Get Mystery Box with random crypto!

የፌደራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ከፍተኛ የሆነ የበጀት ጉድለት ያለባቸውን ተቋማት የወንጀል ምርም | AHADU RADIO FM 94.3

የፌደራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ከፍተኛ የሆነ የበጀት ጉድለት ያለባቸውን ተቋማት የወንጀል ምርምራ እንዲደረግባቸው ጉዳዩን ለፌደራል ፖሊሲ ኮምሽን አሳልፎ ሊሰጥ እንደሚገባ ተገለጸ፡፡
ከመመሪያ እና ደንብ ውጪ ያለአግባብ ክፍያ የፈጸሙ፤ ከተያዘላቸው በጀት ውጪ የተጠቀሙ እና ሌሎች ጉድለቶች የተገኘባቸው በርካታ ተቋማትን አስመልክቶ የፌደራል ዋና ኦዲተር ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሪፖርት ማቅረቡ የሚታወስ ነው፡፡
ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት በተደጋጋሚ ለህዝብ ተወካዮዎች ምክርቤት በሚያቀርበው ሪፖርት መሰረት ተቋማቱ ተጠያቂ እንዲሆኑ ምን መደረግ አለበት ሲል አሀዱም የህግ ባለሙያዎችን ጠይቋል፡፡
የፌደራል ዋና ኦዲተር ባቀረበው ሪፖርት መሰረት የመንግስት ተጠሪ ተቋማት ህግ እና ስርዓትን መሰረት አድረገው በጀታቸውን እያስተዳደሩ እንዳልሆነ ማረጋገጥ ይቻላል ያሉት የህግ ባለሙያው አቶ ካሳሁን ሙላቱ ናቸው፡፡
ሪፖርት የሚቀርብበት ዋና ምክንያት ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ እንደሆነ ለኦዲተር ዋና መስሪያቤት በአዋጅ የተሰጠው ስልጣን ላይ በግልጽ የሚያመላክት የመሆኑንነ የተናገሩት የህግ ባለሙያው ከፍተኛ የሆነ የበጀት ጉድለት ያገኛባቸውን ተቋማት የወንጀል ምርምራ እንዲደርገባቸው ጉዳዩን ለፌደራል ፖሊስ ኮምሽን አሳልፎ መስጠት እና ፍርድ ቤትም በማቅርብ ሀላፊነቱን መወጣት እንዳለበት ተናግረዋል፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24