Get Mystery Box with random crypto!

በአማራ ክልል ምክር ቤት የሚገኙ የአብን ተወካዮች በህግ ማስከበር ሽፋን በክልሉ እየተካሄደ ያለው | AHADU RADIO FM 94.3

በአማራ ክልል ምክር ቤት የሚገኙ የአብን ተወካዮች በህግ ማስከበር ሽፋን በክልሉ እየተካሄደ ያለው የመብት ጥሰት እንዲቆም ጠየቁ፡፡
በአማራ ክልል ምክር ቤት የሚሳተፉ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) አባላት ወቅታዊ የክልሉን ሁኔታ አስመልክተው መግለጫ ማውጣታቸው ይታወሳል፡፡
በመግለጫውም በአማራ ክልል ለአርሶ አደሮች በቂ የማዳበሪያ አቅርቦት እንዲደርስ ፣ በህግ ማስከበር ሽፋን እየተካሄዱ ያሉ የመብት ጥሰቶች እንዲቆሙ ፣ በክልሉ የሚስተዋለው የፌዴራል መንግስት የአስተዳደር ጣልቃ ገብነት እንዲቆምና ሌሎች ጉዳዮችም ተነስተዋል፡፡
ይህን አስመልክቶም አሃዱ በአማራ ክልል ምክር ቤት የአብን ተወካይ ፤ የባህር ዳርና አካባቢው አስተባባሪ ዶክተር በቃሉ ታረቀኝን አነጋግሯል፡፡
በህግ ማስከበር ሽፋን የክልሉ ዜጎች እየተሳደዱ ፣ እየተገደሉና ሰፊ ጦርነትም ተከፍቶባቸዋል ያሉት ዶክተር በቃሉ በዚህ ዘመቻም አድራሻቸው የት እንደሆነ የማይታወቁ ዜጎች አሉ በመሆኑም ይህ አይነቱ የመብት ጥሰትም በአስቸኳይ መቆም አለበት ሲሉ አሳስበዋል፡፡
እንዲህ ያሉ እንቅስቃሴዎች ከክልል አልፎ ለሃገር ቀጣይ ሰላምና መረጋጋትን ከማስፈን አንጻር ፈተና ስለሚሆን መንግስት በትኩረት እንዲያስብ በመግለጫችን ጠይቀናል ሲሉም አብራርተዋል፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24