Get Mystery Box with random crypto!

በሚቀጥለው በጀት ዓመት ሙሉ ለሙሉ የዲጅታል መታወቂያን ተደራሽ አደርጋለሁ ሲል የአዲስ አበበ ከተማ | AHADU RADIO FM 94.3

በሚቀጥለው በጀት ዓመት ሙሉ ለሙሉ የዲጅታል መታወቂያን ተደራሽ አደርጋለሁ ሲል የአዲስ አበበ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወሳኝ ኩነትና ምዝገባ ኤጀንሲ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ አማካሪ አቶ መላክ መኮንን ለአሐዱ እንደገለጹት፣ በአዲስ አበባ ከተማ ለሚኖሩ መስፈርቱን ለሚያማሉና እድሜያቸው መታወቂያ ለማውጣት ለደረሱ ዜጎች የዲጅታል መታወቂያ ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ ነው፡፡
ኤጀንሲው ከሶስት አመት በፊት ጀምሮ የዲጂታል መታወቂያ ተደራሽ ለማድረግ ታቅዶ እየተሰራ ሲሆን ፣ እስካሁን ባለው ወይንም መረጃው እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ በአዲስ አበባ ከተማ በ11 ክፍለ ከተሞች በሚገኙ በ114 ወረዳዎች የድጂታል መታወቂያው እየተሰጠ ቢሆንም፣ 14 ወረዳዎች ተደራሽ እንዳልሆኑ አማካሪው ጠቁመዋል፡፡
አማካሪው አክለውም በኢንተርኔት መሰረተ ልማት ዝርጋታ ጋር በተያያዘ ችግሮች በመኖራቸው የዲጂታል መታወቂያውን በተያዘለት ቀነ ገደብ ተደራሽ ማድረግ አልተቻለም ብለዋል፡፡
ኤጀንሲው እስካሁን ባለው ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን የዲጅታል መታወቂያ ተደራሽ ማድረግ እንደተቻለ ከመስረተ ልማት ጋር ያሉ ችግሮችን በመቅረፍ በቀጣይ በ2016 በጀት ዓመት በመጀመሪያዎቹ ሩብ ዓመታት የዲጅታል መታወቂያውን ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24