Get Mystery Box with random crypto!

AHADU RADIO FM 94.3

የቴሌግራም ቻናል አርማ ahaduradio — AHADU RADIO FM 94.3 A
የቴሌግራም ቻናል አርማ ahaduradio — AHADU RADIO FM 94.3
የሰርጥ አድራሻ: @ahaduradio
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 22.23K
የሰርጥ መግለጫ

አሐዱ ራድዮ 94.3
Your source for top local and international news and analysis.
"Voice of Ethiopian"
የአሐዱ የቴሌግራም ቻናል ቤተሰብ በመሆን ወቅታዊና እውነተኛ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-07-06 14:39:59
ከጤና መድህን አገልግሎት የሚሰበሰበውን ክፍያ ወደ አንድ ቋት ለማስገባት ስራዎች እየተሰሩ መሆኑ ተገለፀ፡፡
ለጤና መድህን አገልግሎት ተብሎ ከአባላት መዋጮ ከሚሰበሰብ ገንዝብ ውስጥ ወደ ባንክ የማይገባ እና በቀበሌ አመራሮች እጅ ገብቶ ለተፈለገለት አላማ ሳይውል የሚቀር ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ መኖሩ መገለጹ የሚታወስ ነው፡፡
አሐዱም ስለጉዳዩ የኢፌድሪ ጤና መድህን አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አማካሪ አቶ ዳምጠው ጥላሁን አነጋግሯል፡፡
በዋና መስሪያ ቤቶች እና በቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቶች ላይ የተሰራው የኦዲት ሪፖርት የ2013ዓ.ም የነበረውን ነው ያሉ ሲሆን የማህበረሰብ የጤና መድህን የአንድ አመት መድህን በመሆኑ የሚሰበሰበው የገንዘብ መጠንም በአባላት ቁጥር ላይ ተመርኩዞ ነው ብለዋል፡፡
የኦዲት ሪፖርቱ አዲሱ የጤና መድህን ተጠቃሚነት አባል የመሆን አስገዳጅ አዋጅ ሳይወጣ በፊት ስለነበረ ይሰበሰባል የተባለው የገንዘብ መጠንም በመድህኑ ተጠቃሚ አባል ቁጥር ላይ በመሆኑ ላይሳካ ይችላል ያሉ ሲሆን በ2014ዓ.ም አስገዳጅ አዋጁ ከወጣ በኃላ መሻሻሎች እንዳሉ እና በቀጣይ በ2016ዓ.ም የተስተዋሉ ችግሮችን እና የአፈጻጸም ጉድለቶችን በመገምገም የክፍያ አሰባሰብ ስርአቱ ላይ ማሻሻያዎች እና ለውጦችን በማድረግ የገንዘብ አሰባሰብ ሂደቱን በአንድ ቋት ለማድረግ እቅድ ይዘው እየተንቀሳቀሱ ነው ብለዋል፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24
1.9K views11:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-06 11:51:02
የሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ የማጣራት ስራው በትምህርት ተቋማት ላይ ሊካሄድ እንደሚገባ ተገለፀ፡፡
በተለያዩ ዘርፎች ላይ የሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ይዘው የሚሰሩ ባለሙያዎች ቁጥር ቀላል የሚባል እንዳልሆነ በተደጋጋሚ ሲገለፅ የሚስተዋል ሲሆን በተገቢው መንገድ አጣርቶ እርምጃ የመውሰድ ስራው ከሁሉም አስቀድሞ በትምህርት ተቋማት ላይ ሊካሄድ እንደሚገባ የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ፕሬዘዳንት ዶ/ር ዮሀንስ በንቲ ለአሐዱ ገልጸዋል፡፡
የሀሰተኛ ማስረጃ በሁሉም ዘርፎች ላይ የሚስተዋል ችግር እንደሆነ ገልጸው በትምህርት ተቋማት ውስጥ ሲሆን ግን በፍጹም ተቀባይነት የሌለው ከመሆኑ ባለፈ በትውልድ እና በአገር ላይ በሂደት የሚያመጣው አደጋ ከፍተኛ እንደሆነ መገንዘብ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
