Get Mystery Box with random crypto!

ድብደባ ደርሶባቸዉ አካል ጉዳተኛ የሆኑ የፓርቲ አባላት እንዳሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት | AHADU RADIO FM 94.3

ድብደባ ደርሶባቸዉ አካል ጉዳተኛ የሆኑ የፓርቲ አባላት እንዳሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ገልጿል፡፡
የተለያየ የፓርቲ አባል ናችሁ በሚል ከሚደርሰዉ አፈናና ማስፈራሪያ ባሻገር ድብደባ ደርሶባቸዉ አካል ጉዳተኛ የሆኑ፤ የስነ ልቦና ቀዉስ የደረሰባቸዉና ፓርቲዎችን እንዳይቀላቀሉ የተደረጉ ግለሰቦች መኖራቸውን የተናገሩት የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ዋና ፀሀፊ ዶክተር ራሄል ባፌ ናቸዉ፡፡
ካለፈዉ አምስት አመት ወዲህ እያንዳንዱ ፓርቲና ፖለቲከኛ የራሱን ርዕዮት ይዞ በመምጣት የተሻለ ስርአት ይኖራል የሚል ተስፋ ተጥሎ የነበረ ቢሆንም መልሶ ወደ ቀድሞው ስርአት እንዲመለስ ሆኗልም ብለዋል፡፡
በተለይም በክልሎች በፓርቲ አባላትና አመራሮች ላይ እየደረሰ ያለዉ የሰብአዊ መብት ጥሰት አደገኛ እንደሆነ እና እየደረሰ ያለዉ ጫናም ቢሆን የፖለቲካ ስርአቱን የሚያዛባ ነዉ ሲሉ የችግሩን አሳሳቢነት የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ዋና ፀሀፊ አብራርተዋል፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24