Get Mystery Box with random crypto!

ወንጀለኞችን ተጠያቂ የማድረግ ስራ የአንድ ተቋም ብቻ ሀላፊነት እንዳልሆነ የፍትህ ሚኒስቴር አስታ | AHADU RADIO FM 94.3

ወንጀለኞችን ተጠያቂ የማድረግ ስራ የአንድ ተቋም ብቻ ሀላፊነት እንዳልሆነ የፍትህ ሚኒስቴር አስታወቀ፡
ወንጀለኞችን በቁጥጥር ስር ስታውሉ እንጂ አስተማሪ እርምጃ ስትወስዱ እየታየ አይደለም የሚል ጥያቄ እና አስተያየት ማህበረሰቡን ጨምሮ ከተለያየ አካላት እየተነሳ ነው ያሉት የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊሲ የኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ሀላፊ አቶ ጄላን አብዲ ፤
የፖሊስ ስራ መረጃን አሰባስቦ ወንጀለኛን ለሚመለከተው አካል ማቅረብ እንጂ አስተማሪ እርምጃ የመውሰድ ሀላፊነት የፍርድ ቤት ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በዚህ ጉዳይ ላይ አሐዱ የጠየቃቸው የፍትህ ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት እና የኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ አወል ሱልጣን ወንጀለኛን ተጠያቂ የማድረግ ስራ ለአንድ ተቋም ብቻ የሚሰጥ ሳይሆን የፖሊስ፤የፍርድ ቤት ፤የአቃቤ ህግ እንዲሁም የማረሚያ ቤት የጋራ ስራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የግልጸኝነት እና የተጠያቂነት መርህ በሁሉም ተቋም ተግባራዊ መደረግ እንዳለበት የተናገሩት አቶ አወል ፖሊስ ምርመራውን ካከናወነ በኃላ ጉዳዩ ምን ላይ ደረሰ የሚለውን ማወቅ እና ማሳወቅ ይጠበቅበታል ነው ያሉት፡፡
ፖሊስ በተለያየ ወንጀል የጀመረውን የምርመራ ስራ ለአቃቤ ህግ ካስተላለፈ በኃላ በመጨረሻ የሚሰጠው ውሳኔ አይመለከተኝም ማለት ስለማይችል የሚሰጠው ውሳኔ ምንም ይሁን ምን እንደ ስኬት ሊያየው እንደሚገባ ገልጸው አቃቤ ህግ ክስ ስለመመስረቱ ፍርድ ቤት ስለመቅጣቱ የመጨረሻውን ውሳኔ ለማህበረሰቡ የማሳወቅ ሀላፊነት እንዳለበት ገልጿል፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24