ይህንን ለመከላከል እና ተገቢውን መፍትሄ እንዲያገኝም ከትምህርት እና ስልጠና ባለስልጣን እና ከሁሉም ክልሎች የትምህርት ቢሮዎች ጋር ተቀራርቦ የመስራት ፍላጎት እንዳላቸውም ጠቁመዋል፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24
2.3K views08:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-06 09:34:05
መንግስት ለሚዲያ ተቋማት እና ሞያተኞች ከለላ የማድረግ ሃላፊነት እና ግዴታ ባለመወጣቱ ዘርፉ ለአደጋ መጋለጡ ተገለጸ፡፡
ከጋዜጠኞች እስር እና አፈና እንዲሁም ሚዲያዎች ላይ ከሚደርሱ ጫናዎች አንጻር ከቅርብ ጊዚያቶች ወዲህ በርካታ ቅሬታዎች በተደጋጋሚ እየተነሱ እንደሆነ ይታወቃል፡፡
ይህንኑ ጉዳይ አስመልክቶ አሐዱ ያነጋገራቸው የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት ፕሬዝዳንት አቶ አማረ አረጋዊ በመንግስት በኩል ሚዲያን የሚቆጣጠረው አካል ከመንግስት ነጻ ሆኖ ተጠሪነቱ ለፓርላማ ይሆናል ቦርዱም በፓርላማው ይሾማል ተብሎ ከጸደቀ በኋላ መንግስት እራሱ ቦርዱን በመሾሙ ቅሬታ ማቅረባቸውን አስታውሰው እስካሁን ድረስ በዚህ ጉዳይ ላይ ምላሽ እንዳልተሰጣቸው ተናግረዋል፡፡
ፕሬዝዳንቱ አክለውም በሃገራችን በሚዲያ ላይ የሚፈጠሩ ችግሮች የህግ ሳይሆኑ የአፈጻጸም መሆናቸውን ገልጸው መንግስት ለጋዜጠኞች እና ሚዲያው ከለላ ማድረግ ሲገባው አሁን ባለው ነባራዊ እውነታ ያንን እንደማይደረግም አንስተዋል፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24
2.5K views06:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-05 11:45:08
በዜጎች ላይ የሚፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ለማስቆም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፍትህ እና የህግ ቋሚ ኮሚቴ ሀላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባ ተገለጸ፡፡
የሰብዓዊ መብት ኮምሽን በዜጎች ላይ የሚፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በተመለከተ አስፈላጊው እርምጃ እንዲወሰድ በተለያየ ጊዜያት ሪፖርት እና መግለጫዎችን ያወጣል፡፡
መንግስት የሰብዓዊ መብት ጥሰት በዜጎች ላይ ከተፈጸመ በኃላ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ከመፈጸሙ አስቀድሞ የመከላከል ስራ መስራት እንዳለበት ለአሀዱ የተናገሩት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ፎረም ዋና ዳይሬክተር አቶ ተረፈ ጠጌቲ ናቸው፡፡
የሰብዓዊ መብት ኮምሽን እና ሌሎች ተቋማትን ጨምሮ በሚፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ላይ የሚያወጡትን ሪፖርት ወስዶ ችግሩን ከመፍታት ይልቅ ክልሎችን ጨምሮ ተቃራኒ የሆነ ምላሽ የመስጠት ሁኔታዎች ይስተዋላል ነው ያሉት፡፡
በኮምሽኑም ሆነ በመንግስት በኩል የሚወጡ የተለያዩ መግለጫዎችና ሪፖርቶች ማህበረሰቡ ላይ ግራ መጋባትን የሚፈጥር እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
