሉ ያላወገዘበት ወቅት እንደሌለም ተናግረዋል፡፡
አክለዉም ከመንግስት ጋር በጋራ መስራት ማለት መንግስትን መደገፍ ማለት እንዳልሆነም አጽእኖት ሰጥተዉበታል፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24
3.7K views07:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-08 12:02:00
በሱዳን የሁለቱ ተዋጊ ሀይሎች ዳግም የተኩስ አቁም ድርድር ማቀዳቸው ተሰምቷል፡፡
የአል አረቢያ ቴሌቪዢን ቻናል ባሰራጨው የትናንት ቀትር መረጃው ሁለቱ የሱዳን ተዋጊ አንጃዎች በሳዑዲ አረቢያና በአሜሪካ አደራዳሪነት ለዳግም የተኩስ አቁም ድርድር መጋበዛቸው ታውቋል፡፡
ሁለቱ ወገኖች ቀድሞ ለአንድ ሳምንት ከዘለቀው የተኩስ አቁም ስምምነት በኃላ ለተጨማሪ አምስት ቀናት የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ መድረሳቸው ቢነገርም በመሃል ግን በአየርና በምድር ወደ ቀደመው ከባድ ጦርነት መመለሳቸው ይታወቃል፡፡
አሁንም ሁለቱ ተዋጊ ሀይሎች ከካርቱምና ከሌሎቹም ከተሞች ጦርነት እጃቸውን ሰብሰበው ይቀመጡ ዘንድ ከአሜሪካና ከሳዑዲ አረቢያ መንግስታት ጥሪ ቀርቦላቸዋል፡፡
የሱዳን ጦር ሀይልና የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሀይሎች ቀጥተኛ ባልሆነ መንገድ እንዲወያዩ ግብዣ ቀርቦላቸዋል ቢባልም ከሁለቱም ወገኖች የተሰጠ አስተያየት የለም ሲል የአሜሪካ ድምጽ ዘግቧል፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24
4.1K views09:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-08 11:00:00
ከአዲስ አበባና ኦሮሚያ ልዩ ዞን ቤታቸዉ የፈረሰባቸዉ ዜጎች ለደብረ ብርሀን ከንቲባ ፅፈት ቤት የድጋፍ ይደረግልን ጥያቄ እያቀረቡ ነው፡፡
በአዲስ አበባና በዙሪያዋ አንዳንድ አካባቢዎች ህገ ወጥ ቤት ግንባታ በሚል የቤት ፈረሳ እየተካሄደ ነዉ፡፡
በዚሁ ቤት ፈረሳ ሳቢያ ዜጎች ወደተለያዩ አካባቢዎች እየፈለሱ ይገኛል ከነዚህም መካከል ቁጥራቸዉ በትክክል ያልታወቀ ዜጎች መግባታቸዉን የደብረ ብርሀን ከተማ አስተዳደር የስነ ህዝብ ባለሙያ እና አስተባባሪዉ አቶ አንተነህ ገብረ እግዚአብሄር ተናግረዋል፡፡
ቤታቸዉ ፈርሶ ወደ ደብረ ብርሃን ከተማ ከገቡት ዉስጥ በአባወራ ደረጃ ብቻ ከ1 ሽህ በላይ ዜጎች ለደብረ ብርሀን ከንቲባ ፅፈት ቤት የቦታና ሌሎች አስቸኳይ ድጋፍ ይደረግልን ጥያቄ ማቅረባቸዉ ለአሀዱ ገልፀዋል፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24
3.9K views08:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-08 10:32:19
በመቀሌ ኢንደስተሪ ፓርክ ዉስጥ ተሰማርተዉ የነበሩ የዉጭ ባለሃብቶችን ዳግም ወደ ስራ እንዲገቡ ለማደረግ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑ ተገለፀ፡፡
በሰሜኑ ክፍል በነበረዉ ጦርነት ምክንያት ችግር ዉስጥ የነበረዉ የመቀሌ ኢንደስተሪ ፓርክን አሁን ላይ ወደ ስራ ለማስገባት የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ከነዚህም ዉስጥ በጦርነቱ ምክንያት ወደ ሀገራቸዉ የገቡ የዉጭ ባለሀብቶችን ወደ ክልሉ ተመልሰዉ ዳግም ስራ እንዲጀምሩ እና በተለያዩ ዘርፎች ኢንቨስት እንዲያደርጉ ለማድረግ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑ ነዉ የተገለፀዉ፡፡
