Get Mystery Box with random crypto!

የተሸሻለው የቤት ግብር ክፍያ ሂደቱ አቅመ ደካሞችን እና ጡረተኞችን ከግምት ባስገባ መልኩ እንደሚከ | AHADU RADIO FM 94.3

የተሸሻለው የቤት ግብር ክፍያ ሂደቱ አቅመ ደካሞችን እና ጡረተኞችን ከግምት ባስገባ መልኩ እንደሚከወን ተገለጸ፡፡
የቤት ግብር ክፍያን በተመለከተ በቅርቡ የወጣውን አዋጅ ተከትሎ በሀገሪቱ ያለውን ነባራዊ እውነታ ያገናዘበ አይደለም በሚል በርካታ ቅሬታዎች ሲነሱ እንደ ነበር ይታወሳል፡፡
ይህንኑ ጉዳይ አስመልክቶ ከአሐዱ መድረክ ጋር ቆይታ ያደረጉት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የታክስ ጉዳዮች ዘርፍ ምክትል ቢሮ ሃላፊ አቶ ዘገየ በላይነህ በማህበረሰቡ ዘንድ የሚነሱ ቅሬታዎች ተገቢ መሆናቸውን አስታውሰው ሆኖም ግን የተጣራ መረጃን ካለማግኘት በሚፈጠር የግንዛቤ እጥረት የሚነሱ ቅሬታዎችን ግንዛቤን በመፍጠር ለማስተካካል እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ከዚህ ባሻገር የግብር ክፍያ ሂደቱ በማህበረሰቡ ላይ ጫና እንዳያሳድር የረጅም ጊዜ የክፍያ ሂደት እንዲኖር በማድረግ ዜጎች በረዥም ጊዜ ውስጥ ተረጋግተው የሚከፍሉበት አሰራር እንዲኖር መደረጉን ገልጸዋል፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24