የሰብዓዊ መብት ኮምሽን የሚያወጣው ሪፖርት በመንግስት በኩል ተግባራዊ እንዲሆን የጋራ አሰራርን ለመዘርጋት እንዲቻል የህዝብ ተወካይዎች ምክር ቤት የፍትህ እና የህግ ቋሚ ኮሚቴ መመሪያ በማዘጋጀት ሀላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24
3.3K views08:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-04 15:45:14
ምርጫ ቦርድ በ4 ዓመት የስራ ሂደት ውስጥ የገጠመውን ችግሮች ቢያሳውቅ ለዲሞክራሲ ሽግግር በቀጣይ ለሚሰሩ ስራዎች አስተዋጽኦ እንደሚኖረው የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ገለጸ፡፡
አጋጠመኝ ባሉት የጤና እክል ምክንያት የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢዋ ብርቱካን ሚደቅሳ በገዛ ፍቃዳቸው ከተሰጣቸው ሀላፊነት ለመልቀቅ ጥያቄ ማቅረባቸው የሚታወስ ነው፡፡
በቀጣይ በተቋሙ አሰራር ላይ ምን ስጋት የሚፈጥሩ ጉዳዮች አሉ ወደ ፊት የሚሰራው ስራ በምን መልኩ ተግባራዊ ሊደረግ ይገባል ሲል አሐዱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ዋና ጸሀፊ ዶክተር ራሄል ባፌን ጠይቋል፡፡
የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢዋ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ በ4 ዓመት ውስጥ በተቋሙ ያሉትን ጉድለቶች እና ክፍተቶች በጽሁፍ አሊያም በማንኛውም መንገድ ማሳወቅ ቢችሉ ለዲሞክራሲ ሽግግር፤ በቀጣይ ለሚሰሩ ስራዎች አስተዋጾ እንዳለው ተናግረዋል፡፡
እስከ ወረዳ ድረስ በመውረድ 6ኛውን ሀገራዊ ምርጫ ፍትሀዊ ለማድረግ ጥረቶችን ሲያደርጉ መቆየታቸውን አስታውሰው የነበሩ ማነቆዎችን ጨምሮ ተቋሙን ነጻ እና ገለልተኛ ማድረግ ያልተቻለበትን ምክንያት ለህዝብ እና ለሀገር ጥቅም ሲሉ ማሳወቅ እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24
3.5K views12:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-04 11:45:11
ከአንጋፋ መምህራን የደረጃ እድገት ጋር በተያያዘ ያቀረበዉ ጥያቄ እስካሁን ምላሽ አለማግኘቱን የአዲስ አበባ መምህራን ማህበር ገለፀ፡፡
ማህበሩ ከዚህ ቀደም በሰጠዉ መግለጫ የአንጋፋ መምህራን የደረጃ እድገትን በተመለከተ በተደጋጋሚ ጊዜ ለሚመለከተዉ አካል ጥያቄዎችን ቢያቀርብም ምላሽ ባለማግኘቱ እስከ ጠቅላይ ሚንስትር ፅህፈት ቤት ድረስ ጥያቄ ለማቅረብ መዘጋጀቱን መግለፁ ይታወሳል፡፡ በአሁኑ ወቅትም ጉዳዩን ለኢትዮጵያ መምህራን ማህበር መተላለፉ እና እንደ ከዚህ በፊቱ ምላሹ የሚዘገይ ከሆነ ወደ በላይ አካል የመምህራኑን ጥያቄ ማቅረባቸው እንደማይቀር የተናገሩት የአዲስ አበባ መምህራን ማህበር ፕሬዝደንት አቶ ድንቃለም ቶሎሳ ናቸዉ፡፡
ፕሬዝደንቱ አክለዉም ለሀገር ባለዉለታ የሆኑ አንጋፋ መምህራን ምንም አይንት የደመወዝ እና የደረጃ እድገት ሳይሰጣቸዉ ጡረታ ለመዉጣት እየተገደዱ ሲሆን ይህ ደግሞ ዉለታቸዉን ማቅለል በመሆኑ ጥያቄዉ በአፋጣኝ ምላሽ ሊሰጠዉ ይገባል ሲሉም ጠይቀዋል፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24
4.7K views08:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-03 14:51:53
የፌደራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ከፍተኛ የሆነ የበጀት ጉድለት ያለባቸውን ተቋማት የወንጀል ምርምራ እንዲደረግባቸው ጉዳዩን ለፌደራል ፖሊሲ ኮምሽን አሳልፎ ሊሰጥ እንደሚገባ ተገለጸ፡፡
