Get Mystery Box with random crypto!

ምርጫ ቦርድ እስካሁን ሲሰራ በነበረው ስራ በተጠበቀው ልክ ነጻ እና ገለልተኛ ነው ማለት እንደማይ | AHADU RADIO FM 94.3

ምርጫ ቦርድ እስካሁን ሲሰራ በነበረው ስራ በተጠበቀው ልክ ነጻ እና ገለልተኛ ነው ማለት እንደማይቻል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ገለጸ፡፡
ባለፉት 4 ዓመታት ከ6 ወራት የምርጫ ቦርድ የማስፈጸም አቀምን ለመጨመር፤ ተዓማኒነቱን ለማሳደግ፤ የፖለቲካ ፓርቲዎችን እንቅስቃሴ ለማገዝ እንዲሁም ነጻ እና ገለልተኛ ለማድረግ ጥረቶች ሲደረግ እንደነበር እና ስኬታማ ስራ ስለመስራቱም መገለጹ ይታወሳል፡፡
አሐዱም ምርጫ ቦርድ ባለፉት ዓመታት ነጻ እና ገለልተኛ ሆኖ ሀላፊነቱን በሚገባ ተወጥቷል ወይ ሲል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ዋና ጸሀፊ ዶክተር ራሄል ባፌን ጠይቋል፡፡
በምላሻቸውም ምርጫ ቦርድን ጨምሮ ከለውጡ በኃላ የተቋቋሙ የዶሞክራሲ ተቋማት ገለልተኛ ይሆናሉ በሚል ትልቅ ተስፋ የተጣለባቸው ቢሆንም ተግባራዊነቱ ግን የሚጠበቀውን ያህል እንዳልሆነም ተናግረዋል፡፡
6ኛውን ሀገራዊ ምርጫ ጨምሮ ነጻ እና ዲሞክራሲያዊ ይሆናል በሚል ከምርጫ ቦርድ ብዙ ተስፋ የተጣለበት ቢሆንም በሚፈለገው ልክ ተግባራዊ አለመደረጉን ይገልጻሉ፡፡
ምርጫ ቦርድ ተፎካካሪ ፓርቲዎች የጠቅላላ ጉባኤ ማድረግ እንደማይችሉ ክልከላ ሲያደርግ ቆይቶ ብልጽግና ፓርቲ ግን ከህግ እና ስርዓት ውጪ ሲያካሄድ አይሆንም ብሎ መከልከል አለመቻሉ ገለልተኛ ያለመሆኑ አንዱ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24