Get Mystery Box with random crypto!

በአማራ ክልል ለሚገኙ ተፈናቃዮች ከ8.3 ሚሊየን ኩንታል በላይ የምግብ ድጋፍ መደረጉ ተገለጸ፡፡ ከ | AHADU RADIO FM 94.3

በአማራ ክልል ለሚገኙ ተፈናቃዮች ከ8.3 ሚሊየን ኩንታል በላይ የምግብ ድጋፍ መደረጉ ተገለጸ፡፡
ከተለያዩ አካባቢዎች በጦርነትና በጸጥታ ችግር ከመኖሪያቸው ተፈናቅለው በአማራ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች ተጠልለው ለሚገኙ ተፈናቃዮች ከ8 ነጥብ 3 ሚሊየን ኩንታል በላይ የምግብ ድጋፍ መደረጉን የተናገሩት የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ከፍተኛ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ አታለል አቡሃይ ናቸው፡፡
ይህ ድጋፍም በዋግ ኸምራ ፣ በሰሜን ጎንደር ፣ ሰሜን ወሎ እና ሰሜን ሸዋ አካባቢ ለሚገኙ ተፈናቃዮች የተሰጠ እንደሆነ አንስተዋል፡፡
በሰሜን ሸዋ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ አጋር አካላት ከሚያደርጉት ድጋፍ ውጭ የአካባቢው ህብረተሰብና ባለሃብቱ በርካታ መጠን ያለው እርዳታ እየሰጠ መሆኑን የገለጹት ባለሙያው በቂ እርዳታ እየደረሰን አይደለም እየተባለ ያለው ከእውነት የራቀ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በዓለማቀፍ ህጎችም ሆነ በሃገር ውስጥ ባሉ ህጎች መሰረት ለአንድ ተረጂ ወይም አባወራ እርዳታ የሚቀርበው በየ45 ቀን መሆኑን አንስተው ተፈናቃዮች በአቅርቦትና ግዥ ሂደቶች ላይ የተወሰኑ መዘግየቶች ሊኖሩ እንደሚችሉ ከግምት ውስጥ ማስገባት አለባቸው ብለዋል፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24