ከመመሪያ እና ደንብ ውጪ ያለአግባብ ክፍያ የፈጸሙ፤ ከተያዘላቸው በጀት ውጪ የተጠቀሙ እና ሌሎች ጉድለቶች የተገኘባቸው በርካታ ተቋማትን አስመልክቶ የፌደራል ዋና ኦዲተር ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሪፖርት ማቅረቡ የሚታወስ ነው፡፡
ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት በተደጋጋሚ ለህዝብ ተወካዮዎች ምክርቤት በሚያቀርበው ሪፖርት መሰረት ተቋማቱ ተጠያቂ እንዲሆኑ ምን መደረግ አለበት ሲል አሀዱም የህግ ባለሙያዎችን ጠይቋል፡፡
የፌደራል ዋና ኦዲተር ባቀረበው ሪፖርት መሰረት የመንግስት ተጠሪ ተቋማት ህግ እና ስርዓትን መሰረት አድረገው በጀታቸውን እያስተዳደሩ እንዳልሆነ ማረጋገጥ ይቻላል ያሉት የህግ ባለሙያው አቶ ካሳሁን ሙላቱ ናቸው፡፡
ሪፖርት የሚቀርብበት ዋና ምክንያት ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ እንደሆነ ለኦዲተር ዋና መስሪያቤት በአዋጅ የተሰጠው ስልጣን ላይ በግልጽ የሚያመላክት የመሆኑንነ የተናገሩት የህግ ባለሙያው ከፍተኛ የሆነ የበጀት ጉድለት ያገኛባቸውን ተቋማት የወንጀል ምርምራ እንዲደርገባቸው ጉዳዩን ለፌደራል ፖሊስ ኮምሽን አሳልፎ መስጠት እና ፍርድ ቤትም በማቅርብ ሀላፊነቱን መወጣት እንዳለበት ተናግረዋል፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24
3.9K viewsedited  11:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-03 11:45:09
በሃገሪቱም ሆነ በኦሮምያ ክልል ውስጥ ኦነግ በሚል መጠሪያ የሚንቀሳቀስ የፖለቲካ ፓርቲ አንድ ብቻ መሆኑ ተገለጸ፡፡
የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ኦነግ የተመሰረተበትን ሃምሳኛ አመት ምክንያት በማድረግ የፓርቲው አባላት እና ደጋፊዎችን ጨምሮ ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው በርካታ እንግዶች በተገኙበት ውይይት አድርጓል፡፡
በእለቱ የፓርቲውን እንቅስቃሴ አስመልክቶ በተለይ ከኦነግ ሸኔ ጋር በተያያዘ ያለው እውነታ ምንድን ነው ሃምሳኛ አመቱን እያከበረ ያለውስ የትኛው ኦነግ ነው ሲል አሃዱ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር የህዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊን አቶ ለሚ ገመቹን አነጋግሯል፡፡
አቶ ለሚ በሰጡት ምላሽም በኦሮሞ ነጻነት ግንባር ስም የሚንቀሳቀሱ በርካታ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከዚህ ቀደምም በኦሮምያ ክልል ውስጥ እንደነበሩ አስታውሰው አሁን ላይ ግን አብዛኞቹ እንደሌሉ እና እንደከሰሙ ገልጸዋል፡፡
አክለውም በአሁኑ ሰአት በክልሉም ሆነ በሃገሪቷ ውስጥ ከሚመለከተው አካል ህጋዊ ፍቃድ ወስዶ በሰላማዊ መንገድ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው በኦቦ ዳውድ ኢብሳ የሚመራው እና ያለፉትን ሃምሳ አመታት ለኦሮሞ ነጻነት እና እኩልነት የታገለው ኦነግ መሆኑን ተናረዋል፡፡
ከዛ ውጪ በፓርቲው ስም የሚንቀሳቀሱም ሆነ የሚጠሩ ሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዎች ከፓርቲው ምንም አይነት እውቅና የተሰጣቸው አለመሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24
