Get Mystery Box with random crypto!

ብሄርን መሰረት አድርገው የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የዜግነት እሳቤን የሚያራምዱ የፖለቲካ ፓር | AHADU RADIO FM 94.3

ብሄርን መሰረት አድርገው የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የዜግነት እሳቤን የሚያራምዱ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ለማደከም አበክረው እንደሚሰሩ ኢዜማ አስታወቀ፡፡
እንደ ሀገር ያለውን የፖለቲካ ምህዳር ለማስፋት እና ገዢ የሆኑ ሃሳቦችን ለዜጎች በማቅረብ ተወዳዳሪ በመሆን ረግድ በፓርቲዎች ላይ የሚነሱ በርካታ ቅሬታዎች መኖራው ይታወቃል፡፡
አብዛኞቹ ፍቃድ ተሰጥቷቸው የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ብሄር ተኮር መሆናቸው ሃገራዊ መግባባት ለመፍጠር በሚደረገው ጥረት ላይ የራሱ የሆነ አሉታዊ ተጽእኖ እንዳሳደረም ይታመናል፡፡
ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ከአሃዱ መድረክ ጋር በነበራቸው ቆይታ ላይ ለተነሳላቸው ጥያቄ ምላሽ የሰጡት የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ፓርቲ ምክትል መሪ አርክቴክት ዮሃንስ መኮንን በሃገሪቱ እየተንቀሳቀሱ ያሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ብሄር ተኮር እና ዜግነትን የሚያቀነቅኑ ሁለት ጽንፎች መሆናቸውን አስታውሰው ይህ መሆኑ ከፍተኛ የሃሳብ ልዩነት እንዲኖር ማድረጉን ተናግረዋል፡፡
አርክቴክት ዮሃንስ አክለውም በተለይ ብሄርን መሰረት አድርገው የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የአንድነት ሃይሉ ላይ የሚያሳድሩት ጫና የጎላ መሆኑንና ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ፓሪቲዎችን ለማዳከም እና ለማሽመድመድ አበክረው እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24