Get Mystery Box with random crypto!

በሀዋሳ ከተማ ህገ-ወጥ የነዳጅ ግብይት መስፋፋቱ ተገለፀ፡፡ በመላ ሀገሪቱ የነዳጅ ግብይት በኤሌክት | AHADU RADIO FM 94.3

በሀዋሳ ከተማ ህገ-ወጥ የነዳጅ ግብይት መስፋፋቱ ተገለፀ፡፡
በመላ ሀገሪቱ የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የተለያዩ እንከኖችን መቀነስ ቢቻልም እንኳን በተለያዩ አካባቢዎች ያለዉ ህብረተሰብ ቴክኖሎጅዉን የመቀበል አቅም በተወሰነ ደረጃ ዝቅ ማለት ህገ-ወጥ የነዳጅ ግብይትን ለመቆጣጠር ተግዳሮት እንደሆነ ተነስቷል፡፡
ከዚሁ ጋር በተያያዘ በሀዋሳ ከተማ ያለዉ ህገ-ወጥ የነዳጅ ግብይት ከፍተኛ መሆኑን የገለፁት በነዳጅ እና ኢነርጅ ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሳህረላ አብዱላሂ ናቸዉ፡፡
ከዚሁ የህገ-ወጥ ንግድ ጋር በተያያዘ በሻሸመኔ እና ሀዋሳ አካባቢዎች የሚገኙ 5 ማደያዎች በጊዜያዊነት መታገዳቸዉም የሚታወስ ሲሆን ከተማዋ ካላት የተጠቃሚ እና በስራ ላይ ያሉ ማደያዎች ቁጥር አለመመጣጠን ጋር ተያይዞ የአቅርቦት ችግር እንዲጨምር አያደርግም ወይ ሲል አሐዱ ዳይሬክተሯን ጠይቆ ባገኘው ምላሽ፤ በሙሉ አቅማቸዉ የሚሰሩ ማደያዎች ቁጥር አነስተኛ መሆን ችግር ሊፈጥር እንደማይችል ተናግረዋል፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24