3.8K views08:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-03 11:13:41
ምርጫ ቦርድ እስካሁን ሲሰራ በነበረው ስራ በተጠበቀው ልክ ነጻ እና ገለልተኛ ነው ማለት እንደማይቻል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ገለጸ፡፡
ባለፉት 4 ዓመታት ከ6 ወራት የምርጫ ቦርድ የማስፈጸም አቀምን ለመጨመር፤ ተዓማኒነቱን ለማሳደግ፤ የፖለቲካ ፓርቲዎችን እንቅስቃሴ ለማገዝ እንዲሁም ነጻ እና ገለልተኛ ለማድረግ ጥረቶች ሲደረግ እንደነበር እና ስኬታማ ስራ ስለመስራቱም መገለጹ ይታወሳል፡፡
አሐዱም ምርጫ ቦርድ ባለፉት ዓመታት ነጻ እና ገለልተኛ ሆኖ ሀላፊነቱን በሚገባ ተወጥቷል ወይ ሲል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ዋና ጸሀፊ ዶክተር ራሄል ባፌን ጠይቋል፡፡
በምላሻቸውም ምርጫ ቦርድን ጨምሮ ከለውጡ በኃላ የተቋቋሙ የዶሞክራሲ ተቋማት ገለልተኛ ይሆናሉ በሚል ትልቅ ተስፋ የተጣለባቸው ቢሆንም ተግባራዊነቱ ግን የሚጠበቀውን ያህል እንዳልሆነም ተናግረዋል፡፡
6ኛውን ሀገራዊ ምርጫ ጨምሮ ነጻ እና ዲሞክራሲያዊ ይሆናል በሚል ከምርጫ ቦርድ ብዙ ተስፋ የተጣለበት ቢሆንም በሚፈለገው ልክ ተግባራዊ አለመደረጉን ይገልጻሉ፡፡
ምርጫ ቦርድ ተፎካካሪ ፓርቲዎች የጠቅላላ ጉባኤ ማድረግ እንደማይችሉ ክልከላ ሲያደርግ ቆይቶ ብልጽግና ፓርቲ ግን ከህግ እና ስርዓት ውጪ ሲያካሄድ አይሆንም ብሎ መከልከል አለመቻሉ ገለልተኛ ያለመሆኑ አንዱ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24
3.8K views08:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-01 11:12:00
በአማራ ክልል ለሚገኙ ተፈናቃዮች ከ8.3 ሚሊየን ኩንታል በላይ የምግብ ድጋፍ መደረጉ ተገለጸ፡፡
ከተለያዩ አካባቢዎች በጦርነትና በጸጥታ ችግር ከመኖሪያቸው ተፈናቅለው በአማራ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች ተጠልለው ለሚገኙ ተፈናቃዮች ከ8 ነጥብ 3 ሚሊየን ኩንታል በላይ የምግብ ድጋፍ መደረጉን የተናገሩት የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ከፍተኛ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ አታለል አቡሃይ ናቸው፡፡
ይህ ድጋፍም በዋግ ኸምራ ፣ በሰሜን ጎንደር ፣ ሰሜን ወሎ እና ሰሜን ሸዋ አካባቢ ለሚገኙ ተፈናቃዮች የተሰጠ እንደሆነ አንስተዋል፡፡
በሰሜን ሸዋ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ አጋር አካላት ከሚያደርጉት ድጋፍ ውጭ የአካባቢው ህብረተሰብና ባለሃብቱ በርካታ መጠን ያለው እርዳታ እየሰጠ መሆኑን የገለጹት ባለሙያው በቂ እርዳታ እየደረሰን አይደለም እየተባለ ያለው ከእውነት የራቀ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በዓለማቀፍ ህጎችም ሆነ በሃገር ውስጥ ባሉ ህጎች መሰረት ለአንድ ተረጂ ወይም አባወራ እርዳታ የሚቀርበው በየ45 ቀን መሆኑን አንስተው ተፈናቃዮች በአቅርቦትና ግዥ ሂደቶች ላይ የተወሰኑ መዘግየቶች ሊኖሩ እንደሚችሉ ከግምት ውስጥ ማስገባት አለባቸው ብለዋል፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24
4.5K views08:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