ከቀዳሚ ስራዎች መካከልም የባለሀብቶቹን የንብረት ጉዳት መጠን እና የደረሰዉን ዉድመት ማጥናት አንዱ ሲሆን በዚህም በተገኘ ዉጤት ፓርኩ ምንም አይነት ጉዳት እንዳልደረሰበት እና የተጎዳ ንብረትም አለመኖሩን ወደ ስፍራዉ የተላከ ልኡ ክቡድን ማረጋገጡን የገለጹት በኢንደስተሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬ የኮርፖሬሽኑ ፅህፈት ቤት ሃላፉ አቶ ፍፁም ከተማ ናቸዉ፡፡
ይህንን ዉጤት በመከተልም ባለሃበቶች እንዲመለሱ የሚያደርጉ ዉይይቶች ሲደረጉ መቆየታቸዉንና በዚህም ተመልሰዉ ወደ ስራ ለመግባት ፍላጎት ያሳዩ የዉጭ ባለሀብቶች መኖራቸዉን አቶ ፍጹም አስታዉቀዋል፡፡

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24
3.9K views07:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-05 16:21:00
የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሀይሎች በካርቱም የሚገኘውን ሙዚየም መቆጣጠራቸው ተገልጿል፡፡
የሙዚየሙ ምክትል ዳይሬክተር በሰጡት ማብራሪያ የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሀይሎች በካርቱም የሚገኘውን እና ትልቁን ሙዚየም መቆጣጠራቸውን አስታውቀው በውስጡ የሚገኙትን ቅርሶች ይጠብቁና ይንከባከቡ ዘንድ አግባብተዋቸዋል ነው የተባለው፡፡
ከባለፈው ሚያዝያ አጋማሽ ጀምሮ ከሀገሪቱ ጦር ሀይል አባላት ጋር ሲዋጉ የነበሩት የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሀይሎች ሙዚየሙን የተቆጣጠሩት ባሳለፍነው አርብ መሆኑም ነው የተሰማው፡፡
የፈጥኖ ደራሽ ሀይሎቹ ሙዚየሙን ከተቆጣጠሩ በኋላ በለቀቁት የምስል መረጃ በሙዚየሙ ላይ አንዳች ጉዳት እንዳልደረሰና ሙዚየሙን ለመጎብኘት የሚፈልጉ ካሉም በሰላም መጥተው መጎብኘት እንደሚችሉ ገልጸዋል፡፡
በሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሀይሎች እጅ የገባው ሙዚየም የጥንታዊ የሰው ቅሪተ አካል ጨምሮ በርካታ ቅርሶችን የያዘ እንደሆነ የዘገበው አልአረብያ ነው፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24
5.7K views13:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-05 15:30:00
የግብጽ ድምበር ጠባቂዎች በእስራኤል ጦር ሀይል ላይ ጥቃት መሰንዘራቸው ተነግሯል፡፡
የግብጽ ድምበር ጠባቂ ፖሊሶች ተኩስ ከፍተው ሶስት የእስራኤል ወታደሮች መግደላቸው ሲገለጽ በሁለቱም ሀገራት ከፍተኛ ባለስልጣናት ዘንድ ድንጋጤን ፈጥሯል ነው የተባለው፡፡
የግብጽ ድምበር ጠባቂ ፖሊሶች ተኩሱን የከፈቱት በእስራኤል ምድር መሆኑን እና ምክንያቱ እንዳልታወቀ ተዘግቧል፡፡
የእስራኤል ጦር ሀይል ባወጣው መግለጫ የሁለቱ ሀገራት መንግስታት ምክንያቱን ለማዎቅ በጋራ ምርመመራ መጀመራቸውን አስታውቋል፡፡
ግብጽ በመካከለኛው ምስራቅ ቀጠና በእስራኤል እና በኢራን በሚደገፉት ታጣቂ ሀይሎች መካከል ሰላምና ጸጥታ ይሰፍን ዘንድ በዲፕሎማሲው ረገድ ጥረት የምታደርግ ሀገር መሆኗ ይታወቃል፡፡ ከእስራኤል ጋር የሰላም ስምምነት በመፈራረም ረገድም የመጀመሪያዋ የአረብ ሀገር ናት፡፡
ባሳለፍነው ቅዳሜ የግብጽ የድምበር ጠባቂ ፖሊሶች የፈጸሙት ጥቃት ምናልባትም ለሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ዳግም መሻከር ምክንያት እንዳይሆን የሚል ስጋት መኖሩን የዘገበው ዲፌንስ ኦፍ ዴሞክራሲስ ነው፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24
4.7K views12:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