Get Mystery Box with random crypto!

በሃገሪቱም ሆነ በኦሮምያ ክልል ውስጥ ኦነግ በሚል መጠሪያ የሚንቀሳቀስ የፖለቲካ ፓርቲ አንድ ብቻ | AHADU RADIO FM 94.3

በሃገሪቱም ሆነ በኦሮምያ ክልል ውስጥ ኦነግ በሚል መጠሪያ የሚንቀሳቀስ የፖለቲካ ፓርቲ አንድ ብቻ መሆኑ ተገለጸ፡፡
የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ኦነግ የተመሰረተበትን ሃምሳኛ አመት ምክንያት በማድረግ የፓርቲው አባላት እና ደጋፊዎችን ጨምሮ ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው በርካታ እንግዶች በተገኙበት ውይይት አድርጓል፡፡
በእለቱ የፓርቲውን እንቅስቃሴ አስመልክቶ በተለይ ከኦነግ ሸኔ ጋር በተያያዘ ያለው እውነታ ምንድን ነው ሃምሳኛ አመቱን እያከበረ ያለውስ የትኛው ኦነግ ነው ሲል አሃዱ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር የህዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊን አቶ ለሚ ገመቹን አነጋግሯል፡፡
አቶ ለሚ በሰጡት ምላሽም በኦሮሞ ነጻነት ግንባር ስም የሚንቀሳቀሱ በርካታ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከዚህ ቀደምም በኦሮምያ ክልል ውስጥ እንደነበሩ አስታውሰው አሁን ላይ ግን አብዛኞቹ እንደሌሉ እና እንደከሰሙ ገልጸዋል፡፡
አክለውም በአሁኑ ሰአት በክልሉም ሆነ በሃገሪቷ ውስጥ ከሚመለከተው አካል ህጋዊ ፍቃድ ወስዶ በሰላማዊ መንገድ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው በኦቦ ዳውድ ኢብሳ የሚመራው እና ያለፉትን ሃምሳ አመታት ለኦሮሞ ነጻነት እና እኩልነት የታገለው ኦነግ መሆኑን ተናረዋል፡፡
ከዛ ውጪ በፓርቲው ስም የሚንቀሳቀሱም ሆነ የሚጠሩ ሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዎች ከፓርቲው ምንም አይነት እውቅና የተሰጣቸው አለመሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24