Get Mystery Box with random crypto!

በአንድ ሚንስቴር መስሪያ ቤት ብቻ የጎዳና ተዳዳሪነትን ችግር ሙሉ ለሙሉ መፍታት እንደማይቻል ተገለ | AHADU RADIO FM 94.3

በአንድ ሚንስቴር መስሪያ ቤት ብቻ የጎዳና ተዳዳሪነትን ችግር ሙሉ ለሙሉ መፍታት እንደማይቻል ተገለፀ፡፡
ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በከተሞች ላይ ኑሮአቸውን በጎዳና ተዳዳሪነት የሚገፉ ህጻናት ቁጥር እየጨመረ የሚገኝ ሲሆን ከችግሩ ስፋት አኳያ በአንድ ሚንስቴር መስሪያ ቤት ብቻ መፍትሄ እንዲያገኝ ማድረግ እንደማይቻል የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የሴቶችና ሕፃናት ዘርፍ ሚኒስትር ደኤታ ወ/ሮ አለሚቱ ኡምድ ለአሐዱ ገልጸዋል፡፡
በአገር አቀፍ ደረጃ በተለያዩ ምክንያቶች ወደ ጎዳና የሚወጡ ህፃናት ከየት አካባቢ እንደመጡ እና ምክንያቶቻቸው ላይ ሰፊ ጥናት በማድረግ ወደ ቤተሰቦቻቸው እንዲመለሱ የማድረግ እንዲሁም አማራጭ ለሌላቸው ደግሞ በጊዜያዊነት ከጎዳና ህይወት ተላቅቀው የሚኖሩበትን መንገድ የማመቻቸት ስራ እየተሰራ ሲሆን ከችግሩ ስፋት አኳያ ግን በቂ የሚባል እንዳልሆነ አስታውቀዋል፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24