Get Mystery Box with random crypto!

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደንና የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ የስልክ ውይይት ማድረጋቸ | AHADU RADIO FM 94.3

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደንና የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ የስልክ ውይይት ማድረጋቸው ተገልጿል፡፡
የሁለቱ ሀገራት መሪዎች ሰፊ የስልክ ውይይት ማድረጋቸው ሲነገር የውይይታቸው ዋና ጭብጥ በወቅታዊነት በሩሲያ ሰላለው ሁኔታ መሆኑም ነው የተዘገበው፡፡
የዩክሬኑ ፕሬዝዳንትና የአሜሪካው አቻቸው በውይይታቸው አሜሪካ ለዩክሬን ያልተገደበ የወታደራዊ እና የሰብዓዊ ድጋፏን አጠናክራ እንደምትቀጥል ተግባብተዋል፡፡
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ለዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ እንደገለጹላቸው ከሩሲያ ወረራ ነፃ ለመውጣት የምታደርገው ሁሉንም ትግሏን በፅናት ትወጣ ዘንድ መተማማኛቸውን ሰጥተዋቸዋል፡፡
የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎድሞር ዘለንስኪ በበኩላቸው ቅዳሜ እለት አመሻሽ በሰጡት ማብራሪያ ማንም ቢሆን በክፋት ተነስቶ ሌሎችን ለማጥፋት ቢሰራ ራሱን እንደሚያጠፋ ሊገነዘብ ይገባዋል ማለታቸው ይታወሳል፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24