Get Mystery Box with random crypto!

መንግስት በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሱ የኤርትራ ወታደሮችን ከክልሉ ለማስወጣት ቁርጠኛ መሆን እንደሚ | AHADU RADIO FM 94.3

መንግስት በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሱ የኤርትራ ወታደሮችን ከክልሉ ለማስወጣት ቁርጠኛ መሆን እንደሚገባዉ የፓለቲካ ምሁራን ገለጹ፡፡
የፌዴራል መንግስትና ህዉሃት በፕሪቶሪያ በተካሄደው ድርድር መሰረት የሰላም ስምምነት ላይ መድረሳቸው የሚታወቅ ነው፡፡
ሁለቱ አካላት ጦርነቱን ቋጭተው ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴ መመለሳቸው ትልቅ ጉዳይ መሆኑን ያነሱት የፖለቲካ ሳይንስና አለም አቀፍ ግንኙነት መምህሩ አቶ ሱራፌል ጌታሁን ሲሆኑ በክልሉ አሁንም በህወሃት አመራሮች በኩል የጦርነት ጉሰማዎች ሲሰሙ ይሰተዋላል ብለዋል፡፡
በክልሉ በተፈጸመው የእርዳታ እህል ስርቆት ምክንያትም የአለም ምግብ ፕሮግራም እርዳታ ማቋረጡን አስታውሰው በተለያዩ አካባቢዎች እህሉ በገበያ ቦታዎች ላይ መሸጡም እንደተነገረ ገልጸዋል፡፡
እርዳታው ለዜጎቹ በከፍተኛ ሁኔታ ስለሚያስፈልጋቸው ድርጊቱ ተገቢ አለመሆኑን ጠቅሰው ክልሉ ድርጊቱን የፈጸሙትን በመለየትና ተጠያቂ በማድረግ እርዳታው በሚቀጥልበት ሁኔታ ላይ በትኩረት መስራት አለበት ብለዋል፡፡ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የኤርትራ ወታደሮችን በተመለከተም ሰራዊቱ ክልሉን ለቆ እንዲወጣ የማድረግ ዋነኛ ስራ የፌዴራል መንግስት በመሆኑ የተለያዩ የዲፕሎማሲ ስራዎችን በመስራት ተፈጻሚ ማድረግ አለበት ሲሉም አስገንዝበዋል፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24