Get Mystery Box with random crypto!

የአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ መቆራረጥ ችግርን ይፈታል የተባለ የኤሌክትሪክ ማሻሻያ ስራ በሚቀጥለው አመ | AHADU RADIO FM 94.3

የአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ መቆራረጥ ችግርን ይፈታል የተባለ የኤሌክትሪክ ማሻሻያ ስራ በሚቀጥለው አመት እንደሚጠናቀቅ የአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ በቀለ ክፍሌ ለአሐዱ እንዳሉት የአዲስ አበባን ኤሌክትሪክ መቆራረጥ ችግር ያስወግዳል ተብሎ ባለፈው ዓመት የተጀመረው የኤሌክትሪክ ማሻሻያ ስራ በተያዘው አመት ይጠናቀቃል ተብሎ የነበረ ቢሆንም በውጭ ምንዛሬና በሲሚንቶ እጥረት ምክንያት ተፈትኖ ቆይታል ብለዋል፡፡
የኤሌክትሪክ ማሻሻያ ስራው በአለም ባንክ ድጋፍና ብድር አማካኝነት በቻይና ባለሙያዎች የሚከናወን ሲሆን፣ በአዲስ አበባ ከተማ በሁሉም አከባቢዎች ተደራሽ እንደሚያደርግና የማሻሻያ ስራው የመስመር ዝርጋታ መቀየር፣ የኤሌክትሪክ ኃይል ማሻሻል፣የኤሌክትሪክ መስመር ፖሎችን መቀየር እንዲሁም ሌሎች ማሻሻያዎችን እንደሚያካትት የኮምኒኬሽን ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24